ሊያና ኬር Liyana Care 7755
5.74K subscribers
327 photos
4 videos
1 file
213 links
➮ የጤና ምክሮች 👨‍⚕️
➮ ሀኪምዎን ያማክሩ7755
➮ ቴሌሜዲስን 💉
➮ በአይነቱ ለየት ያለ ሀክምና📱📲
Download Telegram
🚨 ወዳጅ እና ጠላት ክፍል አንድ

አብዛኛው ሰው በሽታ የሚመጣው በበሽታ አምጪ ተህዋስያን (Infections) አሊያም በዘር (Genetics) ነው ብሎ ያስባል። ሆኖም ግን የገዛ ሰውነታችን የራሳችን ጠላት የሚሆንበት ጊዜስ እንዳለስ ሰምተዋል?

🛡 ⚔️ይህ "አውቶኢሚዩኒቲ" (Autoimmunity) ይባላል።

🧬የሰውነታችን የመከላከል አቅም (Immune System) ግራ በመጋባት የራሳችንን ጤናማ ሴሎች እንደ ባዕድ በመቁጠር ማጥቃት ሲጀምር የሚከሰት እክል ነው።
🔹ለምሳሌ፦ ስለእነዚህ ህመሞች ሰምተው እንደሚያውቁ እርግጠኛ ነኝ፤ ለምጥ (Vitiligo) እና የመጀመሪያው ዓይነት የስኳር በሽታ (Type 1 Diabetes) እነዚህ ህመሞች የሰውነት መከላከያ ራሱን ሲያጠቃ የሚከሰቱ መሆናቸውን ያውቁ ኖሯል?

🔹ይህ "አውቶኢሚዩኒቲ" (Autoimmunity) በአሜሪካ ብቻ ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ያጠቃል።

📍የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ለዚህ ተጠያቂው እየተቀየረ የመጣው ዓለማችን ነው። ለምሳሌ፦

❌ የምግባችን ይዘት በከፍተኛ ሁኔታ መለወጥ

❌ የአየር ብክለት እና መርዛማ ኬሚካሎች (Xenobiotics)

❌ ከፍተኛ ውጥረት (Stress) እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች ናቸው የሚሉ ጥናቶች ይነበባሉ፡፡

"አውቶኢሚዩኒቲ" ከእንግዲህ ብርቅ አይደለም። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በቅርቡ በዓለማችን ላይ ዋነኛ ከሚባሉ የጤና እክሎች አንዱ ሊሆን ይችላል። -------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
🚨 ወዳጅ እና ጠላት ክፍል ሁለት፡
በክፍል አንድ ላይ "ኦቶኢሚዩኒቲ" ምን እንደሆነና ለምን እንደሚከሰት አይተናል። አሁን ደግሞ ምልክቶቹን እናያለን፡፡

✨የኦቶኢሚዩኒቲ ህመሞች ምልክቶች እንደየበሽታው ዓይነት ይለያያሉ፤ ነገር ግን አንድ የጋራ እውነት አለ፤ እነዚህ በሽታዎች ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ድረስ ማንኛውንም የሰውነት ክፍል ሊያጠቁ ይችላሉ። 🤕🦵👁

⚡️የተለመዱ ምልክቶችና የሚያጠቁት የሰውነት ክፍል፦

💪 ጡንቻዎች (Muscles)፦

🔹ጡንቻን የሚነኩ የኦቶኢሚዩኒቲ ህመሞች ከፍተኛ የጡንቻ መድከምን (Muscle Weakness) ያስከትላሉ።

🦴 መገጣጠሚያዎች (Joints)፦

🔹እንደ "ሩማቶይድ አርትራይተስ" (Rheumatoid Arthritis) አይነት ህመም ካለብዎ የመገጣጠሚያ ህመም፣ እብጠት ወይም የሰውነት መገተር (Stiffness) ሊሰማዎ ይችላል።

🩸 ደም እና ሆርሞን (Blood & Hormones)፦

🔹ለምሳሌ የመጀመሪያው ዓይነት የስኳር በሽታ (Type 1 Diabetes) በደም ውስጥ ከፍተኛ የስኳር መጠን (Hyperglycemia) እንዲኖር ያደርጋል።

👁 ዓይን (Vision)፦

🔹አንዳንድ የኦቶኢሚዩኒቲ ህመሞች የማየት ችሎታን ወይም የዓይን ጤናን ሊያቃውሱ ይችላሉ።

❇️ አብዛኛዎቹ የዚህ ዓይነት ህመሞች በውስጥም ሆነ በውጭ "መቆጣትን" ያስከትላሉ። ምልክቶቹም የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፦

🌡 የሙቀት ስሜት ወይም መለብለብ (Warmth)

🔴 የቆዳ ቀለም መለወጥ ወይም መቅላት (Redness)

🎈እብጠት (Swelling)

😫 ህመም (Pain)

⚠️እነዚህን ምልክቶችን ካዩ እንዲሁም ምክንያቱን ማብራራት የማይችሉት አዲስ የህመም ምልክት ካስተዋሉ፣ በተለይም ደግሞ ከወትሮው በተለየ ጤነኛ እንዳልሆኑ በተደጋጋሚ የሚሰማዎ ከሆነ ሳይዘገዩ የጤና ባለሙያ ያማክሩ።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
እራስን ከጭንቀት/ውጥረት ለማረጋጋት የሚረዱ መንገዶች

🤯አእምሮአችን በሃሳብ ሲወጠር እና ስጋት ሲሰማን፣ ሰውነታችንን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ እነዚህን 3 ሳይንሳዊ ዘዴዎች እንጠቀም፦

1. የ 5-4-3-2-1 ዘዴ (ለማረጋጋት) በዙሪያህ ያሉትን ነገሮች በማስተዋል አሁናዊ ሁኔታ ላይ ለማተኮር ይረዳል፡
👁 5 የሚታዩ ነገሮችን ተመልከት
🖐 4 የሚዳሰሱ ነገሮችን ንካ (ልብስህ፣ ጠረጴዛ...)
👂 3 የሚሰሙ ድምጾችን አድምጥ
👃 2 የሚሸቱ ነገሮችን አሽት
👅 1 የሚቀመስ ነገር (ወይም የአፍህ ጣዕም)

2. የሳጥን አተነፋፈስ (Box Breathing) የልብ ምትን ለማርገብ እና አየር በአግባቡ ለማግኘት፦
• ለ 4 ሰከንድ ወደ ውስጥ መተንፈስ • ለ 4 ሰከንድ ትንፋሽን አፍኖ መያዝ • ለ 4 ሰከንድ ትንፋሽን ቀስ ብሎ ወደ ውጭ ማውጣት • ለ 4 ሰከንድ አየር ሳያስገቡ መቆየት (ይህን 3-4 ጊዜ ደጋግመው)

3. ጡንቻን ማዝናናት (progressive Muscle Relaxation) በውጥረት ምክንያት የጠጠሩ ጡንቻዎችን ለማላላት፦ • ከእግር ጣትህ ጀምረህ እያንዳንዱን የሰውነት ክፍል ለ 5 ሰከንድ አጥብቀህ ወጥር፣ ከዚያም በድንገት ልቀቀው። ወደ ላይ እስከ ፊትህ ድረስ ይህንኑ መቀጠል። -------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
🧂 ጨው አታብዙ! ጨው ቀንሱ! ሲባል ሰምታችኋል ግን ለምን?

🔍 በመጀመሪያ ጨው እና ሶዲየም ምን እንደሆኑ እንለይ

⚡️ሰዎች ጨውና ሶዲየም የሚሉትን ቃላት በተለዋዋጭነት ቢጠቀሙባቸውም፣ ሁለቱ የተለያዩ ነገሮች ናቸው ።

•ጨው (Salt): ሶዲየም ክሎራይድ (የገበታ ጨው) ሲሆን፣ 40% ሶዲየም እና 60% ክሎራይድ የያዘ ውህድ ነው ። እንደ ምግብ ማቆያ፣ ለቅመማ ቅመም እና ለኢንዱስትሪ ሂደቶች ያገለግላል።
•ሶዲየም (Sodium): ምልክቱ Na እና የአቶሚክ ቁጥሩ 11 የሆነ ኬሚካላዊ ንጥረ ነገር ነው ። ለስላሳ፣ ብርማ ነጭ እና በጣም ንቁ (highly reactive) የሆነ ብረት ሲሆን በመሬት ውስጥ በብዛት ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች ስድስተኛ ደረጃን ይይዛል።

⚙️ የሶዲየም ጥቅም በሰውነታችን ውስጥ

⚡️ሶዲየም ለሰውነታችን በጣም አስፈላጊ የሆነ ንጥረ ነገር ሲሆን የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፦
•በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የውሃ መጠን ያመጣጥናል ።
•የአሲድ-ቤዝ ሚዛንን ይጠብቃል።
•የጡንቻ እና የነርቭ ሥርዓት በአግባቡ እንዲሰሩ ያደርጋል ።
•አስፈላጊ ማዕድናት በደም ውስጥ እንዲቆዩ ይረዳል ።

⚠️ ከመጠን በላይ ጨው መውሰድ የሚያስከትለው ጉዳት

⚡️ሰውነትዎ በአግባቡ እንዲሰራ ትንሽ መጠን ያለው ሶዲየም ያስፈልገዋል ። ነገር ግን ከመጠን በላይ መውሰድ ለጤናዎ ጎጂ ነው ።
•የደም ግፊትን ይጨምራል ።
•ለልብ ሕመም እና ለስትሮክ አደጋ ያጋልጣል ።
•ለኩላሊት በሽታ እና ለአጥንት መሳሳት (osteoporosis) መንስኤ ሊሆን ይችላል ።

📏 የሚመከረው መጠን (WHO)
•ለአዋቂዎች: በቀን ከ2000 ሚ.ግ. ሶዲየም (ከ5 ግራም ጨው ጋር እኩል የሆነ) ወይም ከአንድ የሻይ ማንኪያ በታች ።
•ከ2 እስከ 15 ዓመት ለሆኑ ልጆች: እንደ ልጆቹ የኃይል ፍላጎት መጠን ቀንሶ እንዲሰጥ ይመከራል።

🔬 ከፍተኛ የጨው አጠቃቀም ለደም ግፊት የሚዳርገው በምን ሳይንሳዊ መንገዶች ነው?

1.የፈሳሽ መከማቸት (Water Retention): በሰውነት ውስጥ ከፍተኛ የፈሳሽ ክምችት እንዲኖር ያደርጋል ።

2.የደም ቅዳ ቧንቧዎች መጥበብ (Systemic Peripheral Resistance)።

3.የደም ሥር መቆጣት (Endothelial Dysfunction)።

🧂 ያነሰ ጨው፣ የተሻለ ጤና። -------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
ስለ አእምሮ ጤና ማወቅ ያለብን እውነታዎች

❌የተሳሳተ እምነት ፦ "የአእምሮ ጤና ችግር የሚገጥመው መጥፎ እድል ወይም 'እርግማን' ላለባቸው ሰዎች ብቻ ነው።"
✅ እውነታ፦ ማንኛውም ሰው ሀብታም፣ ድሃ፣ የተማረም ሆነ ያልተማረ በህይወቱ የአእምሮ ህመም ሊገጥመው ይችላል።

❌የተሳሳተ እምነት ፦ "የአእምሮ ጤና ባለሙያ ጋር መሄድ ለ'እብዶች' ብቻ ነው።"
✅ እውነታ፦ ወደ ባለሙያ መሄድ የአእምሮን ሰላም ለመጠበቅ፣ የተሻለ ውሳኔ ለመወሰን እና የህይወት ፈተናዎችን ለመቋቋም የሚረዳ 'ዘመናዊ እና ብልህ' ምርጫ ነው።

❌የተሳሳተ እምነት ፦ "የአእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ማህበራዊ ህይወት መምራት አይችሉም።"
✅ እውነታ፦ ተገቢውን ክትትል እና ድጋፍ ካገኙ፣ ማንኛውም ሰው ውጤታማ እና ደስተኛ ህይወት መምራት ይችላል።

❌የተሳሳተ እምነት፦ "ለአእምሮ ጤና መድኃኒት መውሰድ ሱስ ያስይዛል።"
✅ እውነታ፦ በሀኪም የታዘዙ መድኃኒቶች አእምሮ ውስጥ ያሉ ኬሚካሎችን ለማስተካከል የሚረዱ እንጂ ሱስ የሚያስይዙ አይደሉም።

❌የተሳሳተ እምነት፦ "የአእምሮ ችግር ያላቸው ሰዎች ደካማ ናቸው።"
✅ እውነታ፦ የአእምሮ ጤና ችግሮች ከብዙ ነገሮች ሊመጡ ይችላሉ፤ እንደ ጭንቀት፣ የህይወት ችግሮች፣ የአካል እና የአእምሮ ሁኔታዎች። ይህ ከ “ደካማነት” አይደለም።

❌የተሳሳተ እምነት፦“የአእምሮ ጤና ችግር ካለ ማዳን አይቻልም።”
✅ እውነታ፦ ብዙ ሰዎች በማማከር (counseling)፣ በሕክምና ይሻሻላሉ፣ ይድናሉ እና መደበኛ ሕይወት ይኖራሉ። -------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
🔥 የሆድ ስብ ወይም ቦርጭ መንስኤዎች — እና ለምን ሊያሳስባችሁ ይገባል!

የሆድ ስብ የውበት ወይም የቅርፅ ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ ጤናችሁ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል። በቀላል መንገድ እንደሚከተለው እንረዳው 👇

👉 የሆድ ስብ አይነቶች

🔹ቪሰራል ስብ (Visceral fat) – የሰውነት የውስጥ ክፍሎችን (Internal organs) የሚከብ — ይበልጥ አደገኛ ነው ⚠️

🔷 ከቆዳ በታች ስብ (Subcutaneous fat) – ከቆዳ ስር የሚገኝ ስብ

⚡️ የሆድ ስብ መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

🍔 ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ – ከመጠን ያለፈ ስኳር እና የተቀነባበሩ (Processed) ምግቦች።

🛋 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማነስ – በቂ ካሎሪ አለማቃጠል።

🍺 ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣት።

😰 ጭንቀት (Stress) – ስብ የሚያጠራቅመውን 'ኮርቲሶል' የተባለ ሆርሞን ይጨምራል።

🧬 በዘር (Genetics) – አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሮ ለሆድ ስብ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።

😴 በቂ እንቅልፍ ማጣት – ከመጠን በላይ ለመመገብ እና ለስብ ክምችት ይዳርጋል።

🚬 ሲጋራ ማጨስ –በአጠቃላይ ሲታይ፣ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች ይልቅ ዝቅተኛ የሰውነት ክብደት መመጠኛ (BMI) ይኖራቸዋል። ሆኖም ግን ከቪሰራል ፋት (Visceral fat) መጨመር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው።

🚨 ለምን አደገኛ ይሆናል?
ከመጠን ያለፈ የሆድ ስብ ለእነዚህ ህመሞች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል፦
❤️ የልብ በሽታ እና የልብ ድካም
🧠 ስትሮክ እና የመርሳት በሽታ (Dementia)
🩺 ከፍተኛ የደም ግፊት
🍬 ዓይነት 2 ስኳር በሽታ
🎗 የተወሰኑ የካንሰር አይነቶች (የጡት እና የትልቁ አንጀት)
🌬 አስም

✅ ዛሬውኑ እርምጃ ይውሰዱ!
ትናንሽ ለውጦች = ትልቅ ውጤት ያመጣሉ

የተመጣጠነ ምግብ ይመገቡ 🥗
በተለይ ስኳር፣ፓስታ፣ማካሮኒ፣የታሸጉ ምግቦች፣ ብስኩት፣ለስላሳ መጠጦች እና አልኮል መጠቀም ይቀንሱ ።

እንቅስቃሴ ያድርጉ 🏃‍♂️

በቂ እንቅልፍ ይተኙ 😴

ጭንቀትን ይቆጣጠሩ 🧘‍♀️

💡 ጤናዎ ትልቅ ዋጋ አለው — ዛሬውኑ ጤናዎን መጠበቅ ይጀምሩ! -------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
📍 ስለ ሳይነስ (Sinus) ማወቅ የሚገቡን ቁልፍ ነጥቦች! 👃
ሳይነሶች (Sinuses) በአየር የተሞሉ የራስ ቅል ውስጥ የሚገኙ ክፍተቶች ሲሆኑ፣ ወደ ውስጥ የሚተነፍሱትን አየር ለማርጠብና ለማጣራት የሚረዳ ፈሳሽ (Mucus) ያመነጫሉ። በተጨማሪም የራስ ቅል ክብደት እንዲቀንስና የድምፅ ማስተጋባት እንዲኖር ይረዳሉ።

የሳይነስ ኢንፌክሽን (Sinusitis) ምንድነው?
ይህ ሕመም የሚከሰተው በሳይነስ ውስጠኛው ክፍል ላይ መቆጣት ሲፈጠር ነው። ይህ መቆጣት አብዛኛውን ጊዜ በቫይረስ፣ በአለርጂ ወይም በባክቴሪያ ምክንያት የሚመጣ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት ብዙ ፈሳሽ ስለሚጠራቀም ለጀርሞች መራባት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

⚠️ ዋና ዋና ምልክቶች
ምልክቶቹ እንደ ሕመሙ ጽኑነት ሊለያዩ ቢችሉም፣ በብዛት የሚታዩት፦

🟢 ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ፦አብዛኛውን ጊዜ ቢጫ ቀለም ያለው ፈሳሽ።

💧 የጉሮሮ ውስጥ ፈሳሽ (Postnasal drip) ፦ ንፍጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ታች ሲፈስ።

😖 የፊት ሕመም፦ በዓይን፣ በአፍንጫ፣ በጉንጭ እና በግንባር ዙሪያ የጫና ስሜትና እብጠት።

👃 መታፈን፦ የአፍንጫ መታፈን ወይም የንፍጥ መዝረክረክ።

🤒 ሌሎች፦ ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ ሳል፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ መጥፎ የአፍ ጠረን፣ የጥርስ ሕመም እና የማሽተት/የመቅመስ ችሎታ መቀነስ።

💊 ሕክምና እና መፍትሔዎች
በጥናቶች መሠረት 70% የሚሆኑት አጣዳፊ የሳይነስ (acute sinusitis) ሕመሞች በቤት ውስጥ በሚደረጉ ጥንቃቄዎች ሊድኑ ይችላሉ።

ምልክቶቹን ለማቃለል የሚረዱ ዘዴዎች፦

1. አፍንጫን በጨው ውሃ መታጠብ።

2. ሰውነት በፍጥነት እንዲያገግም እረፍት ማድረግ።

3. የፊት አካባቢን ሞቅ ባለ ፎጣ መያዝ።

4. የፈላ ውሃ እንፋሎትን በጥንቃቄ መሳብ።

5. የሕመም ማስታገሻዎች እና አፍንጫን የሚከፍቱ (Decongestant) የሚረጩ መድኃኒቶችን መጠቀም።

🔔 የቀሩት 30% ግን ሕመሙ እየጸና ስለሚሄድ የግድ የሐኪም እገዛ እና የሕክምና ክትትል ያስፈልጋቸዋል። ሕመሙ ረዘም ላለ ጊዜ ከቆየ ወደ ሐኪም መሄድዎን አይዘንጉ! -------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
አውቶፎቢያ (Autophobia)

አውቶፎቢያ ማለት ብቻን የመሆን ወይም የመገለል ከፍተኛ ፍርሃት ነው 😨። አንድ ሰው ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ እና አስተማማኝ ቦታ ላይ ቢሆንም እንኳ፣ ብቻውን ሲሆን ከፍተኛ ጭንቀት ይወርረዋል።

⚠️ ዋና ዋና ምልክቶች

😱ብቻን ሲሆኑ መፍራት ወይም የድንጋጤ (panic) ስሜት መሰማት።

👥ብቻን የመሆንን ሁኔታ ለማስቀረት ሁልጊዜ ሌላ ሰው መፈለግ።

🚨 "ብቻዬን ብሆን አደጋ ይደርስብኛል" የሚል ከልክ ያለፈ ስጋት።

😕 ብቻን ሲሆኑ የልብ ምት መጨመር፣ ማላብ ወይም መተንፈስ መቸገር።

🩺 መፍትሄው ምንድን ነው?
አውቶፎቢያ የባለሙያ ድጋፍ ያስፈልገዋል ፦

🗣CBT (ኮኚቲቭ ቢሄቭየራል ቴራፒ)፦ ስለ ብቸኝነት ያለንን የተሳሳተ ፍርሃት የመቀየር ህክምና።

🚶‍♂️Exposure Therapy፦ ብቻን የመሆንን ሁኔታ ቀስ በቀስ በመለማመድ ፍርሃቱን የማላመድ ህክምና።
-------------------------------------------------------
ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia
መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
ለመላው የ ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ!እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳቹ!
በዓሉ የሰላም፣ የጤና ፣ የፍቅር ፣ እና የመተሳሰብ ይሁንልዎ።
መልካም የትንሳኤ በዓል።