በትምህርት ዘርፉ የቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ውጤቶችን ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ
----------------------- // ----------------------
(መስከረም 19/2019 ዓ.ም) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያዘጋጀው እና የኢትዮጵያን የ50 ዓመታት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርምር፣ ኢኖቬሽንና ዲጂታላይዜሽን ጉዞ እንዲሁም ያለፉት 5 ዓመታት የትግበራ ስኬቶችን የሚያሳይ ብሔራዊ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።
በዚህ ጉባኤ ላይ የተለያዩ ተቋማት ሚኒስትሮች፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቀድሞ አመራሮች፣ የግሉ ዘርፍና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ በ1968 ዓ.ም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽንን በማቋቋም በዘርፉ ለ50 ዓመታት በርካታ ሥራዎችን መሥራቷ በጉባኤው ተነስቷል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በርካታ ውጤቶችን ማምጣቱን ጠቅሰው አሁንም ከዲጂታል ዘርፉ በተጨማሪ በባዮ እና ስፔስ ኢኮኖሚ ላይ የሚሠራው ሥራ ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም በትምህርት ዘርፉ የቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ውጤቶችን ተግባራዊ በማድረግ ትውልዱ ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው ባለፉት 50 ዓመታት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ላይ የተለያዩ ሥራዎችን ማከናወኗን ጠቁመዋል።
በተለይም ባለፉት አምስት ዓመታት ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ቴክኖሎጂን ከማላመድ አልፎ ወደ መፍጠር መሸጋገር መቻሉን አንስተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/19cna6n17A/

📢 ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተወዳድራችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ
ትምህርት ሚኒስቴር ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ የሆናችሁ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በተመዘገባችሁበት የምዝገባ ሊንክ በመግባት፣ ስማችሁን እና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን።
📌የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት
🔗 የምዝገባ ሊንክ፦ https://sbs.moe.gov.et/apply
ትምህርት ሚኒስቴር

Ministry of Education and Arizona State University Explore New Areas of Collaboration
---------------------------- //-----------------------
(October 9/2016) H.E. Ato Kora Tushune, State Minister for Higher Education and Development Sector at the Ministry of Education, held discussions with Dr. Kristin Lord, Vice President for Global Strategy and Engagement at Arizona State University (ASU), on strengthening collaboration and expanding innovative learning opportunities in Ethiopia’s higher education sector.
The discussion explored a range of potential areas of cooperation, including the establishment and strengthening of innovation and incubation centers, entrepreneurship development, employment-oriented initiatives through the Center for Entrepreneurship and Employment Development (CEED), and the advancement of Educational Technology (EdTech). Use this link for the detail: https://web.facebook.com/share/p/17j3cubDVp/

ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተመዝግባችሁ መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ
ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባቋቋማቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማር ሂደቱን እያከናወነ ይገኛል።
ሚኒስቴሩ በትምህርት ቤቶቹ የሚገኙ ተጨማሪ ክፍት ቦታዎችን በመጠቀም ተጨማሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የምዝገባ ዕድል አመቻችቷል።
በመሆኑም በትምህርት ቤቶቹ ባሉ ክፍት ቦታዎች ተመድባችሁ ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች ከታች በተጠቀሰው የምዝገባ ሊንክ በመግባት እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት
የምዝገባ ሊንክ፦ https://sbs.moe.gov.et/apply
የትምህርት ሚኒስቴር

📌 በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡
በጊዜያዊ ምደባ ሂደቱ ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጣራት ሥራ ተጠናቆ ምላሽ የተሰጠ በመሆኑ፣ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ በሚለው ማስፈንጠሪያ በመግባት መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የምደባ መረጃችሁ በቀጥታ ለየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚላክ ሲሆን፣ ተቋማቱ በሚያወጡት የጥሪ መርሃ-ግብር መሠረት በጊዜያዊነት ወደተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመሄድ ትምህርታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ።
እንዲሁም የተስትካከለ ምደባ ሊኖር ስለሚችል ከመሄዳቹህ በፊት በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባት https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ እንድታረጋግጡ ይሁን
📌 አዲስ ተማሪዎች፡
የምደባ ቦታችሁን https://student.ethernet.edu.et/view-placement/ በሚለው ማስፈንጠሪያ በመግባት ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፦ ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ስለሆነ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታችሁን መቀጠል የምትፈልጉ ተማሪዎች(በጊዜያዊነት የተመደባችሁትን ጨምሮ) ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚያወጡትን የጥሪ ማስታወቂያ በመከታተል ትምህርታችሁን በነበራቹሁበት መቀጠል እንደምትችሉ እናሳውቃለን።

የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎችን ማጠናከር የገጠሩንናና የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የመረጃና የትምህርት ተደራሽነት እንደሚያሳድግ ተገለጸ፤
---------------------- // -------------------
(ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም) የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ተገቢውን ማህበራዊ አገልግሎት በሚሰጡበት ሁኔታ በመዲናችን አዲስ አበባ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱም የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች የቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔትና የህትመት ሚዲያዎች ተደራሽ ባልሆኑባቸው እንዲሁም የቋንቋ ውስንነት ባላቸው የገጠርና አርብቶ አደር አካባቢዎች ዋና የመረጃ ምንጭ በመሆናቸው፣ አቅማቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ዩኔስኮ ባዘጋጀው መድርክ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ከማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ጋር ለሚተገብሩት ፕሮጀክት ውጤታማነት ከጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን ለወጣቶች የሚሰጡትን ትምህርታዊ አገልግሎት ጥራት ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ዩኔስኮ ዋና ጸሐፊ አቶ ዓለሙ ጌታሁን፤ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ለገጠሩና ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ያላቸውን ወሳኝ ፋይዳ አብራርተዋል።
አክለውም የፕሮጀክቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ወላጆች፣ መምህራን፣ የሃይማኖትና የማህበረሰብ መሪዎች፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም የአካባቢው ባለሥልጣናት በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ የሬዲዮ ጣቢያዎቹ ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/18XdzZ9wRh/