M.O.R East Addis Ababa Branch
25.8K subscribers
6.66K photos
18 videos
659 files
392 links
East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for collecting revenue from customs duties and domestic taxes.
Download Telegram
ተጨባጭ ዕውቀቶችን በመጠቀም፣ ትክክለኛ የአመራር ባህሪያትን በማላበስና የተቋሙን የሥራ ባህል በማስጠበቅ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይገባል  / ወ/ሎ ወርቅዓለም ተሾመ የቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሾል አስኪያጅ
....
ኅዳር 9/2019 ዓ.ም (ምሥራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት)

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የማኔጅመንት አባላትን፣ የሥራ ሂደትና የቡድን መሪዎችን እንዲሁም ከተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለሙያዎችን በመያዝ፤በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመገኘ ለአመራሩ አቅም ግንባታ የሚሆን ሥልጠና  ማለትም የዓዕምሮ ውቅር፣ስትራቴጂክ ማኔጀመንት ፣ውሳኔ ሰጭነት እንዲሁም ተቋማዊ ባህል ምንነትን በተመለከተ ዝርዝር  የስልጠና ሰነዶችን እንዲወስዱ አድርጓል ።
በተያያዘም የ2019 ዓ.ም የአራት ወር ዕቅድ አፈጻጸምን እና የጥቅምት ወር ዕቀድን  መገምገም ችሏል።
በመድረኩ የዕቅድና በጀት አፈጻጸም ክትትል ቡድን አስተባባሪ አቶ ገንዘብ መካሻ የአራት ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በአራት ወራት ውስጥ 1.26 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 1.36 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ እንደሆነ እና ይህም 108.58% አፈጻጸም መሆኑን አሳይተዋል። ከተሰበሰበው አጠቃላይ 1.36 ቢሊዮን ብር ውስጥ 842.43 ሚሊዮን ብር ከቀጥታ ታክሶች፣ 491.29 ሚሊዮን ብር ከቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እንዲሁም 30.55 ሚሊዮን ብር ከታክስ ውጭ ካሉ ገቢዎች የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል።
የሪፖርቱን መቅረብ ተከትሎ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወርቅዓለም ተሾመ ያወያዩ ሲሆን፤ የሥራ ዲሲፕሊንን ማጠናከር፣ የኦዲት ግኝቶችን መቀነስ፣ የሥነ-ምግባር ጥሰቶችንና ብልሹ አሠራሮችን መከላከል፣ የግብር ከፋዮችን ቅሬታ መቀነስ፣ የውሳኔ ጥራትን ማሻሻል እንዲሁም በመንግሥትና በተቋም ደረጃ የተሰጠ ኃላፊነትን በአግባቡና በተጠያቂነት መወጣት እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል።
ከሥልጠናው ጋር በማያያዝም ባለፉት ሦስት ቀናት ከተሰጠው ሥልጠና የተገኙ ተጨባጭ ዕውቀቶችን በመጠቀም፣ ትክክለኛ የአመራር ባህሪያትን በማላበስና የተቋሙን የሥራ ባህል በማስጠበቅ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አጽንኦት ስጥተዋል ።
ወ/ሮ ወርቅዓለም በቀጣይ ሊሠሩ የሚገባቸውን የሥራ አቅጣጫዎች አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት፤ የተጀመረውን መልካም አፈጻጸም በማጠናከር፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ በመፍታት፣ ዕድሎችን በአግባቡ በመጠቀምና በጠንካራ የቡድን መንፈስ የዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት ጠንክረን እንሠራለን ብለዋል።
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጆችና የሥራ ኃላፊዎች በተነሱ ሐሳቦች ላይ ምላሽ በመስጠት የዓመቱን ዕቅድ ለማሳካትም ሆነ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል። ሥልጠናው በአገልግሎት አሰጣጡም ሆነ በገቢ አሰባሰቡ ላይ የሚያመጣው የባህሪ ለውጥ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው የተገኙትን ዕውቀቶች በተግባር ላይ እንደሚያውሉ ተናግረዋል።
❤5👍1