Ethio telecom
✔
308K subscribers
9.78K photos
229 videos
155 files
3.53K links
We Simplify lives & accelerate Ethiopia’s digital transformation & beyond via delivering reliable communications, innovative digital solutions & seamless financial services that empower communities, businesses & nations.

https://t.me/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
#በላቀ_አገልጋይነት

አዲሱን ዓመት በማስመልከት ከደንበኞቻችን ጋር ፍሬያማ ጊዜ አሳልፈናል!


በአዲስ ዓመት ዋዜማ፣ በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ መሪነት ከከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቻችን ጋር፣ በበዓል ድባብ የደመቁ የአገልግሎት ማዕከላቶቻችንን ጎብኝተናል።

“በላቀ አገልጋይነት” በሚል መሪ ሐሳብ ባከናወነው ዓመታዊ መርሐ-ግብር፤ ደንበኞቻችንን በቀጥታ አገልግለናል፤ ስለ ምርቶችና አገልግሎቶቻችን ያላቸውን አስተያየትና ፍላጎትም በቅርበት አዳምጠናል።

ይህ ጉብኝታችን በኩባንያችን “ሰው-ተኮር” ስትራቴጂ መሠረት ደንበኞቻችንን ይበልጥ ለመቅረብ፣ ፍላጎቶቻቸውን ለመረዳትና በኩባንያችንና በደንበኞቻችን መካከል ያለውን አብሮነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው።

በዕለቱ በአራብሳ አዲስ የከፈትነውን የአገልግሎት ማዕከል በመጎብኘት፣ ከሽያጭ ማዕከላቱ የሥራ ባልደረቦቻችንና ከደንበኞቻችን ጋር በመሆን አስደሳች የአዲስ ዓመት መርሐ-ግብር አሳልፈናል።

#Ethiotelecom #telebirr #HumanCentric #NewYear2019
❤41👍15👏4
#በላቀ_አገልጋይነት

የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የበዓል ድባብን በተላበሱ የአገልግሎት ማዕከሎቻችን በመገኘት ውድ ደንበኞቻችንን በላቀ የአገልጋይነት መንፈስ አስተናግደዋል።

ከደንበኞቻችን ጋር የአዲስ ዓመት ደስታን በመጋራት፣ ፍቅርና መልካም ምኞት የተሞላበትን የአዲስ ዓመት መልዕክት አድርሰዋል።

የደንበኞቻችንን እርካታና አጠቃላይ ተሞክሮ ማሻሻልን ማዕከል በማድረግ፣ በሰው ተኮር የአገልጋይነት ባህል የታጀበ ልዩ ቆይታ ነበረ።

​ተጨማሪ ምስሎች 👉 https://bit.ly/4qYDdG3


🌼 መልካም አዲስ ዓመት!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
❤35👍23👏3😍3
🎁 ከውጭ አገራት የአየር ሰዓትና ጥቅል ይቀበሉ፤ 50% ተጨማሪ ስጦታ ያግኙ!

🌼 ለአዲስ ዓመት ከባህር ማዶ በአጋሮቻችን በኩል ከ200 ብር ጀምሮ የተላከልዎን የሞባይል አየር ሰዓት ወይም ጥቅል ሲቀበሉ ለ15 ቀናት የሚያገለግል የ50% ተጨማሪ ስጦታ እናበረክትልዎታለን፡፡

ደንብና ሁኔታዎችን: https://bit.ly/4j7iOcI ይመልከቱ!

👉 እስከ መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ም ብቻ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👍20❤14