M.O.R East Addis Ababa Branch
25.3K subscribers
6.52K photos
18 videos
631 files
390 links
East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for collecting revenue from customs duties and domestic taxes.
Download Telegram
ማስታወቂያ ለግብር ከፋዮች!

ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤2
የየታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ማስተካከያ ማድረግ የሚቻልበት ጊዜ እና ማስተካከያው የሚኖረው ውጤት

ጥቅምት 25 /2019 ዓ.ም( ምስራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት )

በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ማስተካከያ ማድረግ ስለሚቻልበት ጊዜ እና ማስተካከያው ስለሚኖረው ውጤት የሚከተለውን ይላል፦

የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ስህተት የማረም ሂደት የሚጀመረው ታክስ ከፋዩ ስህተት ይታረምልኝ የሚል ማመልከቻ ሲቀርብ ወይም የታክሱ ባለስልጣን በራሱ ተነሳሽነት ስህተት መኖሩን ሲያምንበት ነው፡፡

የታክሱ ባለልጣኑ በታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ላይ ማስተካከያ ማድረግ የሚችለው በሚከተለው ጊዜ ውስጥ ይሆናል፦

ሀ) የመጀመሪያው የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአምስት (5) አመታት ውስጥ፤ ወይም
ለ) ስህተቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በአንድ (1) ዓመት ውስጥ፤ ወይም ከሁለቱ በቀደመው ጊዜ፤

በአዋጁ መሰረት የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ማስተካከያው ስለሚኖረው ውጤት የሚከተለውን ይላል፡-
የሚዘጋጀው የተስተካከለ የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ፦
ሀ) በተደረገው ማስተካከያ ልክ የመጀመሪያውን የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ የሚተካ ይሆናል፤
ለ) በዚህ አዋጅ መሰረት እንደተሰጠ የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ይቆጠራል።
❤12
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋዮች ታክስን በፈቃደኝነት የመክፈል ባህላቸው እንዲጎለብትና ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የ«ሞጁላር»ስልጠና በመስጠት ውይይት አካሄደ።
ምስራቅ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት(ጥቅምት25ቀን2019ዓ.ም.)
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ  ግብር ከፋዮች ታክስን በፈቃደኝነት የመክፈል ባህላቸው ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የ«ሞጁላር»ስልጠና መስጠቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።ግብር ከፋዮች ታክስን በፈቃደኝነት የመክፈል ባህላቸው እንዲጎለብትና ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የ«ሞጁላር» ስልጠና  የመስጠት ሀላፊነቱን  ቅርጫፉ እየተወጣ ይገኛል፤ለ90 ሰዓታት የሚቆየው ይህ ስልጠና፤ ግብር ከፋዮች ስለ ታክስ ምንነት፣ አዋጆች፣ መመሪያዎችና አጠቃላይ አሰራሮች በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚያስችል ነው።
በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት በጥቅምት  ወር ሶስተኛ ሰሚስተር እያጠቃለሉ ለሚገኙ ሞጁላር ሰልጣኞች የመጨረሻውን  ስልጠና የወሰዱ ሲሆን በአሰለጣጠን ሂደቱ ላይም ውይይት ተካሄዷል ፤ አዲሱን የታክስ አስተዳደር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1434/2018 ላይ መሰረት በማድረግ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶች» የተመለከተ ስልጠና ተስጥቷል። ስልጠናውን የሰጡት የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደትአስተባባሪ ወ/ሮ የሺወርቅተጫነ ናቸው።
ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላም የስራ ሂደት አስተባባሪዋ ከሰልጣኞቹ ጋር በአጠቃላይ በትምህርት አሰጣጡ ሂደትና በተነሱ ሃሳቦች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡
❤12
❤2👏2👍1