ለሙስሊሞች ብቻ
በሸሪዓ ገንዘብ የሚባሉት ስድስት ናቸው:: ስንዴ, ገብስ, ተምር, ጨው, ወርቅ እና ብር:: እነዚህ ውስጥ ያልተካከቱት እንደ ሩዝ, ጤፍ, ቆጮ, አልሙኒየም, ብረት ምን ይሁኑ የሚለው አራቱ የመዝሃብ ሊቃውንት የየራሳቸው መለኪያ እንደ ክብደት መመሳሰል, ስፍር መመሳሰል, የቆይታ ዕድሜ መመሳሰል በሚል ከፋፍለዋል:: (ፊያት መጽሓፌ ላይ በዝርዝር አሉ):: ከእነዚህ ውስጥ ፊያት መገበያያ የለም:: ምክንያቱም ፊያት በራሱ ገንዘብ አይደለም:: ቁጥር የተጻፈበት ቦኖ እንጂ:: መቶ ብር ማለት 100 የሚባል ቁጥር ማዘዋወሪያ ትሪ ነው:: ትናንትና ቁጥሩን በወረቀት ላይ ሲያየው ተጨባጭ መስሎት ሲከራከር የነበረ ምእመን ... ዛሬ ላይ ተጨባጭ እንዳልሆነና በሞባይል የሚወነጨፍ የኤሌክትሮን ዳንስ እንደሆነ ሲያይ ግራ ገብቶት ያዳምጥ ጀምሯል:: አልሃምዱሊላህ!
ሪባ ምንድነው ካልን ሪባ ሁለት ነው::
ሪባ በፖዘቲቭ መልኩ ይመጣል:: ለምሳሌ ከማንም ምስጋናም ይሁን ክፍያ የማይከጀልበት ሶደቃ (ምጽዋት) አላህ ዘንድ ይራባል:: ይህኛው ሪባ ለአላህ የሚሰጥ ቀርዶን ሀሰን ይባላል::
ሁለተኛው ዓይነት ሪባ በደል ያለበት ማንኛውም እንቅስቃሴ ወይም ንግግር ወይም ግብይት ያጠቃልላል:: ሪባ በገንዘብ እና ንግድ ብቻ የታጠረ አይደለም:: ንግግርም ላይ ይኖራል:: ውሻ ብሎ ስድብ የጀመረ ሰው ዝም ካልነው ሶደቃ (ምጽዋት) ሲሆን ውሻ ብለን ብንመልስለት መማለስ (ቂሷስ) ይሆናል:: አሕያ ብለን ብንጨምር ሪባ (በደል) ተፈጠረ:: ንግድ ላይ ተመሳሳይ በደል (ሪባ) አለ:: ሲጠቃለል በደል ካለ ሪባ አለ::
የባንክ ሥርዓት ስረ መሠረቱ የተቋቋመው በበደል ላይ ነው:: ቅኝ ገዥዎች ቀድመው የዓለም ሀገራትን በቀበሌ ከፋፈሉዋቸው:: አሁን የምንጋደ^ልበትና የምንጋ^ደልለት ካርታ እንግሊዝ, ፈረንሳይ እና ጣልያን ናቸው የሳሉት:: እንደ ለቅሶ ቤት ካርታ ነው የሚጫወቱበት:: ስለዚህ ለየቀበሌው የየራሱ ደረሰኝ ወይም ቦኖ ታተመለት:: ለኢትዮጵያ ብር, ለኬንያ ሽልንግ, ለስዑዲ ሪያል ተብሎ ቦኖ ተዘጋጀ:: ቦኖው በማንኛውም ሰዓት የመቀየር, የመጨመርና የመቀነስን ሥልጣን ያዙ:: የኢትዮጵያ ቦኖ ከኢትዮጵያ አይወጣም:: የአሜሪካና የዩሮ ቦኖ ግን የትም ሄዶ ይመነዘራል:: ይህንን የሪባ (በደል) ሲስተም በምንም ብታጥበው አይጸዳም:: በብዙ የሙስሊም ደ^ም ታጥቦም አልጸዳም:: የሚያጸዳው ዕውቀት ብቻ ነው:: በመደዳ መንጋጋት እንደ በዓል በግ በመደዳ ለመታ^ረድ ብቻ ነው::

❤53
ጠይቁ:: ስትጠይቁ ምን ብታውቁ እንኳ ምንም እንደማያውቅ ሕጻን ምሰሉ:: ጠይቁ የምለው እኔ እራሴ በጣም ጅል መስዬ ስለምጠይቅ ነው:: ሀብታም መሆን እስከፈለጋችሁ ድረስ ከመጠየቅ አትቦዝኑ:: ተነዛናዥ አሰልቺ ሁኑ እያልኩ ሳይሆን ለመጠየቅ ego አይያዛችሁ:: አዋቂነት መምሰል ሳይሆን መሆን ነው:: ሀብታም ከሆንክ በምንም አግኘው በሀብታምነት ላይ አዋቂ ነህ:: ወንድሜ ብር ያላቸው ሰዎች ስለሀጅ አደራረግ ሸይኾችን ከሚጠይቁ ይልቅ ሀብታሞችን ይጠይቃሉ:: ስለቤት ዲዛይን እና ፍጆታ ኢንጂነሮችን ከሚጠይቁ ቤት የሠራ ሀብታም ጓደኛቸውን ይጠይቃሉ:: ሸይኹም ሀጅ አላደረጉም:: አያውቁትም:: ኢንጂነሩም ቤት አልሠራም:: በሮማና በላቲን የተጣፉ ፎርሙላዎችን ነው የሚያውቀው:: አይጠቅምም:: ልምድ የግድ ነው:: ከሚያወራው ይልቅ የሆነው ያስተምራል:: ካልሆንክ ጠይቅ::
ዛሬ በብዙ ነገር የምበልጠው አንድ ባለሙያ ጋር ደወልኩ:: 9 ወር የፈጀብኝ ማለትም bottleneck (የብርሌ አንገት) የሆነብኝ ጉዳይ በ9 ሰከንድ ንግግር ፈታው:: ፍሬንድ አላወቀውም እንጂ 90 ሺህ ብር ብከፍለው ያዋጣኛል:: በጣም ተራ ጉዳይ ባለመጠየቅህ ብቻ ድቡልቡል ያደርግሃል:: የጠዋት መረጃ ለከሰዓት እያገለገለ ባልሆነበት ተለዋዋጭ ወቅት ... የጥንት ቲዎሪ ይዘህ ዝም ብለህ ሐሳበ-ድቡልbull ሀብሃብ ነገር ትሆናለህ:: ጭንቅላትህ እስኪሞቅ እና ዲፕረሽን ውስጥ እስክትገባ ድረስ ውል አልባ ይሆንብሃል:: በቃ አማራሪ ትሆናለህ::
እና ዛሬ የአስር ዓመት ስትራተጂክ እና የዓመት ኦፕሬሽናል እቅዴን ቁጭ ብዬ እያሻሻልኩ ነው:: ምን ያህል ትራንስፎርም እንዳደረገኝ እኔ ነኝ የማውቀው:: ሁሌ ስልክ እደውላለሁ:: ባለማወቄ ስደውል በፍጹም አላፍርም:: ቢሮም ሳጸዳ በፍጹም የበታችነት አይሰማኝም:: ሁሌ የሚሸውደኝ ደግሞ በጣም አውቀዋለሁ የምለውን ነገር ነው:: ልንገራችሁ:: በጣም አውቀዋለሁ የምትሉትን ነገር ርዕስ አድርጋችሁ አውሩበት:: ተጠያየቁ:: ምናልባትም የተሳሳተ መረጃ አግኝታችሁ እየደከማችሁ ይሆናል::
ድሮ የፈተና የመጀመሪያውን ፕሮግራም ጽፌ ሄጄ በማትስ ፈተና ቀን ሂስትሪ እጥብ አድርጌ ሄጄ ምን እንደሆንኩ እኔ ነኝ የማውቀው:: ለካ በመሃል ፕሮግራሙ ሁለቴ ሁላ ተቀይሯል:: A group of things is called ለሚለው አጼ በካፋ ወይም ሚካኤል ስሁል ሳልለው አይቀርም:: Set እንዴት ትጠፋኛለች? ፑ!

❤41
በመ-ገንዘብ ስለብሪክስ ሰፊ ሽፋን ነው የሰጠሁት::
ከብሪክስ ሁለቱ ባንኮች አንዱ የሆነው NDB ባንክ መመሥረቻ አንቀጾቹ ውስጥ የአምስቱ ሀገራት (Brazil, Russia, India, China, South Africa) አክሲዮን በምንም ዓይነት ሁኔታ ከ55% በታች ሊሆን አይችልም ይላል::
ከብሪክስ ሁለቱ ባንኮች አንዱ የሆነው NDB ባንክ መመሥረቻ አንቀጾቹ ውስጥ የአምስቱ ሀገራት (Brazil, Russia, India, China, South Africa) አክሲዮን በምንም ዓይነት ሁኔታ ከ55% በታች ሊሆን አይችልም ይላል::
👍7
ኢምፖርት ከሀ እስከ ፐእ ድረስ ያልተመዘገባቺሁ እነሆ ግቡለት:: ከሰለጠኑት ውስጥ ጭነው እኛው ጋር ሲደግሙ ደስ ይላል:: ይህ ብቻም አይደለም:: ሁሉንም ዓይነት ስልጠና የማያመልጣቸው አሉ:: የሚፈለገው ይኸው ነው:: ዘላቂ ደንበኝነት:: ቻይና የሄዳቺሁም መንገድ የዠመራቺሁም ቢሮ Yiwu Futian ገበያ አራራሽ 29 በር ጋር ፊትለፊት ባለጆንትራው ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ ነው:: ድንገት መንገድ ጠፍቷችሁ ለቻይኖቹ "ጎማዎ ጣሻ ናሊ?" ብትሉዋቸው ያሳዩዋችሗል:: ጎማዎ ሕንጻ የት ነው? እንደማለት ነው:: ለዲዲ ራይዶቹም ጎማዎ ጣሻ በሉዋቸው:: ስልጠናው ኢምፖርት ድርጅቶች ላይ ለሚሠራም ሰው ይጠእማል:: ድርጅቱ ከማኔጅመንት ኢንስትቲዩት ጭምርት ያስመሰከረ በመሆኑ የተሳትፎ ሰርተፊኬት ጅራ::
-> ጥቅምት 3,4,5/2019
-> ጥዋት እስከ 6:30
—) ቦታ እዚሁ አዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት አካባቢ
-> ሳቢ: 13,800 ብር ቫትን ጨምሮ
ACC. No. 1000762139646
HAB Management and Technologies PLC
-> ኩባንያዎች ስትከፍሉ ዊዝሆልድ ቀንሳችሁ መስደድ መብት ነው::
-> የምታወራርዱ TIN ጣፉ
በቴሌግራም
t.me/hab_management
ስልክ: +251990555599

Telegram
HAB Management
❤16
ቢዝነስ የሚጀመረው በትናንሽ ደረጃዎች ነው:: ከመፋቂያ ወይም መርፌ ሊሆን ይችላል:: ስትጀምሩ ከትልቅ ቢሮ እና ከትልቅ መነሻ ወጪ ከሆነ ትልቅዬ ውድቀት ነው የምትወድቁት:: ያላችሁን ብር በምርቃና መነሻ ላይ ካፈሰሳችሁት ብዙ ነገራችሁ ይፈሳል:: ዲማንድ ሲያደርጋችሁ ብቻ ወጭ አድርጉ:: ስትጀምሩ ትልቅ ወጭ ዘጭ አድርጋችሁ; then የሆነ መመሪያ ጋር ትፋጠጣላችሁ:: ሦስትና አምስት ወር እምጷ ቀሊጥ ይላል:: ስለዚህ ቢዝነስ ስጀምሩ ልክ ወጪ ጋር ስትደርሱ ኔፓ ሁኑ:: ያለ ወጭ ገቢ ገቢ እንደሌለ እርግጥ ነው:: ገንጠል ተደርጎ የሚከፈልበት ቦታ አለ::
❤24
በያዝኩት ብር ንግድ ልጀምር ወይስ ቤት ልግዛ?
-> ያለምንም ማንገራገር ዲጂታል ካርታ የያዘ ቤት ግዛበት:: ካርታ ያልጨረሰ ስቴድየም ከምትገዛ ዲጂታል ካርታ የያዘ የኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ ይበልጣል:: (ይህ መ-ገንዘብ 2 ላይ በደንብ ተብራርቷል):: ከምንም በፊት Asset ይቀድማል:: መኖሪያ ቤት ከገዛህ የሀብታምነት ግማሽ መንገድ ደርሰሃል:: ንጹሕ ብርህ ቋሚ ንብረት ላይ አድርገህ ትረጋጋለህ:: ንግድ የሚነገደው በሞኝ ብር ነው:: ቤት ስለገዛህም ሀብታም አትሆንም:: ግማሽ መንገድ ጋር ስለደረስክ ንግድ ተረጋግተህ ከትንሽ ትነሳለህ:: ንግድ ማለት end consumers ማወቅ ነው:: እነሱ ያሉት ቻይና ወይም ጂቡቲ ሳይሆኑ አጠገብህ መንደር ውስጥ ናቸው:: የኢትዮጵያ ዋነኛ consumer መንግሥት ነው:: ማን ምን ምርት/አገልግሎት, መች, የት ይፈልጋል? ብለህ መሸጥ መቻል ውስጥ ግባ:: ልክ ሥራው ገብቶህ ዘጭ ብር የሚያስፈልግ ቦታ ስትደርስ ወደ ሞኞች ኪስ ወደ ባንክ ትመጣና ይኸው ሥራዬ ይኸው ዋስትናዬ ስትላቸው ኮት ያነጥፉልሃል:: ከንግድ ብትጀምር ግን ብርህ ይሰባበራል:: ድንገት ብትሞት ልጆችህ ይበታተናሉ:: መጀመሪያ ቂ*ጥህን አሳርፍ:: ጭንቅላትህ ያርፋል:: በዚህ የፋይናንስ ሥርዓት እንደ መመሪያ ያዘው:: (ከስር ላይ ማስታወቂያ አለ)

❤29
Hasen Injamo
በያዝኩት ብር ንግድ ልጀምር ወይስ ቤት ልግዛ? -> ያለምንም ማንገራገር ዲጂታል ካርታ የያዘ ቤት ግዛበት:: ካርታ ያልጨረሰ ስቴድየም ከምትገዛ ዲጂታል ካርታ የያዘ የኮንዶሚኒየም ስቱዲዮ ይበልጣል:: (ይህ መ-ገንዘብ 2 ላይ በደንብ ተብራርቷል):: ከምንም በፊት Asset ይቀድማል:: መኖሪያ ቤት ከገዛህ የሀብታምነት ግማሽ መንገድ ደርሰሃል:: ንጹሕ ብርህ ቋሚ ንብረት ላይ አድርገህ ትረጋጋለህ:: ንግድ…
ኢምፖርት ከሀ እስከ ፐእ ድረስ ያልተመዘገባቺሁ እነሆ ግቡለት:: ስልጠናው ኢምፖርት ድርጅቶች ላይ ለሚሠራም ሰው ይጠእማል:: ድርጅቱ ከማኔጅመንት ኢንስትቲዩት ጭምርት ያስመሰከረ በመሆኑ የተሳትፎ ሰርተፊኬት ጅራ::
-> ጥቅምት 3,4,5/2019
-> ጥዋት እስከ 6:30
—) ቦታ እዚሁ አዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት አካባቢ
-> ሳቢ: 13,800 ብር ቫትን ጨምሮ
ACC. No. 1000762139646
HAB Management and Technologies PLC
-> ኩባንያዎች ስትከፍሉ ዊዝሆልድ ቀንሳችሁ መስደድ መብት ነው::
-> የምታወራርዱ TIN ጣፉ
በቴሌግራም
t.me/hab_management
ስልክ: +251990555599
-> ጥቅምት 3,4,5/2019
-> ጥዋት እስከ 6:30
—) ቦታ እዚሁ አዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት አካባቢ
-> ሳቢ: 13,800 ብር ቫትን ጨምሮ
ACC. No. 1000762139646
HAB Management and Technologies PLC
-> ኩባንያዎች ስትከፍሉ ዊዝሆልድ ቀንሳችሁ መስደድ መብት ነው::
-> የምታወራርዱ TIN ጣፉ
በቴሌግራም
t.me/hab_management
ስልክ: +251990555599
Telegram
HAB Management
😁7
Forwarded from Hawlet Ahmed
ቡና ላኪ ትልቅ ካምፓኒ ነው። ቡናውን ከለቀማ ለኤክስፖርት እስከ ማዘጋጀት ያለው ሒደት ብዙ ወጪ አለው። እና ይሄ ካምፓኒ ለዚህ ዝግጅት የቀጠራቸው እጅግ በርካታ ሰራተኞች ከከተማ በጣም የራቀ ሥፍራ (remote area) ላይ ስለነበር ምግብ ለሰራተኞች ማቅረብ ነበረበት። ኋላ ላይ የዓመቱ የምግብ ወጪ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ደርሶ ታክስ ለመክፈል ወጪውን ቀንሶ ቢያቀርብም ወጪው ተጣለበት። ክፈል ተባለ።
ከፈለ ወይ? አልከፈለም። ለምን? አሁን ሥራ ላይ ባሉት የታክስ ህጎችና መመሪያዎች መሠረት ላይከፍል የሚችልበት ቀዳዳ ስለነበር ተከራክሮ አሸነፈ።
ስለታክስ ማወቅ ለቢዝነስ በሕይወት መቆየት ወሳኝ ነው። ሰልጥኑ!
ስለስልጠናው መረጃ ለማግኘት
👇
ቴሌግራም: t.me/hab_management
🤳 +251990555999
ከፈለ ወይ? አልከፈለም። ለምን? አሁን ሥራ ላይ ባሉት የታክስ ህጎችና መመሪያዎች መሠረት ላይከፍል የሚችልበት ቀዳዳ ስለነበር ተከራክሮ አሸነፈ።
ስለታክስ ማወቅ ለቢዝነስ በሕይወት መቆየት ወሳኝ ነው። ሰልጥኑ!
ስለስልጠናው መረጃ ለማግኘት
👇
ቴሌግራም: t.me/hab_management
🤳 +251990555999
❤16
በጣም ዲጂታል በሆንን ቁጥር በጣም ነው ደሃ የምንሆነው:: ምክንያቱም እያንዳንዱ እንቅስቃሴህ በትክክል ይታወቃል:: BRICS ላይ በራስ ገንዘብ ለመገበያየት የብሔራዊ ባንክ ዲጂታል ገንዘብ ነው የተጠየቀው:: ይህ ብቻ ሳይሆን ዲጂታል ገንዘቡ በወርቅ የተደገፈ መሆን አለበት:: አንድ ቶን የሚባል የብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ካለ አንድ ቶን ወርቅ መኖር ይናርበታል:: ሲገለበጥ የተመዘገበ ወርቅ ይኑርህ ነው:: የንግድ ባንክ ሳይሆን የብሔራዊ ባንክ ዲጂታል ገንዘብ የተፈለገው ከብድር አይቀላቀልም:: ከየት ተነስቶ የት ላይ እንዳለ ይታወቃል:: ተጨማሪ ገንዘብ ቢፈጠርበት በቀላሉ ይታወቃል::
(መ-ገንዘብ 2ን ደገምገም አድርጋችሁ ብታነቡ ቀላል ይሆናል)
(መ-ገንዘብ 2ን ደገምገም አድርጋችሁ ብታነቡ ቀላል ይሆናል)
❤20
ተደራሽነቱ ይበልጥ ለማስፋት ይቻል ዘንድ
መ-ገንዘብ 2 የአዋቂ
እና
መ-ገንዘብ 3 የልጆች
ጃዕፈር ጋር ገብቷል:: በጃዕፈር በኩል በመደበኛው የሽያጭ መስመር መስተናገድ ይቻላል::
ቀድማችሁ እኔ ጋር የከፈላችሁ እና በአንዳንድ ምክንያት ያልወሰዳችሁ ምእመናን በዚያው በፖስታ ቤት እየተዳረሰ ነው:: ዛሬም ድረስ "Delivered” የሚል መሴጅ እየገባ ነው:: እኔ ጋር ከፍሎ ለመውሰድ ያልተመቸው ሰው ብሞት እንኳ ከወራሾቼ መውሰድ ይችላል:: ለሁሉም ሐቁን አስቀምጫለሁ:: ለነበረን መልካም ቆይታ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ::
ቃላት የሌለው ምስጋና ይድረሳችሁ:: በድምጽ እና በቪዲዮ ማስረዳቴን እቀጥላለሁ:: አሁን የሚዲያ ውይይት ተራ ይመስለኛል::
ጃዕፈር መጽሓፍት መደ-ብር ብቻ
+251 91 112 5324

👏33
ቤት የገዛችሁ ሰዎች ቀጣይ እርምጃ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ አውጥቶ መሸቀል ነው:: ንግድ ሳይኖራችሁ ቤት ስለገዛችሁ ባንክ አያበድራችሁም:: ባንክ የናንተ ቤት ላይ እንቅልፍ አይሸጥበትም:: ብር እንጂ ልጅ አያስወልድበትም:: ባንክ በሐራጅ ሊሸጥ የሚችለው ከብድሩ ቢበዛ 5% ነው:: የባንክ ትልቁ ዓይን የንግድ እንቅስቃሴያችሁ እንጂ የቤታችሁ ውበትና ጥራት አይደለም:: ሆኖም ግን አሪፍ እንቅስቃሴ ኖሮኣችሁ ቤት ከሌላችሁም አይሰማችሁም:: ሁለቱ በአንድ ወቅት መገኘት አለባቸው:: ቤቱ በእናንተ ቢዝነሱ በወንማችሁ ቢሆን ችግር የለውም:: ወንድማችሁ ዋስ ሆናችሁ ማለት ነው:: ዋና የቤት ባለካርታውና ሚስትየው ይስማሙ እንጂ ስሙ በናንተ ባይሆንም ለባንክ ይሆናል:: ቢዝነሱና የዋስትና ቤቱ በራሳችሁ ከሆነ አቦስቶ ነው:: ፈያdha.
መ-ገንዘብ 2 ላይ በ detail እና የታዳጊዎች 3 ላይ በሚመጥናቸው ቋንቋ ተጥፏል::
መ-ገንዘብ 2 ላይ በ detail እና የታዳጊዎች 3 ላይ በሚመጥናቸው ቋንቋ ተጥፏል::
❤20
Hasen Injamo
ቤት የገዛችሁ ሰዎች ቀጣይ እርምጃ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ አውጥቶ መሸቀል ነው:: ንግድ ሳይኖራችሁ ቤት ስለገዛችሁ ባንክ አያበድራችሁም:: ባንክ የናንተ ቤት ላይ እንቅልፍ አይሸጥበትም:: ብር እንጂ ልጅ አያስወልድበትም:: ባንክ በሐራጅ ሊሸጥ የሚችለው ከብድሩ ቢበዛ 5% ነው:: የባንክ ትልቁ ዓይን የንግድ እንቅስቃሴያችሁ እንጂ የቤታችሁ ውበትና ጥራት አይደለም:: ሆኖም ግን አሪፍ እንቅስቃሴ ኖሮኣችሁ ቤት…
መ-ገንዘብ 2 & 3 የተወሰኑ ኮፒዎች ጃዕፈር ጋር ስላሉ ከፍላችሁ የግል ማድረግ ትችላላችሁ::
+251 91 112 5324
+251 91 112 5324
❤7
አንዳንድ ተማሪዎች ማትሪክ ጥሩ ነጥብ ይዘው ግን የ AAU መግቢያ ፈተና ከመቶ 50 ካላመጡ ... መቁረጫው ነጥብ ቢሞላላቸውም AAU መግባት አይችሉም:: ምሳሌ ማትሪክ 500 ያመጣ ተማሪ ይኮርጅ አይኮርጅ የሚታወቀው የAAU መግቢያ ፈተና ከ>50 በላይ ሲያመጣ ብቻ ነው:: ማትሪክ 300 አምጥቶ ወዲህ የAAU መግቢያ ከሰቀለ ያልፋል::
ሀገራችንን ሰላም ያድርግልንና ተዟዙረው የመማር እድል ይመልስልን:: ወላጅ ልጁን ክፍለሃገር ሲልክ ይበላሽ ይሆን ብሎ ብቻ ነበር የሚሰጋው:: አሁን እኮ ይመለስ ይሆን ወይስ ይታገት ይሆን እያለ በሐሳብ ይብላላል:: ለሰላም ምንም ይከፈላል::
ሀገራችንን ሰላም ያድርግልንና ተዟዙረው የመማር እድል ይመልስልን:: ወላጅ ልጁን ክፍለሃገር ሲልክ ይበላሽ ይሆን ብሎ ብቻ ነበር የሚሰጋው:: አሁን እኮ ይመለስ ይሆን ወይስ ይታገት ይሆን እያለ በሐሳብ ይብላላል:: ለሰላም ምንም ይከፈላል::
👍37
ቻይና አንድ ሾፕ ገብተህ መቶ ሺህ ዓይነት ዕቃ ጋር ትፋጠጣለህ:: ከዚያ ያዋጣኛል አያዋጣኝም ለማለት የምትጠቀምበት ቀላል ካልኩሌሽን አለ:: ሦስት መሠረታዊ ዋጋዎች እና መሸጫውን ካወቅህ እዚያው በደቂቃዎች ውስጥ ትርፍና ኪሳራውን ትበይናለህ:: ይህንን በስልጠና ቁልጭ እናደርገዋለን:: ከዚያ ደግሞ በምትሄድበት መስመር ሁላ ሰዎች ጋር እናገናኝሃለን:: ማን ጥሩ ትራንዚተር እንደሆነ ማን አካውንቲንግና ታክስ ላይ እንደሚያሳልጥልህ ተመቻችቷል:: ካንተ የሚጠበቀው ከነቫቱ 13,800 ብር ብቻ ትወረውርና የስልጠና ሆቴል መገናኘት ብቻ ነው::
ቀን ጥቅምት 345/2019
ሰዓት ከጠዋቱ 2 እስከ 6:30
ቦታ አዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት አካባቢ በአካል ብቻ
ቀን ጥቅምት 345/2019
ሰዓት ከጠዋቱ 2 እስከ 6:30
ቦታ አዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት አካባቢ በአካል ብቻ
❤8
Hasen Injamo
ቻይና አንድ ሾፕ ገብተህ መቶ ሺህ ዓይነት ዕቃ ጋር ትፋጠጣለህ:: ከዚያ ያዋጣኛል አያዋጣኝም ለማለት የምትጠቀምበት ቀላል ካልኩሌሽን አለ:: ሦስት መሠረታዊ ዋጋዎች እና መሸጫውን ካወቅህ እዚያው በደቂቃዎች ውስጥ ትርፍና ኪሳራውን ትበይናለህ:: ይህንን በስልጠና ቁልጭ እናደርገዋለን:: ከዚያ ደግሞ በምትሄድበት መስመር ሁላ ሰዎች ጋር እናገናኝሃለን:: ማን ጥሩ ትራንዚተር እንደሆነ ማን አካውንቲንግና ታክስ…

❤5