M.O.R East Addis Ababa Branch
25.3K subscribers
6.52K photos
18 videos
631 files
390 links
East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for collecting revenue from customs duties and domestic taxes.
Download Telegram
ድጋፍና ክትትሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል
ጥቅምት 27/2019  //ምስራቅ አ/አ/አነ/ግለ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት//
የ2018 በጀት ዓመት የንግድ ትርፍ ማስታወቂያ እና መክፈያ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ ቀርቷል ። ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱም በቀሩት ቀናት ለማስታወቅና ለመክፈል ለሚመጡ ግብር ከፋዮች የአገልግሎት አሰጣጡ ሁኔታ ምን እንደሚመስል በቅርበት በመከታተል ላይ ይገኛል።
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወርቅዓለም ተሾመ፣ እንዲሁም ምክትል ሥራ አስኪያጆች፣ የተቋማዊ ሥጋት ሥራ አመራርና ሥነ-ምግባር ቡድን  እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች  ከተመረጡ ኮሚቴዎች  ጋር  በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያደረጉ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል።
በዚህ አጋጣሚ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር እስካሁን ያላሳወቃችሁና ያልከፈላችሁ ግብር ከፋዮች፣ በቀሩት ሁለት ቀናት ውስጥ በኤሌክትሮኒክስ የታክስ ማሳወቂያ (e-Tax) ሥርዓት በመጠቀም ግዴታችሁን እንድትወጡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል።
❤2👏1
ለ ህግ ባሙያዎች የዓመታዊ የግብር/ታክስ ማሳወቂያ ፎርም ይመለከታል፡
❤2🔥1
ቅሬታ እና ጥቆማ ማቅረብ የሚያስችል ሥርዓት ይፋ ተደረገ

ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር ይፋ የተደረገው ሥርዓት ቅሬታ እና ጥቆማ ማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ሥርዓቱንም የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ዓይናለም ንጉሴ እና የሚኒስቴሩ የኢ-ዳታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳዊት ውብሸት ይፋ አድርገዋል፡፡

ስርዓቱ ይፋ የተደረገው ተቋሙ የሙስና እና የብልሹ አሰራር መከላከል ልዩ የንቅናቄ እቅድ ውይይት ማጠቃለያ እና የተቋሙ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም የውይይት ባካሄደበት መድረክ ነው።

6844 ነፃ የጥሪ መስመር እና ጥቆማ ማቅረቢያ ስርዓት ማንኛውንም የገቢውን ዘርፍ አሠራሮችን በተመለከተ ጥቆማ መቀበል የሚያስችል መሆኑን የሚኒስቴሩ የመረጃ ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ኩራቱ ለማ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ሥርዓትም ባለጉዳዮች በተቋሙ ሰራተኞች ሥነ-ምግባር ላይ ወይም በማንኛውም አገልግሎት ላይ ቅሬታ ሲኖራቸው በነጻ የሚያቀርቡበት መንገድ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

ባለጉዳዮች በዚህ ቁጥር ሲደውሉ የሥነ-ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት ሠራተኞችን በቀጥታ እንደሚያገኙ የገለጹት ዳይሬክተሩ በሥራ መደራረብ ምክንያት ስልኩ ባይነሳ ሠራተኞቹ ያልተነሳውን ጥሪ አይተው ወደ ባለጉዳዮች በመደወል ጥቆማውን መቀበል እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

ተገልጋዮች ይህንን አገልግሎት ሲጠቀሙ እራሳቸውን በማሳወቅ ወይም ሳያሳውቁ ቅሬታቸውን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ቅሬታው እንደቀረበ ለአቅራቢዎቹ መከታተያ ቁጥር ይሰጣቸዋል፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹም ይህንን ቁጥር ተጠቅመው የቅሬታቸውን ሂደት መከታተል ይችላሉ ብለዋል፡፡

ሌላኛው ይፋ የተደረገው የቅሬታ ማቅረቢያ ፖርታል ነው፡፡ ይህ ሥርዓት ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽንን በተመለከተ የተለያዩ ቅሬታዎችን ማቅረብ ያስችላል፡፡

በዚህ ሥርዓት የግብር ማስያዣን በተመለከተ፣ የዘገየ ተመላሽ ገንዘብ፣ ኢ-ፍትሃዊ ቅጣቶች፣ የምዝገባ ጉዳዮች፣ የሁለቱን ተቋማት አጠቃላይ አሠራሮችን እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች ላይ ያሉ ቅሬታዎች መቅረብ እንደሚችሉ አቶ ኩራቱ ገልጸዋል፡፡

በሽመልስ ሲሳይ
ፎቶ:- የትናየት እንዳያፍሩ
❤1