M.O.R East Addis Ababa Branch
25.8K subscribers
6.66K photos
18 videos
659 files
392 links
East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for collecting revenue from customs duties and domestic taxes.
Download Telegram
👍7❤2
ስኬት በትክክለኛ አመራር በስትራቴቴጂካዊ አስተሳስብ ፣በትብብር ፣በተነሳሽነት በውጤታማ ውሳኔ ላይ ይመስርታል።’’ ወ/ሮ ወርቅዓለም ተሾመ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራ አስኪያጅ
---------------------------------
ህዳር 7/2019 ምስራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በዛሬው እለት ከወትሮ ለየት ባለመልኩ የማኔጅመንቱ አባላትን ከፍተኛ አመራሩር ፣የስራ ሂደት እንዲሁም ቡድኖችንና ከተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለሙዎችን ይዞ የ2019 የአራት ወር አፈጻጸም ለመገምገምና ለአመራሩ አቅም ግንባታ የሚሆን የግንዛብዬ ማስጭበጫ ስልጠና እንዲያገኝ በማለት በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ ተገኝቷል።
ይሕንንም በማስመ ልከት ወ/ሮ ወርቅዓለም ተሾመ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልእክታችው ስኬት በትክክልኛ አመራር በስትራቴቴጂካዊ አስተሳስብ ፣በትብብር ፣በተነሳሽነት በውጤታማ ውሳኔ ላይ ይመስርታል፣አመራር ማለትም ትእዛዝ ከመስጠት ባሻገር አቅጣጫ ማሳየት ለስራው ማነሳሳት ችግሮችን በአግባቡ በመፍታት የጋራ ወጤት ማምጣት ይጠይቃል ፣ከአመራሩም ይሕ ይጠብቃል ብለዋል ።
ጠንካራ ተቋም የሚገነባው በብቃት በተነሳሽነት ፣በትብብርና በቁርጠኝነት በሚሰሩ አመራሮችና ሰራተኞች በመሆኑ የሚሰጠውን ስልጠና በአግባብ እንዲሰልጥኑ በማሳስብ ሰልጠናወን በይፋ አስጀምረዋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ የአእምሮ ውቅር /Mindset / በሚል ርእስ በፕሮፌሰር ያለው እንዳወቀ በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ አዘጋጅነት ተሰጥቷል።
በቀጣይ ሁለት ቀናት በዚህ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል ።
❤9👍1😁1