Ethio telecom
✔
308K subscribers
9.78K photos
229 videos
155 files
3.53K links
We Simplify lives & accelerate Ethiopia’s digital transformation & beyond via delivering reliable communications, innovative digital solutions & seamless financial services that empower communities, businesses & nations.

https://t.me/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም በመላ ሀገራችን በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አደረገ

የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የመማሪያ ደብተር ልገሳ መርሃ-ግብሩን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን፤ በዚህም በመላ ሀገራችን በሚገኙ የተመረጡ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ 105,496 ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች 1,265,952 የመማሪያ ደብተሮች ድጋፍ ተደርጓል።

ኩባንያችን #ለነገ_ተስፋዎች በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው ይህ የአዲስ ዓመት የደብተር ልገሳ፤ ከ113.3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን፣ ዓላማውም ተማሪዎች በትምህርት መርጃ መሣሪያዎች እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ተስፋ ለመስጠትና ለመደገፍ ነው።

ኩባንያችን በሚከተለው ሰው-ተኮር ስትራቴጂ መሠረት፣ የደብተር ድጋፉ አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ በአዲስ አበባ እና በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች አዲሱ የትምህርት ዘመን ከመጀመሩ በፊት የሚከናወን ነው።

ይህ ተግባር በስትራቴጂያችን ተካትቶ በዕቅድ የሚተገበር ሲሆን፤ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራትና በማህበረሰቡ ውስጥ የመደጋገፍ ባህልን ለማጎልበት የምናደርገው ተከታታይ ጥረት አካል ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ሰባት ተከታታይ ዓመታት ለ483.8 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከ434.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አድርጓል።

#ለነገ_ተስፋዎች
#ከግንኙነት_ባሻገር_ለወገን_አጋር!
#በአዲስ_ጅማሮ_በአዲስ_ተስፋ_በአዲስ_ዕይታ_2019አዲስ_ዓመት!

#Ethiotelecom #NextHorizon #CSR #ESG #GSMA #OECD #G6countries
❤112👍18🙏10👏7😢5🥰4😁2🤔2🤩2
#በላቀ_አገልጋይነት

በላቀ አገልግሎትና በሙሉ ትጋት የምንጀምረው ስኬታማ የሥራ ሳምንትና ብሩህ አዲስ ዓመት ይሁንልን።

መልካም የሥራ ሳምንት!

#በአዲስ_ጅማሮ_በአዲስ_ተስፋ_በአዲስ_ዕይታ_2019_አዲስ_ዓመት

#Monday #MondayMotivation
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👍21❤16🙏5👌4🥰1
🎉 🎁 በበዓሉ 12% ስጦታ ተገኝቶ ነው!

ለአዲስ ዓመት እስከ መስከረም 19፣ 2019 ዓ.ም. ከባሕርማዶ በቴሌብር ሬሚት ወይም በአጋሮቻችን በኩል ሐዋላ ስንቀበል 12% ተጨማሪ ስጦታ እናገኛለን።

ለሚቀበሉት እያንዳንዱ 1 ዶላር፣ 1 ብር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ይለገሳል!

🎉 በተጨማሪም 400 ዶላር እና ከዚያ በላይ ሲቀበሉ የአሜሪካ ደርሶ መልስ የአየር ትኬት፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ስልክ፣ በጎች፣ አስቤዛ፣ የ6 ወር የብሮድባንድ አገልግሎት ክፍያ፣ የበዓል ገንዘብ ሽልማት እና የወርሃዊ 1 ጊ.ባ. ዕጣ ሽልማት ያገኛሉ።

*127# ደውለን ወይም የቴሌብር ሱፐርአፕን https://bit.ly/telebirr_SuperApp ጭነን ሐዋላችንን ስንቀበል እንዲህ ነን!

#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን
#ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን
#ስንጭን_እንዲህ_ነን
#ስናስጀምር_እንዲህ_ነን
❤26👍13🙏7
ኩባንያችን በመላ ሀገራችን ከሚገኙ ከ50 በላይ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ጋር ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር የ2019 አዲስ ዓመት አቀባበል መርሃ-ግብር አከናውኗል።

ይህ መድረክ “ከግንኙነት ባሻገር ለወገን አጋር” በሚል መሪ ሀሳብ፤ ለሌሎች ተስፋ ለሚሰጡ ተቋማት ዕውቅና ለመስጠትና የሰዎችን ሕይወት በመለወጥ ረገድ በጋራ የተመዘገቡ ስኬቶችን ቃኝተዋል።

የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፤ ማህበራዊ ኃላፊነት ከተረፈን የምንሰጠው ሳይሆን የሰብዓዊነት ዕሴታችንና የሰው-ተኮር ስትራቴጂያችን መገለጫ ነው።

አክለውም፤ በመርሃ-ግብሩ ለተገኙና በመላው ሀገራችን ሕፃናትን፣ አረጋውያንንና ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ለሚረዱ ተቋማት በሙሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የበጎ አድራጎት ተቋማቱ ለሌሎች ተስፋ እንደሰጡ ሁሉ፤ ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮምም ከጎናቸው በመሆን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ የሁልጊዜም ተስፋ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

የበጎ አድራጎት ተቋማቱ በበኩላቸው ኢትዮ ቴሌኮም ቴክኖሎጂን ለሰብዓዊነት በማዋል በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ገቢ ከማሰባሰብ ባለፈ፣ በገንዘብና በሞራል አለኝታ በመሆን የሚያደርግላቸውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አርአያነት እንዳለው ገልጸዋል።

ኩባንያችን አዲሱን ዓመት በአዲስ ጅማሮ፣ ተስፋና ዕይታ በመቀበል፤ ሰውን በማክበርና ለሀገር ዕሴት በመፍጠር ረገድ ያለውን አገራዊ አጋርነት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

ፕሮግራሙን ለመመልከት፡ https://bit.ly/3V1j8CV ይጫኑ

#በበጎነት
#ከግንኙነት_ባሻገር_ለወገን_አጋር
#አዲስ_ዓመት_2019
#Ethiotelecom #CSR
❤40👍17👏4😁4🥰3👌2
🎉🌼 አዲሱን ዓመት ከሰራተኞችዎና ከደንበኞችዎ ጋር በአደይ አበባ ኢንተርፕራይዝ የበዓል ፓኬጅ ያክብሩ።

ለድርጅቶች ስጦታና ለሰራተኞች እውቅና መስጫ ተደርጎ የተዘጋጀው እያንዳንዱ ፕላን ቅናሽ የተደረገባቸውን የድምፅ፣ የዳታና የSMS ጥቅሎች እንዲሁም የ25% ተጨማሪ ስጦታ ያካትታል።

📍 በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የድርጅት አገልግሎት ማዕከል ጎራ ይበሉ ወይም
📩 Corporate.Enterprise@ethiotelecom.et ያግኙን!

#EnterpriseSolutions
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👍37❤36😁4💔1
Live stream started
Live stream finished (40 minutes)
🎉🏆 ልዩ የሚያሸልም የአዲስ ዓመት የተሳትፎ ውድድር!

አዲስ ዓመት ሲመጣ ትዝ የሚልዎን ወዳጅ ሜንሽን ያድርጉ፤ ወዳጅዎ ምላሻቸውን በኮመንት ካስቀመጡ እርስዎ ወደ ዕጣ ዝርዝራችን በመግባት 10GB ተሸላሚ ይሆናሉ!

👉 ከአንድ በላይ ሰው ሜንሽን አድርገው በአንዱ ምላሽ ካገኙ ወደ ዕጣው ዝርዝር ይገባሉ

✍️ መልስዎን በፌስቡክ ወይም ትዊተር አስተያየት መስጫ ላይ ያኑሩ!

#NewYearContest
#Ethiotelecom  #telebirr
#telebirrSuperApp #DigitalEthiopia
#RealizingDigitalEthiopia
👍32❤30😡7🤩6😢3👏1