🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
12.2K subscribers
2.91K photos
301 videos
70 files
8.07K links
ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።

✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼
👇🏾👇🏾👇🏾
@hamdquante

አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል
👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿
Download Telegram
✍
ኩራተኛ ምሳሌው………

የተራራ ጫፍ ላይ እንደቆመ ሰው ነው;
ሁሉም ሰዎች ቲንሽ መስለው ይታዩታል: እሱም ለሁሉም ሰዎች ቲንሽ ሆኖ ይታያቸዋል!!





https://t.me/hamdquante
👍13❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌤
አዲስ ንጋት...……🗣️


ከአላህ ጋ የሚደረግ ግንኙነት የሚታደስበት……
ልቦች ጌታቸው ላይ የነበራቸው ተስፋ የሚሞሉበት…


የዕለቱ ትልቁ ስኬት ማለት;
🔄ቀንህን ለጌታህ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ስትጀምረው ነው!!

🔄የዕለቱ የመጀመሪያ ጉዞህ ወደ አላህ ቤት የምታደርገው ጉዞ ሲሆን ነው!!

🔄የዕለቱ የመጀመሪያው ንግግርህ ከጌታህ ጋ የምታደርገው ንግግር ሲሆን ነው!!


   ለልቡ ብርኃን፧ ለቀልቡ ሰኪና አጎናፅፎ, የሌሊትና የቀን መላኢካዎች በተጣዱበት, ውሎውን በሰላት የጀመረ ሰው ምንኛ የታደለ ነው??!!

        🤲አላህ ይወፍቀን🤲



https://t.me/hamdquante/11279
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💯15❤12
✍
አባት ለልጁ ያስተላለፈው ወስያ ነው………

➡️በሀሳብ የተወጠረ ሰው ቆራጥ ቢሆን እንኳ አታማክረው፤

➡️የተራበ ሰው ምንም ያህል ብልህ ቢሆን እንኳ አታማክረው፤

➡️ሀዘንተኛ ሰው ምንም ያህል ዐዋቂ ቢሆንም አታማክረው፤

➡️ስጋት ላይ ያለ ሰው ምንም ያህል ፈጣን ቢሆንም አታማክረው።

ጭንቀት፣ ረሀብ፣ ሀዘን እና ስጋት ከምንም በላይ አእምሮ የሚሸፍኑ ጉዳዮች ናቸው። የተሸፈነ አእምሮ መፍትሔ የሚሆን ሀሳብ ማመንጨት አይችልም!!




https://t.me/hamdquante/11280
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤17👍10
✍
በሰላሙ ጊዜ የምታደርገው ዒባዳ: በመከራው ጊዜ የመዳኛ ዋስትናህ ነው!!

  ከመልካም ስራ ምንም ሳታሳንስ ዛሬ መስራት የምትችለውን ሁሉ ዛሬውኑ ስራ።

📖{فَلَوْلَا أَنَّهُ كَانَ مِنَ الْمُسَبِّحِينَ}
   {እርሱ ለጌታው ከሚያጠሩት ባይሆን ኖሮ፤}
{لَلَبِثَ فِي بَطْنِهِ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ}
  {እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር፡፡}




https://t.me/hamdquante/11281
👍12❤8
🕋
አላህ የሚጠራው ግን እንዴት ነው??…………

   ብዙ ጊዜ ስለ ዑምራ ሲወራ አንዲት የተለመደች አባባል አለች; "ዑምራ የምትሄደው ገንዘብ ስላለህ ሳይሆን: አላህ ሲጠራህ ነው" ።
  ይህ ምንም ክርክር የማያስነሳ ትክክለኛ አባባል ነው። ግን ግን: አላህ የሚጠራው እንዴት ነው???

   ለዚህና መሰል ጥያቄዎች ሁሉ ምላሽ የሚሆን አላህ በተከበረው ቃሉ ያስቀመጠው ትልቅ መርህ አለ፦

{وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا}
{እነዝያ በእኛ መንገድ ላይ ለሚታገሉት: መንገዳችን እንመራቸዋለን።}

   አንተ የራስህን ጥረት በማድረግ ትለፋለህ: ቀጣዩ አላህ ይመራሃል። ልብህና ጡንቻህ አዘጋጅተህ: ትጥቅህን ይዘህ ጂሀድ ስትወጣ: አላህ ሸሓዳ ይሰጥሃል። ጊዜህን ሰውተህ: ምቾትህ ቀንሰህ:: እንቅልፍህን ትተህ ለመሓፈዝ ለማጥናት ስትታገል: አላህ ዓሊም ያደርግሃል።

እንጂ……………
   አካውንትህ ላይ የፓኬጁ ሁለት ሦሥት እጥፍ ገንዘብ እያለ፤ ከሀገር እንዳትወጣ የተጣለብህ ማዕቀብ ሳይኖር፤ የየለምለም ስልክ ቁጥር ኮንታክት ሊስትህ ውስጥ እያለ;
   ወደ የለምለም ደውለህ ፓስፖርትህን ሳትልክ እንዲሁ ቁጭ ብለህ "አላህ ሲጠራኝ እሄዳለሁ" ብለህ የምትጠብቅ ከሆነማ……… ክፉ ነገር ተናግሬ ቅር እንዳይልህ እጠነቀቃለሁ።


  አሁኑኑ የፈጠነ ደውልና ስምህን አስመዝግብ!! ከዝያ ጥቅምት 26 ሲደርስ አላህ ይጠራህና ትሄዳለህ!!

➡️ 0911674580
➡️ 0911904297
➡️ 0922448888


https://t.me/Yelemlem_travel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤9👍3👌3
✍
  አስበኸዋል???…………
   ምንም ዓይነት የወጪ ብርም ይሁን መጠለያ ሳይኖርህ: መስጂድ ውስጥ ተጠግተህ እየኖርክ: ከጊዜያት በኋላ
  በርካታ የረሱልﷺ ሐዲስ ያስተላለፈ ሰው የሚል ማዕረግ ሲሰጥህ??!!

   መዲና ውስጥ በረሱልﷺ መስጂድ ጥግ ላይ "ሱፋ" በመባል የምትታወቅ ቦታ ነበረች። ምንም ዓይነት ማረፊያና የቀን ወጪ የሌላቸው ደሀ ሰሓባዎች ተጠልለው የሚያርፉባት ቦታ ናት። ረሱልﷺ ለእነዚህ ምስኪና ሰሓባዎች እጅግ በጣም ያዝኑላቸው፣ ይራሩላቸውም  ነበር። ሌሎች ሰሓቦችም ለእነዚህ እንዲንከባከቡ፣ እንዲመግቧቸውም ያነሳሷቸው ነበር።

   ከእነዚህ አሳዛኝና ምስኪን ጀመዐዎች ውስጥ የረሱልﷺ የዘወትር ባልደረባና የንግግራቸው ሰብሳቢ ታላቁ ሰሓብይ አቡ ሁረይራ ይገኝበታል።

  አቡ ሁረይራ ረሀብና ድካሙ በጣም ሲፀናበት አንዳንድ ጊዜ በሚንበሩና በዓኢሻ ጎጆ መሃል ራሱን ስቶ ወድቆ ይወራጭ ነበር። አንዳንድ ከሌላ ቦታ የመጡ የማያውቁት ሰዎች ሲያዩት ዕብድ መስሏቸው ይረግጡታል ሁላ: እሱ ላይ ግን ረሀብ እንጂ ዕብደት አልነበረበትም።

   ይህ ሁሉ እየሆነም ግን ኑሮ ከብዶኛል ብሎ ረሱልﷺ ከመጎዳኘትም ይሁን ሐዲሳቸው ከመሰብሰብ አንድም ቀን አልተቋረጠም።

  እነዚህ ጥቂት የነበሩ የችግር ጊዜዎች ካለፉ በኋላ ግን ይኸው ትውልድ አልፎ ትውልድ ሲተካ: አቡ ሑረይራ ሰብስቦ ያስተላለፈው የረሱልﷺ ሐዲስ የሙስሊሞች መመሪያ ሆኖ ቀጥሏል።ከዚህ የበለጠ ስኬት አለ ወይ???


ምንም እንኳ በዚህ ልክ ባይሆንም……………
   አንዳንድ ጊዜ አንተም ላይ ለሰዎች የማይታያቸው መከራ እየተፈራረቀ፤ ምቾት ፊቷን አዙራብህ፤ ዱንያ ኮረብታ ሊሆንብህ ይችላል። ለጥቂት ጊዜያት ታግሰህ ፀንተህ የምታስቀጥለው ተልዕኮ ምን አልባትም ሌሎች መድረስ ያልቻሉበት ስኬት የምታገኝበት መንገድ ሊሆን ይችላል።

  ይህም ቀን ያልፋልና  ታገስ!! ፅና!!



https://t.me/hamdquante
❤27💯8👍6👌4✍2
🗓
  ምዝገባው ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናቶች ብቻ ቀርተውታል!!

የዑምራ ፍላጎቶን ከእኛ ጋ እውን ያድርጉ!!
   የጥቅምቱ ልዩ የዑምራ ፓኬጅ የምዝገባ ደብተር ሊዘጋ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

  ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ የማይጠቅም ቁጭት ከመቆጨትና በመጨረሻ መጥቶ የትኬት ጭማሪ በመክፈል ከመንከራተት;
   አሁኑኑ በተቀሩ ቀናቶች ፈጥነው ይመዝገቡ!!


እርሶ ነይተው ወስነው ብቻ ይምጡ…………
   ለሁለቱም ሐረሞች ቅርብ በሆኑ ምቹና ዘመናዊ ሆቴሎች አርፈው፤ ሁለት ጁሙዐዎች በሁለቱ ሐረሞች ሰግደው፤ ከእንግልትና ከሙሓለፋ የጠራ ዑምራ በማስደረግ ሊኻድሟችሁ;
  የየለምለም ቤተሰቦች ተዘጋጅተው ይጠብቋችኋል!!


የጉዞ ቀን
ከጥቅምት🥰🥰 እስከ ህዳር 🥰


🥰ቀናት 🕌መዲና 🥰ቀናት 🕋መካ


ወስን!! ደውል!!! ወንድ ሁን!!!!

➡️ 0911674580
➡️ 0911904297
➡️ 0922448888


በአካል ለምትፈልጉን
  ቤተል ሚና_ሞል 2ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን!!




የለምለም ትራቭል የትውልዱ ተስፋ!!
https://t.me/Yelemlem_travel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤6🤝5
✍
    አሕነፍ ኢብኑ ቀይስ ይባላል………

የበኑ ተሚም ጎሳ መሪያቸው ነበር። በቅፅል ስሙ "የዐረቦች ታጋሽ" በሚል ይታወቃል። ከዕለታት በአንዱ ቀን አንድ ገጠሬ ይመጣና ለአሕነፍ ፊቱን 🫲በጥፊ ይቦርሽለታል።

  አሕነፍ በተረጋጋ ስሜት "ምነው? ችግር አለ እንዴ?" ሲል ጠየቀው;
ገጠሬው: "የሆኑ ሰዎች የተወሰነ ብር ሰብስበው ሰጥተውኝ የበኑ ተሚም መሪ በጥፊ እንድመታ አዘውኝ ነው።" አለው
አሕነፍ: "ተሸውደሃል! የበኑ ተሚም መሪያቸው እኔ ሳልሆን ሓሪስ ኢብኑ ቁዳማ ነው" አለው።
  [ሓሪስ ኢብኑ ቁዳማ ማለት፦ በጣም ችኩል እና ቁጡ ሰው ነው።]

  ገጠሬው ወደ ሓሪስ ኢብኑ ቁዳማ በመሄድ የአምስቱም ጣቶቹ አሻራ በሚያሳይ መልኩ የሞቀ ጥፊ ፊቱ ላይ አኖረለት።

  ሓሪስ ለማሰብ እንኳ ጊዜ አልነበረውም;
🗡ሰይፉን ሳብ አደረገና የገጠሬው እጅ ጎምዶ አሳጠረለት።
   👌አሕነፍ ኢብኑ ቀይስ የፈለገው ይህንኑ ነበር!!




https://t.me/hamdquante
👍15❤7🤝5
✍
አንዳንድ ኢማሞች ግን…………

ዛሬ ጁሙዐ በሰገድኩበት መስጂድ የሆነው…………
   ከኹጥባ በፊት "የዛሬው ኹጥባችን የሚሆነው……" ብሎ ከ50 ደቂቃ እስከ 1ሰዓት የሚረዝም ረዥዥዥም ሙሓደራ።

ከዝያስ?? አትሉም…………
   ከዝያማ ጀምዐው በዚህ ድክምምም አደረገውና የመጀመሪያው ኹጥባ 4ደቂቃ  ሁለተኛው ኹጥባ 3ደቂቃ

ኧረ ይደብራል!!





https://t.me/hamdquante
👌7❤3✍2👍1
👌
    ለየት ባለ መልኩ………

  ወፋፍራም ሰዎች በደንብ አብዝታችሁ ዓፊያ መለመን ይኖርባችኋል!!

  የሆነ አደጋ ሲደርስባቸው ወይም ሲጎዱ ቀላል ነው እንዴ የሚሰቃዩት??!!
   ቤተሰባቸው የሚያየው ስቃይስ??!!

ወላሂ ለፌዝ አይደለም👇
   በተቻላችሁ ያህል ላለመወፈር ተጠንቀቁ!!





https://t.me/hamdquante
💯13❤3👍3👌3🤝3
☕️
Wow የጉራንስ ሴቶች!!

በሐጃ ወደ አጠና ተራ አካባቢ ውዬ ዕርሜን ብዬ የተውኩት የመንገድ ላይ ☕️ቡና ብጠጣ;

👌ቦሌ ከምንጠጣው የስቲም ቡና በዐስር እጥፍ የተሻለ። ኧጅ የትረፍ!!


🫵"እንትን ተጨምሮበት ስለሆነ ነው" የሚል ይቦለካል።




https://t.me/hamdquante
👌9❤7
✍
    ለሰደቃ ሲጠየቅ መቶ ሺህዎች ሚሊየኖች የሚሰጥ ሰው ለምን አይሆንም;
   ስልኩን የሰካበት ቻርጀር ነቅሎ እንዲሰጥህ ስትጠይቀው ደስስስ አይለውም።

የሚተዛዘኑ ባልና ሚስት ሆነው እንኳ………
"እንካ የኔን ሰካው" ስትለው ወይም "እንኪ የእኔን ሰኪው" ሲላት ፊታቸው ላይ ቅሬታ ይታያል።


  በዚህ ዘመን አንድ ሰው ምን ያህል ቸር እንደሆነ ማወቅ ከፈለክ;
   ስልኩ ቻርጅ ላይ ሰክቶት ሳለ ነቅሎ የአንተው እንዲሰካልህ ጠይቀው።


ድረድግ!!




https://t.me/hamdquante
👍18❤6🤝1
✍
ሁሉም ሰው ማለት ይቻላል…………

   ታክሲ ውስጥ ሲገባ: ወይም ከጓደኞቹጋ በተቀማመጠበት;
   ስለ ትላልቅ ጉዳዮች የሚያወራበት ስልክ ሲደወልለት ደስስስ የሚለው ለምንድን ነው???




https://t.me/hamdquante
👍15❤5👌2
☝️
አላህ አይሳሳትም‼️

🌐የጉዳዮቹ አስተናባሪ አላህ እስከሆነ ድረስ;

አሁንም አልሃምዱሊላህ
‼️





https://t.me/hamdquante
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👌16❤8👍4💯2
✍
  በጣም ብዙ ዕቅዶች አታቅድ። ምክንያቱም
      ሕይወት ለአንተ ብዙ ዕቅዶች አሏት!!

  አስተውለህ ከሆነ በሕይወትህ ውስጥ የሆኑት ነገሮች;
   አብዛኞቹ ከዕቅድህ ውጪ የሆኑ ናቸው።




🤝https://t.me/hamdquante
👍29❤5
✍
   አስተውላችሁ ይሆን??…………

  አንዳንድ ጊዜ ምን አልባትም መስጂዶች ሲገነቡ ለጊዜያዊነት ተብለው የሚዘጋጁ ቦታዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ወይም ከከተማ የራቁ ቦታዎች ይሆንና በዘመናዊነት ያልተገነቡ መስጂዶች ሊሆኑ ይችላሉ።

የሆነው ሆኖ……………
   በእነዚህ የዘመናዊነት ጌጥ ባላገኙ መስጂዶች ውስጥ ሲሰገድ የሚገኘው ሰኪናና ሑሹዕ የተለየ ነው!!



https://t.me/hamdquante
❤12👍11
🫵
   አንዳንዶቹ ሰው ላለማስቀየም የሚሄዱበት ርቀት የሚገርም ነው!!

  ጓደኛሞች ናቸው። አብረው ጉዞ ወጥተዋል። ከመሃል ለአንዱ
"ሂድ ስጋ ገዝተህ ና" አሉት።
"እኔ ግዢ አልችልም" አለ።

  ሌላኛው ተልኮ ሄዶ ገዝቶ መጣ። ስጋው ከመጣ በኋላ "ግዢ አልችልም" ላለው;
  "አሁን እሳት አቀጣጥልና ይጠበስ" አሉት።
  "ኧረ እኔ እሳት ማንደድ አልችልም" አለ።

እሳቱን አነደዱትና;
  "በል እሺ ጠባብሰህ አቀራርበው" አሉት።
  "ውይ ይበላሽብኛል: ምንም ጠብሼ አላውቅም" አላቸው።

ጠባበሰው አዘገጃጅተው ካቀረቡት በኋላ;
  "ና እንብላ" ሲሉት…………
  "አሁንም እምቢ ካልኩማ ልትቀየሙኝ ነው" አለና መብላት ጀመረ።





https://t.me/hamdquante
👌22❤14🤝6👍5💯1
🔥
    ወንጀልን አቅልሎ ማየት!!


ኢማም ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ይላሉ፦
  "አንድ ባሪያ ወንጀል ላይ ከዘወተረና ወንጀሉን ልቡ ውስጥ አቅልሎ ማየት ከጀመረ; የሰውየው የመጥፊያው ምልክት ነው።
👉🏽ወንጀል በባሪያ ዐይን በቀለለ ልክ አላህ ዘንድ የከበደ ይሆናል።"

   [الجواب الكافي (٥٨)]



https://t.me/hamdquante
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👌16👍7❤4🤝1
✍
በሐይማኖታዊም ይሁን በፍልስፍና ሚዛን ገለልተኛ የሚባል ነገር የለም!!

ከሐቅ ጋ ያልሆነ ሰው ከባጢል ጋ መሆኑ አይቀሬ ነው!!


📖{فَذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمُ الْحَقُّ ۖ فَمَاذَا بَعْدَ الْحَقِّ إِلَّا الضَّلَالُ}
  {እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነት በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ?}



https://t.me/hamdquante/11296
👌13❤8👍2
✍
ከዛሬ 1145 ዓመታት ወደ ኋላ መልሼ ግሩም ክስተት ላስቃኛችሁ???



☕️እየጠጣችሁ ጠብቁኝ👇👇👇


.
👍27❤9🤝1