🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
12.2K subscribers
2.91K photos
301 videos
70 files
8.07K links
ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።

✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼
👇🏾👇🏾👇🏾
@hamdquante

አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል
👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿
Download Telegram
✍
አላህ ጥሎ አይጥለኝም አይባልም፤

አላህ አይጥለኝም ነው የሚባለው።




https://t.me/hamdquante
👍56💯3❤1
.

🇮🇷 ኢራን ውስጥ ኣያቱላህ
🇱🇧 ሉብናን ውስጥ ሂዝቡላህ
🇾🇪 የመን ውስጥ አንሷሩላህ
ብለው ይንቀሳቀሳሉ።
የሚገርመው;……  አንዳቸውም አላህን አያውቁትም!!




https://t.me/hamdquante
❤19👍7💯4
✍
መድሃኒታችን የጠፋው ለዚህ ይሁን???

  ባላገር ነው። ተኩላ ይነክሰውና ወደ ሩቅያ ቤት ይሄዳል። ሩቂያ አድራጊው;
  "ምንድን ነው የነከሰህ?"  ሲል ጠየቀው
ሰውየው ተኩላ ለማለት አፍሮ "ውሻ" አለው።

ልክ ሩቂያ ማድረግ ሲጀምር………
  "በዝያው ቲንሽ ቲንሽ የተኩላ ቀላቅልበት" አለው።


  ሁላችንም እኮ ችግራችን፣ በሽታችን፣ ድክመታችን ጠንቅቀን እናውቀዋለን። ሆኖም ግን………
  ፈርተን ወይም አፍረን እንደብቀዋለን።





https://t.me/hamdquante
👍30❤6💯4👌3✍1
🚫
ተጠንቀቅ‼️

  አላህ ከወፈቀህ መድረክ ላይ ከሰዎች ፊት ቆመህ ካልሆነም በሌላ በየትኛውም መንገድ ዕውቀትህና ዐቅምህን ተጠቅመህ ወደ አላህ መንገድ ትጣራ ይሆናል።

   ግዴታህን ለመወጣትና ወደ ጌታህ ለመቅረብ ነይተህ በምታደርገው ዳዕዋ ብዙ ሰዎች ምን አልባትም አንድም ሰው ላይቀበልህ ይችላል። የሚጠበቅብህን ካደረግክ ይህ አያስወቅስህም፤ ከአንተ የተሻሉ ነብያቶች ከአንተ የበለጠ ትግል አድርገው እንኳ ቲንሽ ሰው እንጂ ያልተቀበላቸው አሉ፤ አንድም ሰው ያልተቀበላቸውም አሉ።

ይህ ኪሳራ አይባልም።

ትልቁ ኪሳራ እና ውርደት ማለት……………
    ወደ አላህ የመጣራት መድረክ ላይ ቆመህ በአንተ ብልሹ ስነምግባር መሠረት ወይም በአንተ ስግብግብነት ምክንያት ወደ ዲን ተጠግተው የነበሩ ሰዎች የምታሸሽ ከሆነ ነው።

🚫ተጠንቀቅ‼️




https://t.me/hamdquante
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👌9❤8👍5✍1
🕋
     ምንዳውና ቱሩፋቱ እንዳለ ሆኖ………


  አንዴ እዚህ ጋ ተቀምጠህ ለምታገኘው ለህሊና እድሳት ብቻ ምንም ያህል ብትከፍል የከሰርክ አትሆንም ነበር!!





https://t.me/hamdquante
❤17👍9
✍
ምንም ነገር ላይ ከዚህ………… እስከዚህ የሚል ገደብ ልታደርግ ትችላለህ: 🤲ዱዐ ላይ ግን በጭራሽ❌


  ነብዩ ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላት ወሰላም: ኢስማዒልና ሀጀርን: ምንም ዓይነት ዛፍ ቅጠል በሌለበት ምድረ_በዳ በረሀ ላይ ካስቀመጣቸው በኋላ ያደረገውን 🤲ዱዐ ተመልከት;

  {… وَارْزُقْهُم مِّنَ الثَّمَرَاتِ…}
  {…ከፍራፍሬዎችም መግባቸው።}

   አላህ የወዳጁን ዱዐ ተቀብሎ በአለትና በተራራ በተከበበችው መካ፧ በየትኛውም አምራች ሀገር የማይገኙ የፍራፍሬ ዓይነቶች እስከዛሬ ድረስ ተሰባስበው ይገኛሉ።


   "እንዴት አርጎ?? በምን መልኩ??" የሚለው ሳያስጨንቅህ: አላህ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንደሚችልና ዱዐህን እንደሚቀበልህ አርግጠኛ ሆነህ ጠይቀው። ከእሱ የሚጠበቀው  {ሁን} ማለቱ ብቻ ነው።





https://t.me/hamdquante
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤19👍6
   💥የጥቅምት ተዘግቶ💥
    
🔄 የታኅሳስ ተከፍቷል!!🔄
 
       🔝🔝🔝🔝🔝

   ለ🥰🥰ኛ ጊዜ በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ምዝገባ ሲደረግ የቆየው የጥቅምት ወር የዑምራ ፓኬጅ ምዝገባው ተጠናቆ።

ለ 🥰🥰ተኛው ዙር የተዘጋጀው ልዩ የዑምራ ፓኬጅ የምዝገባ ደብተሩ ተከፍቷል!!



   የጥቅምት 🥰🥰 ተጓዦቻችን ሁሉም ዓመታዊ ቪዛቸውና የደርሶ መልስ ትኬታቸውን ተቀብለው የበረራ ቀናቸው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።


እናንተም…………
    በዚህኛው አስባችሁ ላልተሳካላችሁም ይሁን ለቀጣይ ለነየታችሁ በአጠቃላይ
   ከታኅሳስ
🥰እስከ 🥰🥰 

December
1️⃣0️⃣to 2️⃣0️⃣

በሚቆየው ልዩ የዑምራ ፓኬጅ መሳትፍ እንድትችሉ ከአሁኑ መመዝገብ ትችላላችሁ።


ለሁለቱም ሐረሞች ቅርብ የሆኑ ምቹና ዘመናዊ ሆቴሎች በማዘጋጀት በቤተሰባዊ እንክብካቤ ልንኻድማችሁ ተዘጋጅተናል።


የሁል ጊዜ ምርጡና ተመራጭ ትራቭል
=>የለምለም የጉዞ ወኪል!!

🎁ፓኬጁ የሚያካትተው……
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

💳ዓመታዊ የዑምራ ቪዛ፤
✈ደርሶ መልስ የአየር ትኬት፤
🎓በሁለቱም ሐረሞች የሆቴል ክፍያ፤
🎓ዘመናዊ የባስ ትራንስፖርት፤
🎓በሁለቱም ሐረሞች የተለያዩ ቦታዎች ዝያራ፤



💯የለምለም ትራቭል የጉዞዎ ታማኝ አጋር

➡️ 0911674580
➡️ 0922448888
➡️ 0911904297

📍አድራሻ ቤተል ሚና ሞል 2ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን

🌟 https://t.me/Yelemlem_travel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤6🤝5👌3
🇺🇸
   የአሜሪካ ወታደር………
ቁሞ የሚሄድበት የጀርባ አጥንት ካለው በቂው ነው: የሚያስብበት አእምሮ አያስፈልገውም።

      /አልበርት አንስቴይን/



  የአሜሪካዊያኖች ድድብናና ጭካኔ የገለፀባት ድንቅ ዐረፍተነገር ናት።






https://t.me/hamdquante
👍19❤3👌2
✍
    እቺ ዱንያ………

💫ዩሱፍﷺ ተሽጦባታል፤
💫ኑኅﷺ ተስተባብሎባታል፤
💫ሙሳ
ﷺ በደጋሚነት ተወርፎባታል፤
💫ሙሐመድ
ﷺ በድንጋይ ተወግሮባታል፤
💫ኢብራሂም
ﷺ ወደ እሳት ተወርውሮባታል፤
    ከዚህ ሁሉ በኋላ ለአንተ እንዴት ምቹ ልትሆን ትችላለች ከቶ???


የዱንያ ሐቂቃዋ ማለት፦
   እንደ አንድ ሰው ነው, ከዛፍ ጥላ ስር ተኛ: በህልሙ የሚወደው ነገር አየ: ወድያው ነቃ: ቦታውን ትቶ ሄደ።






https://t.me/hamdquante
👍13❤3
✍
ሴት ልጅ ደብቃ ልቲዘው የምትችለው ብቸኛው ሚስጥር;
ዕድሜዋ ነው አሉ።





https://t.me/hamdquante
👍8❤7🤝3
✍
    በየትኛውም ዓይነት መንሐጅ፤
   በየትኛውም የዕውቀት ደረጃ፤
በየትኛውም ሀገር ላይ ያለ ሙስሊም ሁሉ…………

   ከላይ የተቀመጡ ቪዲዮዎች ሲመለከት ልቡ በአንድ ቅፅበት ወደ አንዲት ቦታ ይመታል!!


                  🤲اللهم عمرة🤲
🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋




https://t.me/hamdquante
👍14❤3👌2
📖{لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي كَبَدٍ}
{ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ሆኖ ፈጠርነው፡፡}


ከከፊል ሰለፎች ተይዞ በተላለፈው፦
   አላህ ከፈጠራቸው ፍጥረታቶች ሁሉ እንደ የሰው ልጅ መከራ የሚበዛበት ፉጡር የለም፤ ከመሆኑም ጋ ከፍጥረታት ሁሉ ደካማው እሱ ነው!!
          /ኢማሙ ቁርጡብይ/





https://t.me/hamdquante
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👌11👍5❤3
✍
ዐላማህ እንዳይሳካ ከፈለክ፦
👇
👉ለምትገናኛቸው ሁሉ ስለ ዕቅድህ ንገራቸው¡¡





https://t.me/hamdquante
👌30💯9👍4❤3✍1
✍
መጥቶ ስለ አንዱ ክፋት ሲነግርህ……
🤲አላህ ለእሱም ለእኛም ያስተካክለን🤲 በለው። ከዚህ ሌላ አትጨምር።



https://t.me/hamdquante
👍20❤4👌3
✍
   ውበቱ የሚጀምረው ከስሙ ነው!!

🕋ضيوف الرحمن  የአል_ረሕማን እንግዶች

ሲጀመር………
   በቋንቋም ይሁን በየትኛውም ማህበረሰብ ተለምዶ "እንግዳ" የሚለው ቃል የተከበረና የተዋበ ማዕረግ ያለው መጠሪያ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አንድ እንግዳ በእንግድነቱ የተከበረ ከመሆኑም ጋ……… እንግድነቱ የተቀበለው ወይም ለእንግድነት የጋበዘው አካል ባለው ደረጃ ልክ የእንግዳው ክብርና ደረጃ ከፍ ይላል። ለዚህም ነው ሰዎች የሆነን እንግዳ መጥራት ወይም መጋበዝ ሲፈልጉ: ቀጥታ ራሳቸው ከመጥራት ይልቅ "እከሌ ጠርቶሃል" ብለው የሚያስልኩት። መልእክተኛውም ቢሆን "ዐለቃዬ ጋብዞሃል" ብሎ ያስተላልፋል እንጂ "ጋብዤሃለሁ" አይልም።

ምክንያቱም፦
    ተጋባዡ እንግዳ በሚጋብዘው አካል ደረጃ ልክ ደረጃውን ክብሩን ስለሚወሰን ነው።

ለምሳሌ………
  የሀገሪቷ የግብርና ሚኒስቴር ጥሪ አድርጎላቸው የመጡ እንግዶችና የሀገሪቷ ፕሬዝዳንት ጥሪ አድርገውላቸው የመጡ እንግዶች የሚያገኙት ክብር ተመሳሳይ አይደለም። ተጋባዡ እንግዳ ተመሳሳይ ሰው ሆኖ እንኳ የሆነ ሰዓት የገቢዎች ሚኒስቴር ሌላ ጊዜ ደግሞ የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስቴር እንግዳ አድርገው ቢያቀርቡት የሚያገኘው ክብር ተመሳሳይ አይደለም። ተጋባዡ አንድ ሰው ሆኖም የሚጋብዙት አካሎች ስለተለያዩ በእነርሱ መለያየት ምክንያት እሱ የሚያገኘው ክብር ይለያያል።
   የሀገራችን ልዑካኖች አሜሪካ ጠርታቸው ቢሄዱና ኬንያ ጠርታቸው ቢሄዱ የሚያገኙት ክብር እኩል አይደለም።

አሁን መልዕክቱ የተገለጠላችሁ ይመስለኛል!!

  የምድር የሰማይ ፈጣሪና አስተናባሪ፤ የሁሉም መመኪያና መጠጊያ፤ የትኛውም ነገር ሁን በማለቱ ብቻ የሚሆንለት ልዕለ ሀያሉ አላህ እንግዳ አድርጎ ሲጠራህ፧ ክብርህ ምንኛ የተለቀ ሊሆን ነው??!!


🕋ضيوف الرحمن  የአል_ረሕማን እንግዶች
 
ሲባል ውበቱ የሚጎላው ለዚህ ነው። አላህ ጠርቶህ፣ አላህ መርጦህ፣ አላህ ጋብዞህ ወደቤቱ ሲጠራህና ጥሪውን ተቀብለህ ስትገኝ………… ከዚህ የበለጠ ክብር የለም!!



🤲አላህ ደግሞ ደጋግሞ ይወፍቀን🤲


https://t.me/hamdquante
❤22👍10💯1
✍️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍8❤1
☝️
የአላህ አላህነቱን ተመልከት!!

  አላህ በተከበረው ቃሉ ስለ ደጋግ ባሮቹ፣ ስለ ወዳጆቹ፣ ስለ ምርጦቹ ሲናገር አንድም ቦታ ላይ "ከስህተት የተጠበቁ ፍጹም ናቸው" ብሎ አይገልፃቸውም። {አላህ ባዘዛቸው ነገር አያምፁትም፤ የታዘዙትን ይሰራሉ} ብሎ ፍጹማዊነት የሰጣቸው ለመላኢካዎች ብቻ ነው። ከሰው ልጆች ሆነው ደጋግ ስለሆኑ ባሮቹ ሲናገር ግን {ከስህተታቸው ምህረት የሚጠይቁ፤ በስህተታቸው ላይ የማይዘወትሩ} እያለ በዚህ ተመሳሳይ ገለፃ ይገልፃቸዋል።

አላህ………
   ከአንተ ፍጹማዊነትን አይሻም፤ ልትሆን ስለማትችል።

አላህ………
   ከአንተ የሚፈልገው ከወንጀልህ ተመልሰህ ምህረት እንድትጠይቀው ነው!!


ተመልከት……………
    እያንዳንዱ ሀገር ላይ ተደንግገው የተቀመጡ ህገመንግስታዊ ስርዓቶች ብትመለከት፧ የሆነ ወንጀል ይጠቀስና የዝያ ወንጀል ፈፃሚ ቅጣቱ ቀጥሎ ይጠቀሳል። ሁሌም አንድ ወንጀለኛ ከተያዘ ቀጥሎ የሚጠብቀው [ህጋዊም ይሁን ህገ_ወጥ: ፍትሓዊም ይሁን ኢ_ፍትሐዊ] ቅጣት ነው።

   እያንዳንዱ ቁርኣን ውስጥ እና ሐዲስ ውስጥ የተጠቀሱ የወንጀል ዓይነቶች ብታይ ብትመለከት ግን; ከትልቁ ኩፍርና ሽርክ ጀምሮ ለእያንዳንዱ አላህ ለሚታመፅበት ወንጀል የምህረት በር ተከፍቶለታል። የትኛውንም አላህን የሚያስቆጣ ወንጀል የፈፀመ አካል ወደ አላህ ከተመለሰና ምህረት ከጠየቀ አላህ ይምረዋል።

ቀጣዩን አንቀፅ ተመልከት፦
📖{قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ}
  {እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን ሁሉ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና በላቸው፡፡}
    [አል_ዙምር:⁵³]

   አላህ በዚህ በተከበረ አንቀጽ ላይ እየተናገረ ያለው ስለ ሰጋጆች ወይም ስለ ጿሚዎች ወይም ስለ ደጋጎች አይደለም። አንድ… ሁለት… ሦሥት… ምናምን ሳይሆን በወንጀል ተጨማልቀው ወንጀላቸው ከመተለቁና ከመብዛቱ "ነፍሳቸው ላይ ድንበር እስከማለፍ" ስላደረሳቸው አካሎች ነው።

ሆኖም…………
   "እናንተ ሙጅሪሞች፣ አመፀኞች፣ ጥጋበኞች" ወይም በመሳሰሉ ቃላቶች ሳይሆን;
   የትኛውም ሙእሚን ቢጠራበት ሊያስደስተውና ሊኮራበት በሚችል ውብ ጥሪ {ባሮቼ ሆይ!!} እያለ ይጠራቸዋል።
 
ምክንያቱም………
  እሱ አላህ ነው!! እሱ አዛኝ ነው!!


ሌላው የሚገርመው…………
   አላህ ሲቀጣህ በፍትሕ ነው፤ ሲምርህ ደግሞ በችሮታው ነው!!

   አንድ ባሪያ ከሰራው ወንጀል ምህረት ሳይጠይቅ አላህን ቢገናኝና አላህም በዚህ ወንጀሉ ሊቀጣው ቢፈልግ;
  የሚሰጠው ቅጣት ከወንጀሉ ተመሳሳይና ተመጣጣኝ የሆነ ነው!!

📖{وَالَّذِينَ كَسَبُوا السَّيِّئَاتِ جَزَاءُ سَيِّئَةٍ بِمِثْلِهَا}
   {ለእነዚያም ኃጢአቶችን ለሠሩት የኃጢኣቲቱ ቅጣት በብጤዋ አለችላቸው፡፡}
    [ዩኑስ:²⁷]


  ከሰራው ስህተት ወደ አላህ ተመልሶ፤ አላህን የሚያስወደድ ስራ ሰርቶ አላህን ለተገናኘ ባሪያ ግን አላህ ሲመነዳው በስራው እኩኩል ሳይሆን አጥፍ ድርብ አርጎ በብዙ አብዝቶና አሳምሮ ነው።

📖{مَّثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ كَمَثَلِ حَبَّةٍ أَنبَتَتْ سَبْعَ سَنَابِلَ فِي كُلِّ سُنبُلَةٍ مِّائَةُ حَبَّةٍ ۗ وَاللَّهُ يُضَاعِفُ لِمَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ}
  {የእነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ሰዎች (የልግስናው) ምሳሌ በየዘለላው ሁሉ መቶ ፍሬ ያለባቸውን ሰባት ዘለላዎች እንደ አበቀለች አንዲት ፍሬ ብጤ ነው፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው (ከዚህ በላይ) ያነባብራል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡}
     [አል_በቀራ:²⁶¹]
   አንዲት መልካም ስራ እስከ ሰባት መቶ ትባዛለች። አላህ ለፈለገው ከዚህም በላይ ይጨምርለታል።


ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ ሁለቱም በአንዲት አንቀጽ ይገልፃቸዋል፦
📖{مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ}
  {በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡}
   [አንዓም:¹⁶⁰]


እንዲሁም…………
   አንድ ባሪያ ለብዙ ጊዜያት ወንጀል ላይ የቆየ ሆኖ በስተመጨረሻም ወደ አላህ መመለስ ቢፈልግ… "አላህ ሊምርህ ከፈለክ፧ ወንጀል ላይ በቆየኸው ልክ ተውበት ላይ መቆየት አለብህ" አይባልም። ዐስር፣ ሀያ፣ ሀያ አምስት ዓመታት በወንጀል የኖረ ሰው ወደ አላህ ተመልሶ ምህረት እንዲደረግለት ከፈለግ፧ ያንን ሁሉ ዓመት የሰራው ወንጀል በአንዲት ቀን, በአንዲት ሰዓት, ሳይባል በአንዲት ቅፅበት አላህ ሁሉንም ይምረዋል።

ምክንያቱም፦
   አላህ ከአንተ የሚፈልገው ወደ እሱ የተዘነበለ ንፁህ ልብ ብቻ ነው!!


   አንተ ብቻ ወደ አላህ ተመለስ…… ሁሉም ነገር ወደ አንተ ይመለሳል!!





https://t.me/hamdquante
👍12❤10💯3👌2
⚫️
    አንተና ሞት⚫️


ልክ ስትሞት ከሁሉም ቀድሞ ከአንተ የሚወገደው ስምህ ነው።

  እንደ ሞትክ "ሬሳው የታለ" ማለት ይጀምራሉ።
  ሊሰግዱብህ ሲፈልጉም
"ሰላተል ጀናዛ (የሬሳ ሰላት) ይሰገድ" ይባባላሉ።

ሊቀብሩህ ሲፈልጉም
  "ሬሳው አቅርቡት ይባባላሉ።"
👇
👉ገና ከጅምሩ ካንተ ላይ ስምህ ይነሳል።


🚫ጎሳህ ብሄርህ ዘርህ አያታልልህ።

💫እቺ ዱንያ እንዴት የተዋረደችና የምንሄድባት ሀገር እንዴት የከበደች ናት⁉️


📍ተመልከት……
   ስትሞት ሦስት ዓይነት ሰዎች መርዶህ ይሰማሉ።

🥇ኛ,  በዘፈቀደ አንተን የሚያውቁህ ናቸው። መሞትህ ሲሰሙ
  "ውይ፣ ምስኪን ነበር፣ ሲያሳዝን" ይላሉ።

🥈ኛ, የሚቀርቡህ ጓደኛችህ ናቸው። በምትሞት ጊዜ;
ለቀናት ወይም ለሳምንታት ሊያዝኑ ይችላሉ;  ከዝያ በኋላ ወደ ጉዳያቸውና ወደ ሳቃቸው ይመለሳሉ።

🥉ኛ, ቤትህ ውስጥ የሚፈጠረው ጥልቅ የሆነ ሀዘን ነው።
  እነርሱም ለሳምንታትና ለወራት አንዳንዴም ለዓመታት ሊያዝኑ ይችላሉ።
ከዝያም ወደ ቀጣይ ሕይወታቸውና ወደ ሳቃቸው መመለሳቸው አይቀርም።



እንዲህ…… እንዲህ…… እያለ ዱንያ ላይ የነበረህ ታሪክህ ያከትማል።

💎የአኼራ ሕይወትህ ይጀምራል!!
🌙ቁንጅናህ
    🌙ንብረትህ
       🌙ጤንነትህ
          🌙ወላጆችህ
             🌙ልጆችህ
               🌙ባለቤትህ

      ሁሉ ካንተ ይወገዳሉ።


💎እውነተኛ የሆነው ሕይወት አሁን ትጀምራለህ።

💫ትጠየቃለህ………
    👉ጌታህ ማን ነው?
       👉ነብይህ ማን ነው?
         👉እምነትህ ምንድን ነው?


❓ምን ያህል ተዘጋጅተሃል❓



     https://t.me/hamdquante
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍24❤18👌2✍1