ንፅህናው የተረጋገጠ ውብ አካባቢ፣ ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ ለመገንባት ምቹ መደላድል ይፈጥራል!
ከተማችን ከጥቂት ዓመታት በፊት በንፅህናቸው ጎላ ብለው የሚታዩ ሰፈሮች ብዙም አልነበሯትም፡፡ በመሀል ከተማ ጭምር ከአስፋልት ገባ ሲባል የቆሻሻ ክምሮችን፣ ባልተገባ መልኩ መፀዳጃ የሆኑ ቦታዎችን ማየት የተለመደ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
በተለይም የወንዝ ዳርቻ አካባቢዎች ደግሞ በዘፈቀደ ይጣል በነበረው ደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻ ምክንያት የነዋሪዎችን ህይወት አወሳስበው ቆይተዋል፡፡
በአካባቢ ንፅህና ጉድለት የሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎች በተደጋጋሚ ሲከሰቱባት የቆየችው መዲናችን የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷን የሚመጥን መልካም ገፅታ አልነበራትም፡፡
ህፃናት በምቾት የሚያድጉባት፣ ወጣቶች ብሩህ ነገአቸውን የሚገነቡባት፣ የሀገር ባለውለታ አረጋውያን ጤናማ ህይወት የሚኖሩባት፣ ኢትዮጵያውያን የሚኮሩባት፣ አፍሪካዊያንም በተምሳሌትነት የሚጠቅሷት ውብ ከተማ ለማድረግ በተያዘው ግልፅ አቅጣጫ መዲናችን በአዲስ የለውጥ ምህዋር ውስጥ ትገኛለች፡፡
አዲስ አበባ አሁን ላይ በጥልቅ ጉስቁልናዋ የምትቆዝም፣ በቆሻሻ ክምር እና በመጥፎ ሽታ የምትሳቀቅ ከተማ አይደለችም፡፡ ንፅህናን ከውበት ጋር መለያዋ እያደረገች እንደ ስሟ ውብ አበባ መሆን የጀመረችው መዲናችን በተምሳሌትነት የምትጠቀስ የተሞክሮ ማዕከል ወደመሆን ተሸጋግራለች፡፡
በተለወጠ አስተሳሰብ እየተመራች፣ የዳበረ የስራ ባህልን መለያዋ ያደረገችው መዲናችን ለአፍሪካ መቀመጫነት አትመጥንም የምትባልበትን የታሪክ ስብራት ተሻግራለች፡፡
በፈጣን ዕድገቷ የስዕበት ማዕከል መሆን የጀመረችው ከተማችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ብቻም ሳትሆን በተለያዩ ስኬቶች ከበርካታ የዓለም ከተሞች ጋር ተወዳድራ የምትሸለም ሆናለች፡፡
አዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት UN-Habitat በቻይና ያዘጋጀውን የ2026 እ.ኤ.አ የዓለም ከተሞች ቀን “የሸንሃይ አዋርድ” ሽልማት አሸናፊ መሆኗም ተጨባጭ ስኬቶቿን ብቻም ሳይሆን ብሩህ ነገዋን አመላካች ነው፡፡
አረንጓዴ ልማቷን ከ2 ነጥብ 8 በመቶ ወደ 23 በመቶ በማሳደግ፣ በተለይም በኮሪደር ልማት እና በወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮግራሞች የከተማችንን ንፅህና በማረጋገጥ፣ ውበቷን ከፍ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት የህዝባችንን ጤናማ ህይወት ከማስጠበቅ ባሻገር፣ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እንድታሸንፍም ጉልህ ድርሻ ማበርከት ችለዋል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
#aa_prosperity

አዲስ አበባ ፤ በዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት መድረኮች ተከታታይ እውቅና እያገኘች ያለች ከተማ!
ከተማን መለወጥ የሚቻለው በግልጽ ራዕይ፣ በተቀናጀ ጥረትና የሰው ልጅን ሕይወት ማዕከል ባደረገ የልማት አቅጣጫ ነው። አዲስ አበባም ይህንን እሳቤ በተግባር እየተረጎመች መሆኗን በዓለም አቀፍ መድረክ ዳግም አስመስክራለች።
በቅርቡ በቻይና ሻንሃይ ከተማ በተካሄደው የ2026 የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማት ውድድር፣ አዲስ አበባን ጨምሮ አምስት ከተሞች ተሸላሚ ሆነዋል።
በዘንድሮው የሻንሃይ ሽልማት እውቅና ያገኙት፦
1. አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ)
2. ሳንቲያጎ ዴ ካሊ (ኮሎምቢያ)
3. ኢስታንቡል (ቱርኪዬ)
4. ጂንግዴዠን (ቻይና)
5. ካቶቪስ (ፖላንድ) ናቸው።
ይህ ሽልማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአራተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዲስ አበባ በአራቱ ዙሮች ሁለት ጊዜ እውቅና አግኝታለች። በ2024 የሴኡል ስማርት ሲቲ ሽልማትን፣ በ2026 ደግሞ የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማትን አግኝታለች።
ከዚህ በተጨማሪ፣ በ2023 አዲስ አበባ በምገባ ፕሮግራምና በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዘርፎች ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች ያለች ከተማ በመሆኗ ዓለም አቀፍ እውቅናና ሽልማት አግኝታለች።
ይህ እውቅና ለሀገራችን ታላቅ ክብር ከመሆኑም በላይ፣ እየሠራን ላለነው ሥራ ብርታትና ተጨማሪ ተነሳሽነት የሚሰጥ ነው። ከሁሉም በላይ፣ በከተማችን የምንተገብራቸው ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃና የአኗኗር ሁኔታ ለማሻሻል የምናደርገው ጥረት፣ እንዲሁም የከተማዋን የተፈጥሮና ማኅበራዊ ፀጋዎች ወደ ልማትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የመቀየር ሥራችን ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የሚያረጋግጥ ዓለም አቀፍ ምስክርነት ነው።
የመደመር እሳቤያችንም ልማትን ከሰው ሕይወትና ደኅንነት ጋር አጣምሮ ያያል። ከተሞች የሥልጣኔ መገለጫ እንዲሆኑ፣ ያላቸውን ፀጋዎች በመለየትና በማልማት፣ የሰውን አቅም ከተፈጥሮና ከኢኮኖሚያዊ ሀብቶች ጋር በማቀናጀት ለጋራ ብልፅግና መሥራትን ይጠይቃል።
በከተማችን የልማት ጉዞ እስካሁን የተጓዝነው ርቀት ጠንካራ መሠረት የጣለ ቢሆንም፣ የሚቀረን ረጅም ጉዞ እንዳለ እናውቃለን። ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዘመናት ከተጫኗት ድህነትና ልዩ ልዩ ችግሮች በዘላቂነት ለመላቀቅ፣ ቀጣይነት ያለው ለውጥ ለማምጣትና ወደ ብልፅግና ለመሸጋገር የጀመረችው ጉዞ ፍሬ እያፈራ ይገኛል። ሆኖም ይህንን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ወደ ተሟላና ዘላቂ ለውጥ ለመቀየር የሁሉንም ዜጎች ርብርብ፣ ቁርጠኝነትና ተሳትፎ ያስፈልጋል። ስለሆነም ሁላችንም ለለውጡ በቁርጠኝነት መትጋት ይገባናል።
ያገኘነውን ዓለም አቀፍ እውቅናም እንደ መዳረሻ ሳይሆን፣ እንደ ተጨማሪ ኃላፊነትና ለበለጠ ሥራ ማበረታቻ እንወስደዋለን።
ይህንን ተነሳሽነት በመያዝ፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች የሥልጣኔና የብልፅግና መሠረት እንዲሆኑ እንሠራለን። አቅሞቻችንን በመደመር፣ ፀጋዎቻችንን ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር፣ ክብራችንን የሚመጥን የብልፅግና ግብ ለመድረስ ትጋታችንን እናጠናክራለን።
ከተሞቻችን የመደመር ሥልጣኔ መዳረሻ፣ ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ተስማሚ የኑሮ አካባቢ፣ ለቀጣዩ ትውልድም ዘላቂ የብልፅግና ውርስ እንዲሆኑ በጋራ እንሠራለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የመደመር እይታ ለሀገራዊ ከፍታ! ለዲፕሎማሲያችን እመርታ!
ኢትዮጵያ እየተመራችበት ያለው የመደመር ፅንሰ-ሐሳብ ከራሳችን ሀገራዊ እውነታ እና ከሀገር ውስጥ ፍላጎቶች የመነጨ ነው፡፡ ሀገራችን የነበረችበትን ተበታትኖ የመቆም ፈተና እና ውስብስብ ችግሮች በጥልቀት በመተንተን ዘላቂ መፍትሔ መትለም አስችሏል፡፡
የህዝባችንን እሴቶች፣ የሀገር ውስጥ ልምዶችን፣ ባህሎችን እና እውቀቶችን ከዘመናዊው ዓለም አቀፍ እውቀትና ቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀቱ የመደመር ፍልስፍና ለሀገራችን ሁለንተናዊ ጉዞ ተስማሚና ውጤታማ መሆኑ በተግባር ተረጋግጧል፡፡
የመደመር እይታ ቀደም ሲል የተሰሩ መልካም ስራዎችን የመካድ ወይም የመደምሰስ አመለካከት የሌለው ይልቁንም ባለፉት ዓመታት በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካው ዘርፍ የተመዘገቡ አዎንታዊ ውጤቶችንና ድሎችን ጠብቆ የሚያስቀጥል፣ ከትናንት ወረቶች ላይ አዳዲስ ድሎችን በመጨመር ሀገራችንን ወደ ከፍታ ምዕራፍ የሚያሸጋግር አካታች እሳቤ ነው፡፡
ስኬቶችን አልቆ ከማስቀጠል ባሻገር ትናንትን በቅንነትና በግልጽነት በመገምገም በሂደት ያጋጠሙ ጥፋቶችንና ስህተቶችን እያረሙ መጓዝ ግድ ይላል። እንደ ሀገር ሲያጋጥሙ የቆዩ ስህተቶች እንዳይደገሙ በማድረግ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራርን መገንባት የመደመር እሳቤ ዋና ዓላማ ሲሆን፣ ሀገራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በላቀ ፍጥነት ወደፊት እንድንራመድ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር ችሏል።
የመደመር እሳቤ ዋና ግብ በየዘመኑ ሲከማቹ የቆዩ ችግሮች መፍታት ብቻ ሳይሆን፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን በማድረግ የመጪውን ትውልድ ሁለንተናዊ ፍላጎትና ጥቅም በማረጋገጥ ነገን ዛሬ መገንባት ነው፡፡
የመደመር እሳቤ አብሮ ማደግን፣ ቀጠናዊ ትስስርን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚያበረታታ ዘመኑን የዋጀ ተራማጅ እይታ ነው፡፡ የሀገራችንን ውስብስብ ችግሮች እየፈታ ለአፍሪካ ጭምር የተስፋ ብርሀን እየፈነጠቀ የሚገኘው ሀገር በቀሉ የመደመር ፍልስፍና ዲፕሎማሲያዊ አቅማችንንም ከፍ እያደረገ ይገኛል፡፡
የመደመር መንግስት ፍኖተ ካርታ የሆነው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ‹‹መደመር›› መፅሀፍ ከሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ባሻገር በእንግሊዘኛ፣ በአረብኛ፣ በቻይንኛ፣ በሩሲያኛ እና በመሳሰሉት ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች እየተተረጎመ መሆኑ የኢትዮጵያ ተፅዕኖ ፈጣሪነት አቅም እያደገ መምጣቱንም ማሳያ ነው፡፡

የመዲናችን ሁሉን አቀፍ ዕድገት የእሳቤ ጥራትና የተግባር ቁርጠኝነት ውጤት ነው!
አቅምን በደመረ፣ ፀጋዎችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ባዋለ፣ ነገን አሻግሮ በተመለከተ ግልፅ እሳቤ በገበታ ለሸገር ፕሮጀክት መሰረቱ የፀናው አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ የማድረግ ውጥናችን ፍሬያማ በመሆኑ፣ መዲናችን ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ተምሳሌታዊነቷ ሰፍቷል፡፡
ግዙፉን የአድዋ ድል መታሰቢያ ጨምሮ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል፣ ግዙፍ የገበያ ማዕከላት፣ ግዙፍ ሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ በየክፍለ ከተማው የተገነቡ የፀጥታ ተቋማት፣ የውሃ መሰረተ ልማቶች እና ሌሎችም ግዙፍ የልማት ነጠብጣቦች በመንገድ መሰረተ ልማቶች እየተሳሰሩ የከተማችንን አዲስ ገፅታ መግለጥ ችለዋል፡፡
ለከተማችን ፈጣን ዕድገት ማርሽ ቀያሪ ሆኖ የተከሰተውና ተሞክሮው በሁሉም የሀገራችን ከተሞች እየሰፋ የሚገኘው የኮሪደር ልማትም የመዲናችንን የከፍታ ጉዞ እያፋጠነው ይገኛል፡፡
የመፍጠር እና የመፍጠን መርሀችን አካል የሆነው የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም የነዋሪዎቻችንን ህይወት ከማሻሻል ባሻገር መዲናችንን ውብ ገፅታ በማላበስ የቱሪስት መዳረሻነቷን አሳድጓል፡፡
የከተማ መልሶ ግንባት ስራዎች በተለይም በውሃ፣ በመንገድ፣ በቴሌ፣ በመብራት እና በሌሎችም ተቋማት የቅንጅት ክፍተት ምክንያት ሲፈጠሩ የቆዩ የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችንም እየቀረፉ እንደሚገኙ መረዳት ይቻላል፡፡
አካባቢን የማልማት፣ ከተማን የመገንባት፣ ሀገርን የማሳደግ፣ ህዝብን ፍትሀዊ ተጠቃሚ የማድረግ የብልፅግና ፓርቲ አሻጋሪ እሳቤዎች ልቀው እንዲተገበሩ የመደመር መንግስት አበክሮ እየተጋ ሲሆን፣ ህዝባችንም ሁሉን አቀፍ ተሳትፎውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ከውጭ ነዳጅ ጥገኝነት ወደ ሀገር ውስጥ ሀብት አጠቃቀም፤ የመደመር መንግስት የከተማ ልማት አዲስ ምዕራፍ!
በአዲስ አበባ የተጀመረው ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተሸጋገሩ የከተማ አውቶቡሶችን ወደ ሥራ ማስገባት ተራ የትራንስፖርት ለውጥ ብቻ አይደለም።
በመደመር መንግሥት የልማት ዕይታ ውስጥ ሲታይ፣ የሀገርን ሀብት ወደ ሕዝብ ተጨባጭ ጥቅም የመቀየር፣ የኢኮኖሚ ነፃነትን የማጠናከር፣ የቴክኖሎጂ አቅምን የማሳደግና ሰው ተኮር የከተማ ልማትን የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው።
በጥቅምት 22 ቀን 2019 የመጀመሪያዎቹ 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተቀየሩ አውቶቡሶች ወደ አገልግሎት ገብተዋል። 400 ተጨማሪ አዳዲስ የጋዝ አውቶቡሶችም እንደሚመጡ ተገልጿል። ይህ ለውጥ ከሚያመጣቸው የታሪፍ፣ የወጪና የአካባቢ ጥቅሞች ባሻገር ትልቅ የልማት ትርጉም አለው።
በመደመር መንግሥት ዕይታ ለከተማዋና ለሕዝቡ ያለውን ትርጉም ዋና ዋና ነጥቦች ስንመለከት:-
👉 የሀገርን የተፈጥሮ ፀጋዎችን ወደ ሕዝብ ተጨባጭ ጥቅም መቀየር!
ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቶች ያሏት ሀገር ናት። ነገር ግን የሀብት መኖር ብቻውን ልማት አያመጣም፤ ዋናው ጉዳይ ያለንን ሀብት ወደ ምርታማነትና የሕዝብ ጥቅም መቀየር ነው።
በጎዴ የሚመረተውን የተፈጥሮ ጋዝ ወደ መዲናዋ በማምጣት፣ በከተማ ትራንስፖርት ውስጥ መጠቀም መቻሉ የዚህ ሀሳብ ተግባራዊ ማሳያ ነው።
ይህም ሀገራችን ከተፈጥሮ ፀጋዎቿ ተጠቃሚ ብቻ ሳትሆን፣ ፀጋዎቿን በመጠቀም ለዜጎቿ የተሻለ ኑሮ መፍጠር እንደምትችል ያሳያል።
👉 የውጭ ምንዛሬ ጫናን መቀነስና የኢኮኖሚ ነፃነትን ማጠናከር!
የነዳጅ ግዢ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ ከሚያስከትሉ ዘርፎች አንዱ ነው። የከተማ አውቶቡሶች በአገር ውስጥ በሚመረት የተፈጥሮ ጋዝ መንቀሳቀሳቸው ከውጭ የሚገባ ነዳጅ ላይ ያለንን ጥገኝነት ለመቀነስ ያግዛል።
ይህም ማለት፦
- ለነዳጅ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ መቆጠብ፤
- የሀገር ውስጥ ሀብትን ለምርታማ ዘርፎች ማዋል፤
- በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መዋዠቅ ምክንያት የሚፈጠርን የኢኮኖሚ ጫና መቋቋም፤
- የሀገርን የኢኮኖሚ መቋቋም አቅም ማጠናከር ማለት ነው።
ይህም እንደ ሀገር የተጀመሩ የራሳችንን ሀብት ተጠቅመን የራሳችንን የኢኮኖሚ ጫና የመቀነስ ጉዞ የሚያጠናክር ነው።
👉 በዜጎች ላይ ሊደርክ የሚችል ተፈጥሮዋዊና ሰው ሰራሽ ጫናዎችን መቀነስ!
የትራንስፖርት ወጪ የከተማ ነዋሪዎችን ዕለታዊ የኑሮ ወጪ ከሚወስኑ ነገሮች አንዱ ነው።
የአውቶቡስ የሥራ ማስኬጃ ወጪ ሲቀንስ ይህ በትክክል ወደ ተጠቃሚው ከተላለፈ፣ ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎት ያገኛሉ።
የከተማ ልማት ማለት መንገድ፣ ሕንፃና ድልድይ መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎች በንጹህ አየር፣ በጤናማ አካባቢና በተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖሩ ማስቻልም ነው።
ከናፍጣ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ መሸጋገር የተሽከርካሪዎችን የተወሰኑ የአየር ብክለት አመንጪ ጋዞችና ቅንጣቶች ለመቀነስ ያግዛል።
በዚህም፦
- የአየር ብክለትን መቀነስ፤
- ለከተማ ነዋሪዎች ጤናማ አካባቢ መፍጠር፤
- የአረንጓዴ ከተማ ግንባታን ማጠናከር፤ እና
- የከተማን የአካባቢ ዘላቂነት ማሳደግ ማለት ነው።
እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች ከናፍጣ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ መሸጋገር ወደ ዘላቂ የኃይል አጠቃቀም የሚወስድ ጠቃሚ የሽግግር እርምጃ ነው።
👉 የሀገር ውስጥ አቅምን፣ ቴክኖሎጂንና እውቀትን ማሳደግ!
ከዚህ ፕሮጀክት ትልቅ ትምህርት የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝን ማምረት ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊ ጥቅም ማዋል የሚያስችል ቴክኖሎጂና አቅም መገንባት መቻልን ነው።
ጋዙን ከማምረቻ ቦታው ወደ አዲስ አበባ ማጓጓዝ፣ የጋዝ ማደያዎችን መገንባት፣ አውቶቡሶችን ማስተካከልና በሀገር ውስጥ የሰው ኃይል ሥራውን ማከናወን አዲስ የእውቀትና የቴክኖሎጂ አቅም ይፈጥራል። ይህም በሀገራችን ልጆች ሆኖ ታይቷል፤ ትልቅ ስኬትም ነው።
ይህ በቀጣይ ለሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችም የሚስፋፋ አቅም ነው። የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን ማብቃት፣ የቴክኒክ እውቀትን ማስፋፋት፣ የጥገናና የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪን ማጠናከር ያስችላል።
👉 የመደመር መንግሥት የልማት ጉዞን በተግባር ማሳየት!
የመደመር ዋና መርህ ያሉንን ሀብቶች፣ አቅሞች፣ እውቀቶችና የልማት እድሎች አቀናጅቶ ለጋራ ዓላማ ማዋል ነው።
ይህ ፕሮጀክትም በዚሁ ዕይታ ሲታይ በተለያዩ ዘርፎች ያሉ አቅሞችን አቀናጅቶ ውጤት የማምጣት ተግባራዊ ማሳያ ነው።
- የኢነርጂ ዘርፍ የሚያመነጨው ሀብት፤
- የትራንስፖርት ዘርፍ የሚያቀርበው አገልግሎት፤
- የቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚያመነጨው መፍትሔ፤
- የሰው ኃይል የሚያበረክተው እውቀት፤
- የመንግሥት ተቋማት የሚያደርጉት ቅንጅት።
እነዚህ ሲዋሃዱ የአንድ ዘርፍ ስኬት ብቻ ሳይሆን የሀገር አጠቃላይ የልማት አቅም ይጠናከራል።
👉 አዲስ አበባን አለም አቀፍ ተወዳዳሪና ዘመናዊና ከተማ ማድረግ!
አዲስ አበባ የሀገሪቱ መዲና ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ማዕከል ናት። ስለዚህ የከተማዋ የትራንስፖርት ሥርዓት ዘመናዊ፣ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው፣ ቀልጣፋና አካባቢን የሚጠብቅ መሆን አለበት። ይህንንም ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።
የተፈጥሮ ጋዝ አውቶቡሶች መግባት ከኤሌክትሪክ አውቶቡሶች፣ ከቀላል ባቡር፣ ከዘመናዊ የአውቶቡስ መስመሮችና ከእግረኛ ተስማሚ የከተማ መሠረተ ልማቶች ጋር በተቀናጀ መልኩ ሲዳብር አዲስ አበባን የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ያላት ከተማ ያደርጋታል።
አዲስ አበባን የብልፅግና ማሳያ ከተማ የማድረጉ ሂደት ከዚህም በላይ ጎልቶ ይቀጥላል።