SMH General Construction
22.5K subscribers
1.48K photos
45 videos
293 files
1.18K links
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም

👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(Eng sintayehu melese)

tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons

ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ
Download Telegram
          🌟Online Class (With Certificate)

1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software

🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken

🫵For Registration - 0948552002  Or @AbelMuluken

🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution

🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
👍3😍1
"አድዋ-00 ሙዚየም"❤️

https://t.me/ethioengineers1
👍10❤5🤔1
አርክቴክቱ እስክንድር ውበቱ🦺
👍27👏6
💥የግዙፉ አድዋ ሙዚየም ኪነ ህንጻ በዋና አርክቴክቱ እስክንድር ውበቱ አንደበት

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአርክቴክቸር እና የከተማ ፕላን ምሩቁ እስክንድር፤ ህንጻዎችን ሲነድፍ 28 ዓመት ገደማ አሳልፏል። ከሥራዎቹ መካከል አዲስ አበባ ሰንጋ ተራ አካባቢ የሚገኘው ባለ 37 ወለሉን የሕብረት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት “ሕብር ታወር” ተጠቃሽ ነው።

ከእስከ ዛሬ ሥራዎቹ መካከል ትልቁ ደግሞ ፒያሳ ላይ የተዘረጋው የአድዋ ሙዚየም ነው።

እንደ እስክንድር አገላለጽ ይህ ፕሮጀክት፤ እንደ ሌሎች ሥራዎች የደንበኛን ፍላጎት በህንጻ ንድፍ የመተርጎም ሥራ ብቻ አይደለም። “ከ1.5 ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ የሚቀመጥ ነገር ህንጻ ብቻ አይደለም” የሚለው እስክንድር፤ በትምህርት፣ በሙያ እና በንባብ ያሰባሰበውን የ“ኧርባን ዲዛይን” ጽንሰ ሀሳብ በትልቅ ደረጃ ሙከራ (experiment) ያደረገበት መሆኑን ይገልጻል።

▪ አርክቴክት እስክንድር እና የአድዋ ሙዚየም መገጣጠም

የአድዋ ሙዚየምን የሚገነባው ተቋራጭ “ቻይና ጂያንግሱ ኢንተርናሽናል” ከእስክንድር ጋር ሲሠራ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። እስክንድር የነደፈውን የሕብረት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንጻን የገነባው ይህ ኩባንያ ነበር።

በ2011 ዓ.ም. የአድዋ ሙዚየምን ለመገንባት ጨረታ የወጣው ከቤተ መንግሥት ፓርኪንግ እና ከአብርሆት ቤተ መጽሐፍት ፕሮጀክቶች ጋር በአንድ ላይ እንደነበር እስክንድር ያስታውሳል። እነዚህን ፕሮጀክቶች ለመገንባት የሚጫረቱ ተቋራጮች የህንጻውን ንድፍ የሚሠራ የአርክቴክት ድርጅት አብረው ማቅረብ ነበረባቸው።

በዚህ ጨረታ ላይ የሚወዳደረው ጂያንግሱ ኢንተርናሽናል ለኢትዮጵያዊው የአርክቴክቸር ድርጅት “እስክንድር አርክቴክትስ” የእንጣመር ጥያቄ አቀረበ።

“እነዚህን ፕሮጀክቶች ሲጫረቱ ከፕሮጀክቶቹ ውስጥ ‘የትኛው ውስጥ መሳተፍ ትፈልጋለህ?’ ተብሎ ነው [ጥያቄው] የመጣው። ከነበሩት ውስጥ ይበልጥ ሊፈትነኝ የሚችል እና ሀሳቡም በጣም ቅንጭብ ሆኖ የቀረበ ስለሆነ፤ ብዙ ዲዛይን የማድረግ ዕድል ስለሚኖረኝ አድዋን መርጬ ከቻይና ጂያንግሱ ግሩፕ ጋር ተጣማሪ ሆነን እዚህ ውስጥ ገባን” ይላል ሥራው የመጣበትን አጋጣሚ ሲያስታውስ።

ፕሮጀክቱን ያስጀመረው በቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የሚመራው የከተማዋ አስተዳደር የሚገነባውን ህንጻ በተመለከተ ያስቀመጣቸው የመነሻ ሀሳቦች ነበሩ። ህንጻው የሚኒሊክ ሀውልት ከሚገኝበት መንገድ እኩል ሆኖ እንዲጀምር እና እጅጉን ከፍታ ያለው እንዳይሆን ማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ መነሻዎች ውስጥ አንዱ ነው።

በሙዚየሙ ህንጻ ላይ የሰንሰለታማ ተራራ እና የነጋሪት ሀሳቦችን እንዲጸባረቁ ማድረግም የከተማ አስተዳደሩ መስፈርቶች ነበሩ። እነዚህ ሀሳቦች እንዴት ይካተቱ የሚለው ደግሞ የህንጻ ነዳፊው እስክንድር ፈጠራ ነው።

“የራሴን ሀሳቦች እንድጨምር ነጻነት ነበረኝ” የሚለው አርክቴክቱ፤ “ሁልጊዜ የሚጠየቀውን ኢትዮጵያዊ ኪነ ህንጻ” ለመሥራት ሙከራ ማድረጉን ይናገራል።

▪ ከሚኒሊክ ሀውልት ጋር ፀሐይ የሚጋራው የምድር ቤት ነጋሪት

በ3.3 ሄክታር ላይ ያረፈው የአድዋ ሙዚየም ቁመቱን ከፍ ያደረገ አንድ ወጥ ህንጻ አይደለም። በተለያዩ መንገዶች የተሳሰሩ እና የአጠቃላይ ህንጻው አካል የሆኑ የተለያዩ ስብስቦችን (ሰብ ሴቶችን) የያዘ ነው።

ወደ አድዋ ሙዚየም የሚያስገቡት አራት ዋነኛ መግቢያዎች፤ የሚያደርሱት የተለያየ ገጽታ እና አገልግሎት ወዳላቸው የህንጻው ክፍሎች ነው። መግቢያዎቹ ስያሜያቸው የደቡብ ጀግኖች፣ የሰሜን ጀግኖች፣ የምሥራቅ ጀግኖች እና የምዕራብ ጀግኖች የሚል ነው።

እስክንድር፤ “ታሪክ እንደሚያሳየው ከሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ [ጦርነቱ ላይ] ተሳትፎ ተደርጓል ነው። ስለዚህ ሁሉም በአቅጣጫ ተወክለዋል። የበሮቹ ስያሜ ሲሰጥ ስሜቱም፣ ተመሳሌትነቱም እርሱ ነው” ይላል ከስያሜው ጀርባ ያለውን ምክንያት ሲያስረዳ።

ከአድዋ ጦርነት ጋር የተያያዙ ቅርሶች የሚቀመጡበት ሙዚየም የሚገኘው በሚኒሊክ ሀውልት በኩል ባለው የሰሜን ጀግኖች መግቢያ ነው። ይህ መግቢያ ሀውልቱ ከሚገኝበት መንገድ እኩል (flat) ሆኖ የሚጀምር ሲሆን ለአድዋ ድል በዓል ማክበሪያ የሚውል ሰፊ ፕላዛን ይዟል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ የአድዋ ድል በዓል በዚህ ስፍራ ላይ እንደሚከበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

በአድዋ ድል በዓል ማክበሪያው ስፍራ መሀል ላይ በአንድ ጎኑ ከፍ ያለ ባለመስታወት ክብ ቅርጽ ተቀምጧል። ከመስታወቱ ስር የሚገኘው፤ ምድር ቤት (basement) ውስጥ የተሠራው ባለ ሁለት ወለል ሙዚየም ነው።

መስታወቱ፤ አስፓልቱን ተሻግሮ ባለው የሚኒሊክን ሀውልት ላይ የምታርፈውን ፀሐይ ወደ ታች አውርዶ ምድር ቤት በሚገኘው ሙዚየሙ ውስጥ ተፈጥሯዊ ብርሃን ይፈነጥቃል። በክብ መስታወት (circular skylight) በኩል 20 ሜትር ቁልቁል የሚወረወረው የፀሐይ ብርሃን ማረፊያው ደግሞ በሙዚየሙ መሀል፣ ከመስታወቱ ትይዩ የተቀመጠ ነጋሪት ነው።

እስክንድር የነጋሪቱን አቀማመጥ ሲገልጽ፤ “የሙዚየሙ መጀመሪያም፣ ማጠንጠኛም ነው” ይላል።

“ጦርነት ሲገባ፣ አዋጅ ሲነገር፣ ክተት ሲታወጅ የሚጎሰመው ነጋሪት ነው። ነጋሪቱ መሃል ላይ ሆኖ የሙዚየሙ የትኩረት ማዕከል (focal point) ነው፤ መነሻም ነው። ሙዚየም ውስጥ ስትገባ ጉብኝትህን ከአንድ ነገር ትጀምራለህ” ሲል ያብራራል።

“ሙዚየሙ ራሱ ሙሉ በሙሉ ከመሬት በታች ነው ያለውና ቀጥታ የሚመጣልህ ብርሃን ነው” የሚለው አርክቴክቱ፤ “ብርሃንን ቀርጾ ማስገባት እና በብርሃን መጫወትን” ሙከራ ያደረገበት የህንጻው ክፍል መሆኑን ያስረዳል።

እስንክድር፤ በህንጻው ንድፍ ላይ ደጋግሞ ያንጸባረቀው ሌላኛው ሀሳብ የአድዋ ጦርነት የተካሄደበትን ምድረ ገጽ የሚወክለው ሰንሰለታማ ተራራ ነው። የህንጻው የውስጥ እና የውጭ ጎኖች፣ የደረጃ መደገፊያዎች ላይ በተቀመጡት ወጣ ገባ እያሉ አግድም በሚሄዱ መስመሮች እንዲሁም በደረጃ ፋንታ በተቀመጡት ተዳፋቶች (ramp) ላይ መንጸባረቁን እስክንድር



https://t.me/ethioengineers1
👍19❤1
ተራራ “በአርክቴክቸራል ቋንቋ” ከተገለጸባቸው የህንጻው ክፍሎች ውስጥ አንዱ በማዘጋጃ ቤት በኩል የሚገኘው መግቢያ ነው። በዚህ መግቢያ ላይ ከደረጃ ባሻገር የተቀመጠው ዚግ ዛግ የሚሄድ ተዳፋት (ramp) ከርቀት ሲታይ የተራራ ይመስላል።

በዚህ መግቢያ ወደ የሚዘልቁ ጎብኚዎች ደረጃውን እንደጨረሱ የሚያገኙት እቴጌ ጣይቱ በመቀለው ውጊያ የውሃ ምንጮችን በመያዝ የጣልያን ጦር እጅ እንዲሰጥ ለተጠቀሙት ስልት መታሰቢያነት የዋለ የውሃ ፋውንቴን ነው።

ተራራማ እና ድንጋያማ አካባቢን በአድዋ ሙዚየም ላይ የማንጸባረቅ ሀሳብ፤ የህንጻው ቀለም ላይም ታይቷል። በተለይ በህንጻው የውጭ ክፍል ላይ ጎልቶ የሚታየው ቀለም “ሸክላ መሳይ” ነው።

ከህንጻው ትልቅነት አንጻር የተለያዩ ቀለማትን መጠቀም ይቻል እንደነበር የሚናገረው እስክንድር፤ ይበልጥ “ተፈጥሯዊ ነው” ብሎ ያሰበውን ይህንን ቀለም በብቸኝነት መጠቀሙን ይገልጻል። “ተራሮቹን የበለጠ የመግለጽ አቅም ያለው ቀለም ነው። ለህንጻውም የራሱ መገለጫ ሰጥቶታል” ይላል።

▪ ድንጉዛ በፒያሳ

እስክንድር፤ አንድ ህንጻ ሲሠራ ለአካባቢው እና ለነዋሪዎች የሚያስተላልፈው “ጥበብ” ሊኖረው ይገባል የሚል እምነት አለው።

በአድዋ ሙዚየም ላይ “ሞክሬዋለሁ” የሚለው ዋነኛው ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ምልክቶች እና መገለጫዎችን በህንጻ ዲዛይን ውስጥ የማካተት ሀሳብን ነው።

“ሌሎች አገራት ላይ ብዙ ፓተርኖች ላይ ኤክስፐርመንት ያደርጋሉ። እኛ አሁን ማየት ያለብን ወደ ውጭ ሳይሆን ወደ ውስጥ ነው። እነዚህን ነገሮች መሞከር እፈልግ ነበር” ሲል የህንጻን ገጽታ ከአገርኛ አውድ ጋር (local context) ጋር የማስተሳሰር ሙከራው በዚህ ፕሮጀክት መጀመሩን ያስረዳል።

በኢትዮጵያ ባህል ውስጥ “ያልታዩ ጥበቦች” መኖራቸውን የሚያነሳው እስክንድር፤ “ዘመናዊ ነገር እንሥራ ማለት አይደለም። በብዙ መልኩ እኛን የሚመስል ነገር [ወደ ማስቀመጥ] ነው መሄድ ያለብን” ይላል።

በአድዋ ሙዚየም ላይ ያካተተው አንዱ አገርኛ ምልክት በደቡባዊ ኢትዮጵያ በጋሞ እና በወላይታ አካባቢዎች የሚለበሰው “ድንጉዛ” ነው። በደማቅ ቀይ፣ ቢጫ እና ጥቁር ቀለሞች ዐይን የሚገባው ድንጉዛ፤ በጥለቱ ላይ የሚቀመጡት ወጣ ገባ ያሉ መስመሮችም መለያዎቹ ናቸው።

ይህን የድንጉዛ ጥለት የመስመር አካሄድ ከ100 ሜትር በላይ በሚሄድ የህንጻው ክፍል ላይ ተንጸባርቋል። በህንጻው የውጪ ክፍል ላይ የሚገኙት የጦር እና ጋሻ ምልክቶች የተቀረጹት በድንጉዛ የመስመር አካሄድ በተቀመጡ ቅርጾች ላይ ነው።

ከአክሱም ሀውልት እና ከላሊበላ ኪነ ህንጻ የተወሰዱ ምልክቶችም በህንጻው የደረጃ ድጋፎች እና የኮሪደር ስፍራዎች ላይ ማንጸባረቁንም አርክቴክቱ ይናገራል።

▪ የድሮዋ ፒያሳ መልክ በአዲሱ የአራዳ ምልክት ላይ

የንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት፤ አዲስ አበባ አሉኝ የምትላቸው ኪነ ህንጻዊ ውበትን የተጎናጸፉ ህንጻዎች የተገነቡበት ነው። ብሔራዊ ቲያትር፣ ማዘጋጃ ቤት እና የንግድ ባንክ የቀድሞ ዋና መሥሪያ ቤት ከእነዚህ ህንጻዎች መካከል ናቸው።

እነዚህን ህንጻዎች የተነደፉት እንደ ፈረንሳዊው ሄንሪ ሾሜት እና ጣልያናዊው አርትሮ ሜዜዲሚ ባሉ የውጭ አርክቴክቶች ነው። እስክንድር፤ “የአካባቢውን ሁኔታ አጥንተው አካባቢያዊ አውዱን (local context) ለማምጣት የሚሞክሩ አርክቴክቶች ነበሩ” ሲል ያሞካሻቸዋል።

የእነዚህ ህንጻዎች አንድ መገለጫ ከፊታቸው አጭር ሆነው ለእግረኛ መረማመጃ ስፍራ መፍጠራቸው ነው። “የአራት ኪሎ መደዳው እና ዞሮ ወደ ፒያሳ ሲመጣ [ህንጻዎች] በደረጃዎች እተገናኙ አርኬድ (ታዛ) አላቸው። እግረኛ በምቾት፣ በጥላ እንዲሄድ ነው” የሚለው አርክቴክቱ፤ የፒያሳ ህንጻዎች ከመንገዱ ጋር “በጣም የተናበቡ” መሆናቸውን ያነሳል።

“ከፒያሳ የምወስደውን የበፊት (traditional) ፕላኒንግ ልበለው። አሁን ዘመናዊ ፕላኒንግ ደግሞ አለ። እኔ ወደዚያ [ወደበፊቱ] ነው መመለስ የምፈልገው። ያ ጥሩ ፕላኒንግ ነው” የሚለው አርክቴክቱ በአድዋ ሙዚየም ላይ እግረኛ የሚራመድባቸው ታዛዎችን መፍጠሩን ያስረዳል።

በሙዚየሙ ህንጻ ውስጥ የሚገኙት መደብሮች ደጃፋቸው እንደ ፒያሳው መብራት ኃይል ህንጻ እግረኛን የሚያስተናግዱ ናቸው።

ከአራዳ ህንጻ ጋር አዋሳኝ በሆነው አቅጣጫ የሚገኘው የአድዋ ሙዚየም ደግሞ ሌላኛው የፒያሳ ገጽታ ምሳሌ አድርጎ የተነደፈ ነው። በሙዚየሙ ሁለት ብሎኮች መካከል ረጅም ደረጃ የተዘረጋበት ይህ የደቡብ ጀግኖች መግቢያ፤ ከፒያሳው 70 ደረጃ ጋር ተመሳሳይነት አለው።

▪ የአድዋ ሙዚየም ሀውልቶች እና የሚነሱ አስተያቶች

የአድዋ ሙዚየም የህንፃ ንድፍ ሲሠራ ከጦርነቱ ጋር የተያያዙ 40 ገደማ ቅርጾች እንደተካተቱበት እስክንድር ይናገራል። ከእነዚህ የሚቆሙ እና በግድግዳ ላይ የሚለጠፉ ቅርጾች ውስጥ ግማሾቹ መሠራታቸውን የሚገልጸው አርክቴክቱ፤ “የተወሰኑት ወደፊት ይሰራሉ” ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅሷል።

በአሁኑ ጊዜ ተቀርጸው ከቆሙት ሀውልቶች መካከል የአጼ ሚኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ እንዲሁም 12 የጦርነቱ አዝማቾች ይገኙበታል። የአጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ሀውልት የውሃ ፋውንቴን በሚገኝበት ፕላዛ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠዋል። የጦር አዝማቾች ሀውልት ደግሞ በከተማ አዳራሽ የውጨኛ ክፍል ላይ በሚገኙት አምዶች ላይ ተቀምጠዋል።

እንደ እስክንድር ገለጻ የሀውልቶቹን አቀማመጥ በተመለከተ መጀመሪያ የሠራው ንድፍ ላይ ተጨማሪ ሀሳቦች ተካትተዋል። በንድፉ ላይ የ12ቱ የጦር አዛዦች ሀውልቶች በአንድ እልፍኝ ላይ እንዲቀመጥ ተደርጎ ነበር። የእቴጌ ጣይቱ ሀውልት ደግሞ በመቀለው ጦርነት ንግሥቲት ላመጡት የጦርነት ስልት መታሰቢያ በተሠራው የውሃ ፋውንቴን መሃል ላይ እንዲሰፍር ተነድፎ ነበር።

የእነዚህ ሀውልቶች ፎቶግራፍ በሶሻል ሚዲያ ገጾች ላይ ከተሰራጨ በኋላ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ተደምጠዋል። በቅሬታ መልክ ከተነሱት አስተያየቶች ውስጥ የሀውልቶቹን የቁመት መጠን እና ገጽታ እንዲሁም የተሰሩበት ቁስን የተመለከቱ ይገኙበታል። የሠዓሊያን እና የቀራፂያን ማኅበር በሙዚየሙ ቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች ላይ “አልተሳተፍኩም” ማለቱም ሌላኛው አስተያየት ነበር።

የሀውልት እና ሌሎች የቅርፅ ሥራዎች የሚከናወኑት ከ20 እስከ 25 አባላት ባሉት የቀራፂያን ቡድን መሆኑን የሚናገረው እስክንድር፤ “በፎቶግራፍ የተደገፉ የታሪክ መጽሐፍትን ይዘው፤ ጊዜው በቂ እንኳን ባይሆን [የሀውልቶቹን] ገጽታ ከዚያ ላይ እያጠኑ ሠርተዋል። ይህንን አይቻለሁ” ይላል።

ይሁንና የቅርጽ ሥራዎቹ ቀድመው ተጀምረው ለጥናት ሰፊ ጊዜ መሰጠት እንደነበር ይገልጻል።

አርክቴክቱ እንደሚያስረዳው በአድዋ ሙዚየም ውስጥ ከሚቀመጡት የቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች መካከል “ወሳኝ” የሆኑት ከነሐስ እንዲሠሩ በህንጻው ንድፍ ላይ ሰፍሯል። ይሁንና በአሁኑ ሰዓት ለሀውልቶቹ ግንባታ ጥቅም ላይ የዋለው ቁስ ሌላ መሆኑን አመልክቷል።

“እኛ ስናስቀምጥ ወሳኝ ሥራዎች በነሐስ እንዲሠሩ ተቀምጧል። የተያዘላቸው የሥራ ዝርዝር እንደዚያ ነው። በዚህኛው ግን አሁን ለማስመረቂያ ስለማይደርሱ፤ በመቀጠል የነሐስ ሀውልቶች እንደሚሠሩ ነው የማውቀው” ሲል በህንጻው ንድፍ ላይ በተቀመጠው መሠረት ሀውልቶቹ በድጋሚ ይሠራሉ የሚል እምነቱን ገልጿል።

ሀውልቶቹ አሁን የተሠሩበት ቁስም ቢሆን ግን ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ቅርፆችን ለመሥራት ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑን አስረድቷል።


https://t.me/ethioengineers1
👍13❤2
ከቅርፅ ሥራዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱትን አስተያየቶች እንደሚጋራ የሚናገረው እስክንድር፤ “የአርት ሥራን መልሶ አሻሽሎ መሥራት፣ መለወጥ ይቻላል” ይላል። በአሁኑ ሰዓት ያልተሠሩት የቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች ሲከናወኑ “ከዚህ ልምድ ተወስዶ የሚቀጥለውን ሂደት በማሳተፍ፣ ጊዜ በመስጠት እና በጥናት ይበልጥ ቢኬድበት” የሚል ምክረ ሀሳቡን አስቀምጧል።

የሀውልቶቹን ሥራ ጨምሮ ከዋና ንድፍ ላይ ለውጥ የተደረገባቸው ነገሮች ቢኖሩም “90 በመቶ በሚባል ደረጃ” ያስቀመጠው አርክቴክቸር ወደ ተግባር መተርጎሙን እስክንድር ይናገራል። የአድዋ ሙዚየም ግንባታ “በአስቸጋሪ” ሁኔታ ውስጥ የተከናወነ መሆኑን በመጥቀስም ጥሩ ሥራ መሠራቱን ያስረዳል።

ከሙዚየሙ ግንባታ ጋር የሜካኒካል፣ የኤሌክትሪካል እና የኦዲዮ ቪዥዋል ሥራዎችም “በጣም በከፍተኛ ሁኔታ” መከናወናቸውን በመግለጽ፣ በግንባታው ሂደት ጥቅም ላይ የዋሉት እቃዎችም ደረጃውን የጠበቁ እንደሆኑ አክሏል።

እስክንድር፤ “ለአድዋ በሚመጥን መልኩ ያለንን ሁሉ ሰጥተን ሠርተነዋል። ለብዙ ጊዜ ሌሎች ሥራዎችን ሳንሠራ ሁልጊዜ እዚህ ጋር ነን። ማንኛውም እንደዚህ [ዓይነት] ኪነ ህንጻ ሲሠራ ፍጹም ሊሆን አይችልም፤ ብዙ ትችቶች እንደሚመጡ አውቃለሁ። ግን ባለን አቅም ሁሉ የምንችለውን ጥረት አድርገን [ሠርተነዋል]” ይላል።

እስክንድር ወደ ሦስት አስርት ዓመታት እየተጠጋ ባለው የሥራ ልምዱ ውስጥ ትልቁ ስለሆነው ፕሮጀክት ሲያነሳ፤ “በውጭም ዓለም ሙዚየምን የሚሠራ አርክቴክት ‘ዕድለኛ ነው’ ይባላል። በክፍለ ዘመን [አንዴ] የሚመጣ ዕድል ሊሆን ይችላል። እጅግ በጣም ዕድለኛ ነኝ” ሲል ስሜቱን ለቢቢሲ አጋርቷል።

ምንጭ: ቢቢሲ አማርኛ


https://t.me/ethioengineers1
👍16
🌟የ ኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከ መሬት ወይም ከወለል ያላቸው ከፍታ

✨(Electrical Accessories Height from the floor):-

☑️ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ማለትም ማብሪያና ማጥፊያ፣ ሶኬት፣ ቆጣሪ፣ ዲስትሪቢዩሽን ቦርድ ወ.ዘ.ተ. ከወለል  ያላቸውን ከፍታ ነው የምናየው።
☑️ብዙዎቻችሁ ስለነዚህ አክሰሰሪዎች ትክክለኛ ቦታ ለማወቅ ብዙ መፅሐፍ አንብባችሁ ይሆናል፤ ምናልባት ትክክለኛ መረጃ አላገኝ ብላችሁ ግራ ተጋብታችሁ ይሆናል፤ ወይም ደግሞ አንፃራዊ  ትክክለኛ ቦታውን አውቃችሁ የምትሰሩም ትኖራላችሁ። ጭራሹንም ደግሞ ስለ አቀማመጡ ግድ የማይሰጣችሁ አስባችሁትም የማታውቁ መስራቱ ላይ ብቻ ትኩረት የምታደርጉ ትኖራላችሁ። ሁላችሁም ተከታተሉን መልሱን ታገኛላችሁ።
☑️አሜሪካን ሀገር የሚገኘው "ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ደንብ" ወይም "National Electrical Code" የተባለው የግል ድርጅት ስለሁሉም ጥቃቅን የሚባሉት እንኳን ሳይቀሩ በስፋት ህጎችንና መመሪያዎችን አስቀማጧል። አሁንም የአለማችን ሀገሮች እየተጠቀሙበት የገኛሉ። ነገር ግን የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ስላላቸው ከፍታ ምንም ያለው ነገር የለም።
☑️"አለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ደንብ" "International Electrical Code" ቢሆንም ግለፅ የሆነ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ስላላቸው ከፍታ ያስቀመጠው ነገር የለም።
☑️"የኢትዮጵያ ህንፃ ደንብ መመሪያ" ወይም "Ethiopian Building Code standard" የሚለው መፅሃፍም ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ህጎች በዚህ መፅሐፍ የሚዳኙ ቢሆንም አብዛኞቻችሁ እንዳያችሁትና ከስሙም እንደምንረዳው ለግንባታ/ለሲቪል ስራው ብቻ የተዘጋጀ ነው የሚመስለው ፤ ለማንበብ ስትሞክሩም እንቅልፍ ጠሪ ነው ። ራሱን የቻለ የኤሌክትሪክ ህግ የለም በዛ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ  ስራውም ተጠቅልሎ ለሲቪል ምህንድስናው ተሰቷል። እንኳን ስለኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች  ከወለል ስላላቸው ከፍታ ሌሎች ህጎችም መፅሐፉ ላይ የተጠቀሱት በግልፅ አልተቀመጡም።
☑️ ስለዚህ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች  ከወለል ያላቸው ከፍታ እነዚህ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ  ካልተጠቀሰ ለምን ከፍታቸውን ማወቅ አስፈለገ? ለምን እንደፈለግን አንዘረጋቸውም/አናስራቸውም?
🔸መለሱም አዎ በግልፅ የተቀመጠው ህግ ያላቸው ሀገሮች ሊኖሩ ቢችሉም። እንደምሳሌ በተጠቀሱት ላይ ግልጽፅ የሆነ ህግ የለም። ነገር ግን ለእይታ እንዳይደብር በማሰብ፣ ለመጠቀም ለሁሉም አምች እንዲሆን፣ አደጋን ለመቀነስ በማሰብ እንዲሁም  አቅመደካምችን፣ ህፃናትንና አካል ጉዳተኞችን ግምት ውስጥ በማስገባት የተለመደ የከፍታ መጠን አለ።

🔹ስለዚህ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች  ከወለል ያላቸው ከፍታ የስምምነት ወይም የምርጫ ጉዳይ ነው። ነገር ግን በጣምም ከፍም ሆነ ዝቅ ማለት የለባቸውም የተለየ ፍላጎት ከሌለ በስተቀር። በተቻለ መጠን ፊት ለፊት የሚታይና ለአጠቃቀም ምቹ ማድረግ ነው። በብዛት የምንጠቀምበት የተለመደ ከፍታ አለ እሱን ከማየታችን በፊት የበለጠ ትኩረት ስለሚገባን ነጥቦች እንይ:-

🔘አንዴ በጀመርነው ከፍታ መጨረስ። ይህ የአብዛኛው ሙያተኛ ችግር ነው። ነገር ግን መሆን ያለበት ቦታ ላይ  በተለያየ ምክንያት ማድረግ ካልቻልን ትንሺ ከፍ ወይም ዝቅ ልናደርግ እንችላለን። 
🔘በተቻለ መጠን አክሰሰሪዎች ተመሳሳይ ቀለም፣ መጠንና ቅርፅ  እንዲኖራቸው ማድረግ
🔘ስንገጥም ውሃ ላክችን መጠበቅ መንጋደድ የለበትም። ትንሽም ቢሆን።
🔘point ለመጨመር ወይም ለመቀነስ ተብሎ ለይታ ደስየማይልና ከተለመደው አስራር ውጭ በፍፁም አለመስራት።
🔘ለአቅመ ደካሞች(ለሽማግሌዎችና ለአዛውንቶች)ና ለአካል ጉዳተኞች ሲባል ሶኬቶችን በጣም ዝቅ ማለት የለባቸውም፤ ማብሪያ ማጥፊያዎች ደግሞ በጣም ከፍ ማለት የለባቸውም።
🔘በተቻለ መጠን በጣም ህፃን ልጆች ካልሆኑ በስተቀር ሁሉም የቤተሰብ አባል እራሳቸውን ችለው አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ።
🔘አዲስ ዝርጋታ ካለሆነ በስተቀር የሚቀየር ወይም የሚጠገን ከሆነ ከፍታውን ከሌሎች ጋር እኩል ማድረግ ነው ያለብን።
🔘የሻወር ቤት ወይም የመፀዳጃ ሶኬትና ማብሪያ ማጥፊያ በተቻለ መጠን ከፍ ማለት አለባቸው። ይህ ብቻ ሳይሆን ከውሃ መራቅ አለባቸው።
🔘በተቻለ መጠን ከማንኛውም ኮርነር፣ በር፣ መስኮት ወ.ዘ.ተ. 35cm መራቅ አለባቸው።

🔸እነዚህን ግንዛቤዎች ከያዝን በብዛት  የተለመደውንና ከላይ የጠቀስናቸውን መሰረት ያደረገ የከፍታ መጠን በቀጣይ እናያለን።

🔹በበዛት የተለመደውና አብዛኛቻችን የምንስማማበት የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ከወለል ያላቸው ከፍታ:-
የአክሰሰሪ ከወለል ያላቸው አይነቶች ከፍታ በ cm

1. ማብሪያ/ማጥፊያ ...130-140
2.ሶኬት ... 45-50
3.ዲስትሪቢዩሽን ቦርድ...170-175
4.ኪችን ሶኬት...90-100
5.አኑንሴተር...170-175
6.ቤል ስዊች...130-140
7. ቆጣሪ...175-180
8.ሻወር/መፀዳጃ ቤት ሶኬት..180-200
9. ሻወር/መፀዳጃ ቤት ማብሪያ ማጥፊያ...150

🚧ማሳሰቢያ:- ከዚህ በፊትም እንዳልነው ዋናው ነገር ለአጠቃቀም ቀላልና ምቹ ማድረግ ነው።

✨ስለዚህ  ቦታው ላይ ያሉትን ነገሮች ታሳቢ በማድረግ እንደሁኔታው ከፍም ዝቅም ማለት ይችላል።

Via Amen Electric


https://t.me/ethioengineers1
👍34😍3❤1
የአዲስ ኮንክሪት ጥሩ ባህርያት /Properties of Fresh Concrete/

▶️ኮንክሪት ለመብላለት/ለመደባለቅ/Mix/፣ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ/to transport/፣ለማስቀመጥ/deposit/ እና ለመጠቅጠቅ/Compact/Vibrate/ ቀላል ወይም ምቹ ሆኖ ሲገኝ ጥሩ ነው።

▶️የእነዚህ ጥምር ውጤት ኮንክሪቱ ከስራ ምቹነቱ ባሻገር ኮንክሪቱ ላይ የመግጠጥ ችግር እንዳይከሰት
/resistance to segrigation/ የሚረዳ ይሆናል።

▶️ከላይ የገለፅናቸውን ባህርያት ያሟላ ኮንክሪት «ምቹ»/Workable/ ነው ብለን የምንጠራው ይሆናል።

⏺እንዚህን ባህርያት የሚያሟላ መሆኑን የምናተጋግጥበት የስራ ምቹነት/ፅኑነት ምርመራ/ workability test/ Consistancy test ይባላል።

✨የኮንክሪት workability ላይ ተፅዕኖ ሊያደርሱ የሚችሉ ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

1ኛ.የውህድ ምጣኔ ትክክል አለመሆን/Mix ratio/

2ኛ. የጠጠር ወይም የአሸዋ የግርድፍ መጠናቸው/Gradation/ ወይም ቅርፅ/Shape/ልክ ያለመሆን

⏺የኮንክሪት workability እንዴት ማወቅ እንችላለን?

▶️በሳይት እና በቤተ ሙከራ ይህን የምናረጋግጥባቸው 4 መንገዶች አሉ።

🚧እነዚህም

⏺1. Slump test
⏺2.Compacting factor test
⏺3.Veebee test እና
⏺4.Vibro workability test ናቸው።

🚧ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት
/Slump test /Cone test/ or /Sand test/

💫የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በቀላሉ በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት
ሲሆን የኮንክሪትን ለስራ ያለውን ምቹነት (Workability) እና ፅኑእነት
(Consistency) ለመለካት ይጠቅማል።

🌟ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ወቅት መሰራት ያለበት ሲሆን በምን ዓይነት የጊዜ ልዩነት ወይም በየስንት መጠን መሰራት እንዳለበት በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል።

🌟ስላምፕ ቴስት በቀላል ወጪ የሚሰራ በመሆኑ ተመራጭ የመፈተሻ መንገድ ነው በዚህ ምክንያት ከ1922 GC ጀምሮ እስካሁን አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።

🌟የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ውጤት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች
(Factors influencing slump test result)

1- ለኮንክሪቱ  የተጠቀምናቸው ግብአቶች ባህርይ።

⏺ለምሳሌ:  ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ መጠን እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣ እርጥበት ፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም

2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠንና አይነት መስተጋብር.

3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም።

4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ

5- የኮንክሪቱ ሙቀት መጠን /temperature/

6- የተጠቀምነው የውሃ መጠን

7- ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ

🌟Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች ምን ምን ናቸው?

⏺ጉርድ የኮን ቅርፅ/Truncated cone/ :-ይህ ቅርፅ ማውጫ 30 cm
ቁመት የታችኛው ዲያሜትር 20 cm
የላይኛው ዲያሜትር 10cm ዲያሜትር ነው

⏺Plate/መደብ/ :- ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው
መጠቅጠቂያ ብረት/Compaction rod/

💫የስራ ቅደም ተከተሉ እንዴት ነው?

1ኛ. መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ
ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት።

2ኛ. ቅርፅ ማውጫውን (mold ) ትልቅ ዲያሜትር ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን/plate/ ላይ ማስቀመጥ።

3ኛ. የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer በኮንክሪት መሙላት።

4ኛ. እያንዳንዱን የኮንክሪት ሌየር 25 ግዜ በመጠቅጠቂያው ብረት መምታት የአጠቃጠቅ ጉልበታቱ እኩል መሆን አለበት።

5ኛ. ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ስፋት ባለው ጫፍ ላይ ያለ ትርፍ ኮንክሪትን በቅርፅ ማስወገድና መለሰን።

6ኛ. በርጋታ  ቅርፅ ማውጫውን
(mold) ወደላይ በመሳብ ከኮንክሪቱ ማለያየት።

7ኛ. ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold) ያለውን የርዝመት ልዩነት መለካት።

🌟ማስታወሻ

⏺ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን መከወን አለብን።

⏺ከቴስት በኋላ የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች
/Results to be/

🚧True Slump

🏷ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ትክክለኛው ልኬት ነው።

⏹ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ ቁመት ከቅርፅ ማውጫው አንፃር የምናገኘው ልዩነት ነው።

🚧Zero Slump

🏷ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃና
ሲሚንቶ
/water-cement ratio/ያለው መሆኑን ያሳያል።

🚧Collapsed Slump:

🏷ይህ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ
የኮንክሪቱን የውሃና ሲሚንቶ/water-cement ratio/ ምጣኔ ትልቅ መሆን ያሳያል እንዲሁም የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ እና High workability mix መሆኑን ያሳየናል።

🚧Shear Slump

🏷ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤቱ ሙሉ
እንዳልሆነ ይነግረናል።


https://t.me/ethioengineers1
👍31❤8👏1
የኮንስትራክሽን_ሥራዎች_ውል_አዘገጃጀት፣_ለሕግ_ባለሞያዎችና_ለምሕንድስና_ባለሞያዎች_በአማርኛ_የቀረበ፤.pdf
271.8 KB
💥ውል ለብዙ ስራዎች መቀላጠፍ መሰረት የሆነና የተለያዩ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ችግሩን የመፍቻ ዘዴ ነው። የአገራችን ህዝብ ስለውል ያለው ግንዛቤ የዳበረ ነው ለማለት የሚከብድ ቢሆን የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ባለሙያዎችን በማማከር ውል አዘጋጅተው ወደ ስራ የሚገቡበት ሁኔታ አለ። የሰው ልጅ በቃሉ ይታሰራል ነውና ውል ለሚያስፈልገው ጉዳይ ሁሉ ህጉን በተከተለ መልኩ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱ የተሻለ ነው።

💫የዉል ይዘቱም የተለያየ ሲሆን የኮንስትራክሽን ሰራ ውል ስናዘጋጅ መከተል ያለብንን መንገድ ይህ የተዘጋጀው ፅሁፍ አብራርቶ ያስቀምጣል።

https://t.me/ethioengineers1
👍21❤2
💥የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሌሎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ዛሬ  የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:52 ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ህንጻ ጀርባ ለህንጻ ግንባታ የመሰረት ብረት እያሰሩ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ ሶስት ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋስት መረጃ ባደረሱት መረጃ አደጋዉ የደረሰዉ  ሰራተኞቹ  ለመሰረት በተቆፈረዉ አስር  ሜትር ጥልቀት ባለው ቦታ በስራ ላይ እንዳሉ ድንጋይ ተንዶባቸዉ ነዉ።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች  ህይወቱ ያለፈዉን ሰዉ አስከሬን የአወጡ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸዉ  ተጎጂዎች  ህክምና አየተደረገላቸዉ ይገኛል።

ዛሬ አደጋ የደረሰበት ቦታ አሁንም  ለአደጋ የተጋለጠ በመሆኑ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም የሚመለከታቸዉ አካላት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስበዋል።

በአዲስ አበባ በግንባታ የስራ ላይ አደጋ በ20 ቀናት ዉስጥ  የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ  ስድስት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን አቶ ንጋቱ ለፋስት መረጃ ተናግሯል።


https://t.me/ethioengineers1
👍7🤔7❤1
💥ህግ ምን ይላል?

💫በህንፃ ለሚደርስ ጉዳት የሚኖር ኃላፍነት
❗️

https://t.me/ethioengineers1
👍7🔥2
💥Hydraulics and water supply Lecture

🚧ለዛሬ ደሞ የ ላየኛው የምድር ውሃ (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች ኣዘጋጅተናል

🌟⓵ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት እንዳይገቡ ያግዳል ።

🌟⓶ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና
የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ።
⏺ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3) አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
⏺እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል

🌟⓷ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት (coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው።
ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል።

🌟⓸መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ።

⏺ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው።
በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብዱ እጅግ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን በፍሎኩሌሽን ወቅት ስንጠቀማቸው የነበሩ ኬሚካሎችን በመጠቀም እንዲዘቅጡ ይደረጋል።

🌟⓹ ማጥራት (filtration)፦በዚህ የማጥራት ደረጃ ከማዝቀጥ ደረጃ ያለፉ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን እጅግ ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት  አካል (medium ) እንዲያልፍ በማድረግ የድፍረስነቱን መጠን እጅግ መቀነስ ነው።

🌟⓺ማከም (Disinfection) ፦ ከላይ በተጠቀሱ የማጣሪያ ሂደቶች የተጣራው ውሃ (በዋነኛነት ከተለያዩ ህይወት ከሌላቸው ጥቃቅን ቆሻሻዎች) ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት
ከመድረሱ በፊት በዚህ ሂደት (ዲስኢንፌክሽን) ማለፍ አለበት ምክንያቱም ውሃው ለአገልግሎት የሚቀርበው ከተለያዩ በአይን ከማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።

⏺ዲስኢንፌክሽን ውሃውን በማፍላት ፣ ሚካኒካል በሆነ መልኩ ፣ ለጨረር በማጋለጥ (radiation ) እንደሁም በኬሚካል ሊከናወን ይችላል።

☄በሃገራችን በዋነኛነት ሃሎጅኖችን (ብሮሚን ክሎሪን እና አይኦዲን ) በመጠቀም ኬሚካል በመጠቀም ውሃን እናክማለን።

➡ከዚህ ሁሉ የማጣራት ሂደት በኋላ የተጣራው ውሃ ይጠራቀምና
ለተጠቃሚዎች ይዳረሳል።

▶ስለ surface waterን የማጣራት ሂደቶች ጥቂት የሆነ ገለፃን እንዳደረግንላችሁ ተስፋ
እናደርጋለን ።

🏷ርእሱ ሰፊ እንደመሆኑ ዳግመኛ በጥልቀት ለመዳሰስ ቃል እንገባለን


https://t.me/ethioengineers1
👍27❤1💯1
🌟Online Class (With Certificate)

1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software

🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken

🫵For Registration - 0948552002  Or @AbelMuluken

🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution

🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA
👍3👏1
💥በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ከተሰማሩ ተቋማት የመረጃ ማሰባሰብያ መጠይቅ

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ‘የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዳታ አስተዳደር ሥርዓት (Ethiopian Construction Data Management System (ECDMS))’ ለማዘጋጀት ያለመ ፕሮጀክት እያሰራ ይገኛል።

የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ የኮንስትራክሽን
ኢንደስትሪ መረጃዎችን በፌዴራል፣ በክልል፣ በከተማ/ወረዳ እንዲሁም ከግል ድርጅቶች በመሰብሰብ፣ በማደራጀት እና በመተንተን እንዲሁም በተቀናጀ ድረ-ገጽ ላይ የተመሰረተ አሰራርን በመጠቀም ለተጠቃሚዎች ለማዳረስ ያለመ ነው። የፕሮጀክቱ የመጨረሻ ውጤት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን አፈፃፀም እና ተወዳዳሪነት ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል።

ለዚህም የሚኒስቴር መ/ቤቱ (MUI) ፕሮጀክቱን ክአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ አርክቴክቸር፣ ሕንጻ ግንባታ እና
ከተማ ኢንስቲትዩት (EiABC – AAU) የፕሮጀክት ጥናትና የምክር አገልግሎት ስምምነት ፈጽሟል።

EiABC - AAU ከመንደር ኢንፎርሜሽን አርኪተክቸር ሶፍትዌር ዲዛይን (MinArc)፣ አልሚው ድርጅት ጋር በመተባበር ጥናቱን በማካሄድ እና
የመረጃ ሥርዓቱን በመንደፍ ላይ ናቸው።

ይህ መጠይቅ የተዘጋጀው በEiABC - AAU የፕሮጀክቱ ጥናትና ዲዛይን ቡድን ሲሆን አላማውም ከኮንስትራክሽን 
ኢንዱስትሪ ተዋናዮች መረጃ ለመሰብሰብ ነው፡፡

ለሁሉም ጥያቄዎች ምላሽ እንድትሰጡ እና በተቋማችሁ ከግንባታ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን
(ማለትም ከህንፃዎች፣ መሠረተ ልማት፣ የግንባታ እቃዎች እና የማሽነሪ ግብአቶች፣ የግንባታ ባለሙያዎች ጋር
የተያያዙ መረጃዎችን) ለመሰብሰብ የምትጠቀሙባቸውን ቅጾች፣ ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (KPIs) እና ሰነዶች (ሶፍት ኮፒ እና/ወይም ሃርድ ኮፒ) እንድታቀርቡ በአክብሮት ለመጠየቅ ነው።

የምታቀርቧቸው የመረጃ ቅጾች እና የግንባታ ተዛማጅ መረጃዎች
ለዳታቤዝ ሲስተም ልማት ፕሮጀክት ጠቃሚ ግብአቶች ይሆናሉ።

ለምታደርጉልን ትብብር በቅድሚያ እናመሰግናለን።
የካቲት 2016

ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካለዎት እና ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ የጥናት ቡድኑን የወከለውን ባለሙያ ማግኘት ይችላሉ።

(አቶ ባህሩ ሰለሞን
ስልክ
09 16 05 50 16)

https://forms.gle/tPkNzKmQ7JDqDUQZ8
👍17🙏1
🦺ውድ የኢትዮ ኮንስትራክሽን ቤተሰቦቻችን በዚህ ቻናል ላይ ፖስት ምናረጋቸውን በ ድምፅ ቨዲዮ ለማግኘት ከታች ባለው ሊንክ የቲክቶክ ገጻችንን ይቀላቀሉ እናመሰግናለን❗️

https://www.tiktok.com/@ethiocons
❤8👍1
💥የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)

⚡️የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡

⚡️በተለይም ከላይ ስለ ሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡

⚡️በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለ ቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡

⚡️የጥገና እና ብልሽት አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡

⚡️በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡

⚡️ለምሳሌ፡- በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ይነበባል፡-“ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለ ሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡”

⚡️በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ 3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቅጽ 18 በሰ/መ/ቁ 101378  በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ናሰው ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር መካከል በነበረው ክርክር የጥገና ዋስትና (maintenance bond) ሊኖር እንደሚችል ካተተ በኋላ አንድ ሥራ ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የሌለው መሆኑን እሰገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡


https://t.me/ethioengineers1
👍13👏2
          🌟Online Class (With Certificate)

1. ETABS Price = 2000birr
2. Ms Project Price = 2500birr
3. Quantity Survey Price = 2000birr
4. Civil 3D Price =2500birr
5. Etabs With Safe Price = 3000birr
6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
7. AUTOCAD Price = 2000birr
8. ProtaStructure Software

🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken

🫵For Registration - 0948552002  Or @AbelMuluken

🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution

🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
👍11
💥በሰው መሬት ላይ ለተሰራ ቤት ሕጉ ምን ይላል??

አንድ ሰው የራሱ ይዞታ ባልሆነ መሬት ላይ  ወይም በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት ከሰራ ከህግ አንፃር እንዴት ይታያል ለሚለው የፍትሀ ብሔር ሕጉን ቁጥር 1170 ና 1179 እናያለን።

የአንድ የመሬት ይዞታ ባለቤት በይዞታው ላይ የመጠቀም መብቱ የራሱ ነው፡፡ ሌላ ሰው በዚያ መሬት ላይ ህንፃ ወይም ቤት ሊሰራ አይችልም ልስራ ካለም ባለይዞታውን በማስፈቀድ መስራት አለበት አለበለዚያ ባለይዞታው በመሬቴ ላይ ቤት መስራት አትችልም ብሎ  መቃወም ይችላል።

ነገር ግን መሬቴ ላይ ቤት መስራት አትችልም እየተባለና ባለይዞታው እየተቃወመ  በእምቢተኝነት በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሰራ ሰው በሰው መሬት ላይ በሰራው ቤቱ አንዳችም መብት የለውም። ባለይ ዞታው በመሬቱ ላይ  እየተቃወመው  ቤት የሰራው ሰው ሁለት አማራጭ የህገ መፍቴዎች አሉት

1. ለቤቱን መስሪያ ያወጣውን ወጪ ሳይመልስለት ቤቱን ለቆ እንዲሄድ ማድረግ ይችላል።

2. ቤቱን የሰራው ሰው በራሡ ወጪ ቤቱን አፍርሶ እንዲሄድ ለመፍቀድ ይችላል፡፡ ባለመሬቱ በይዞታው ላይ ባለመኖሩ ወይም በሌላ ምክንያት በመሬቱ ላይ ቤት የሚሰራውን ሰው በወቅቱ መቃወም ባይችልም ቤቱ መሰራቱን እንዳወቀ ቤቱን ማስለቀቅ ወይም ማስፈረስ ይችላል።

ስለዚህ የራስ ያልሆነ ይዞታ ላይ ቤት መስራት አይቻልም። ይቻላልም ከተባለ ባለመሬቱ ፍቃደኝነቱን መግለፅ አለበት።

በመሬቱ ላይ ሌላ ሰው ቤት ቢሰራ እንደማይቃወም በግልፅ ወይም በዝምታ መፍቀድ ይችላል።

በግልፅ ወይም በዝምታ በመፍቀድ (ተቃውሞ ሳያቀርብ) በመሬቱ ላይ ሌላ ሰው ቤት ሲሰራ ያልተቃወመ ወይም የተስማማ ባለይዞታ እንደ ፌደራል ሰበር.በመዝገብ.ቁጥር 30101.ቅፅ 6 እና በመዝገብ.ቁጥር.105125.ቅፅ 20 በተወሰነው ውሳኔ መሰረት  ቤቱን የሰራው ሰው ባለቤት ይሆናል የመሬቱ ባለይዞታም በእንዲ አይነት ሁኔታ ቤቱን ለሰራው ሰው የቤቱን ግምት ከፍዬ ላስለቅቅ ማለት አይችልም።

የፍ/ህ/ቁ.1179ን አስመልክቶ ሰበር በቅፅ 25 የመ/ቁ. 189608 የሰጠው ትርጉም
***
በፍ/ህ/ቁ. 1179 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ተፈፃሚነት  የሚኖረዉ በባለይዞታዉ እና ይዞታዉን ይዞ ቤት በሰራ ሰዉ መካከል የታወቀ ግንኙነት በሌለበት ሁኔታ ብቻ በመሆኑ የባድ ቦታ ሽያጭ ዉል መፍረሰን ተከትሎ በቦታዉ ላይ የተሰራ ቤት ህጋዊ ዉጤትን አስመልክቶ ለጉዳዩ ተፈፃሚነት ያለዉ በፍ/ህ/ቁ. 1818 ነዉ።

Via ሳሙኤል ግርማ
 
#ConstructionLaw

https://t.me/ethioengineers1
👍19