Prosperity Party A.A - ብልፅግና
11.1K subscribers
5.87K photos
371 videos
5 files
431 links
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት
Download Telegram
ኢኮኖሚያችን አይበገሬ ሆኖ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን እንዲቋቋም፣ ቀድሞ መዘጋጀትና አማራጮችን ማስፋት የግድ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#aa_prosperity
የመደመርን የአብሮነት እሴት በመላበስ፣ እሳቤውን አልቆ በመተግበር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና እናረጋግጥ!

ሀገር በቀሉ የመደመር እሳቤ ኢትዮጵያ ያሏትን በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ሰው ሰራሽ ጸጋዎች በአግባቡ በመጠቀም ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ የተቀየሰ ሁለንተናዊ የለውጥ መንገድ ነው። ይህ ዕሳቤ አዎንታዊ እሴቶቻችንን በመጠበቅ፣ የነበሩ ግድፈቶቻችንን በማስተካከልና አዳዲስ የፈጠራ እይታዎችን በመጨመር የሚጓዝ ተራማጅ እሳቤ ነው።

በአካልም፣ በአዕምሮም፣ በስነ ምግባርም ጤናማ ትውልድ ለመገንባት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥረው ይህ አካታች እሳቤ የታሪክ ስብራቶችን በማረም ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከበረችና የበለጸገች ተምሳሌት ሀገር ለማድረግ ያለመ ታላቅ ሀገር በቀል ፍልስፍና ነው።

የመደመር አስተሳሰብ ዋና መሠረቱ የህዝቦቻችን አንድነት፣ ትብብርና አብሮነት ሲሆን፣ ልዩነቶቻችንን እንደ ውበትና እንደ ጥንካሬ በመቁጠር፣ በጋራ ልማትና በጋራ ሰላም ላይ በጽናት እንድንቆም ያደርገናል።

በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚውና በማህበራዊ ዘርፎች የሚስተዋሉ ጤናማ ያልሆነ ተፎካካሪነትንና መገለልን በማስወገድ፣ በምትኩ አሳታፊነትንና እኩልነትን ያበስራል። በተደመረ አቅም እያንዳንዱ ዜጋ ለሀገሩ ዕድገት የድርሻውን አወንታዊ አስተዋጽኦ ሲያበረክት፣ የህዝባችን የመከወን አቅም ይጎለብታል፤ የጋራ ዕድገቱም በእጅጉ ይፋጠናል፡፡

በመደመር እሳቤ መሪነት በመላ ሀገሪቱ እየተከናወኑ በሚገኙ አካታች ሁለንተናዊ ልማቶች ታሪካዊ ስብራቶቻችን እየተጠገኑ፣ የህዝባችን የኑሮ ደረጃ እየተሻሻለ፣ የሀገራችን ከፍታም እየተበሰረ ይገኛል፡፡

በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ የሚገኘው የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ተስፋ ሰጪ ጥረት፣ የኢትዮጵያን መራቆት እያስቀረ ልምላሜዋን እያበሰረ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የመደመር እሳቤ አተገባበር ቱሩፋቶች ናቸው፡፡

መዲናችን ከጥልቅ ጉስቁልና በመውጣት ወደ ተምሳሌትነት እያደረገች ያለው ሽግግር፣ የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ የበርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶች እውን መሆን፣ በዲፕሎማሲው እና በሌሎችም እየተመዘገቡ የሚገኙ ተጨባጭ ድሎች የእሳቤዎቻችን ጥራት ማሳያ፣ የተደመረ አቅማችን ማብሰሪያ መሆናቸውንም መረዳት ይቻላል፡፡

የመደመርን የአብሮነት እሴት በመላበስ፣ እሳቤውን አልቆ በመተግበር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ታሪካዊ አሻራን ማሳረፍ ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
#aa_prosperity
አዲስ አበባ፡ የአህጉሪቱ የጋራ ተስፋና የጋራ ዕጣ ፈንታ የሚመከርባት መድረክ ናት!

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መዲና ብቻ ሳትሆን፣ የአፍሪካውያን የጋራ መዲና፣ የአህጉሪቱ የውይይት፣ የትብብር፣ የዲፕሎማሲና የጋራ መፍትሔ ማመንጫ ማዕከል እየሆነች መጥታለች።

በመደመር መንግሥት የከተማ ልማት ዕመርታ፣ አዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ያስመዘገበቻቸው የልማት ስኬቶች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ዓለም አቀፍ የመዳረሻነት አቅሟን ከፍ አድርገዋል።

የተሻሻሉ መሠረተ ልማቶች፣ ዘመናዊ የከተማ ኮሪደሮች፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች፣ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች፣ የመንገድና የትራንስፖርት አውታሮች፣ የመዝናኛና የቱሪዝም መስህቦች ከተማዋን ውብ፣ ምቹ፣ ዘመናዊና ለዓለም አቀፍ ኩነቶች ተመራጭ ማዕከል እያደረጉዋት ነው።

ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የቢዝነስ ማኅበረሰቡ፣ የባለሀብቶች፣ የቱሪስቶችና የልማት አጋሮች መገናኛ ስፍራ ከመሆን ባለፈ፣ የአህጉሪቱ የጋራ ተስፋና የጋራ ዕጣ ፈንታ የሚመከርባት መድረክ ናት።

ይህም የኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማሳደግ፣ የከተማዋን ኢኮኖሚ በማነቃቃት፣ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠርና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን በማጠናከር ረገድ ትልቅ አቅም ነው።

አድዋ የአፍሪካ አንድነት፣ ነፃነትና የጋራ የወደፊት ራዕይ ምልክት ነው። የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአዲስ አበባ፣ በታሪካዊው የጥቁር ሕዝቦች የድልና የነፃነት ምልክት በሆነው የአደዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ጉባኤ ማካሄዳቸው ከተራ የስብሰባ ቦታ ምርጫ በላይ ጥልቅ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና አህጉራዊ ትርጉም አለው።

አድዋ አፍሪካውያን በአንድነት፣ በጀግንነትና በራስ የመወሰን አቅም የቅኝ ግዛትን ምኞት ያከሸፉበት፣ ለጥቁር ሕዝቦችም የክብርና የኩራት ታሪካዊ መሠረት የጣሉበት የድል ታሪክ ነው።

ዛሬ በዚሁ ታሪካዊ ሥፍራ የአፍሪካ የፖለቲካ ኃይሎች መሰባሰባቸው፣ ያለፈውን የጋራ ድል በማስታወስ የአህጉሪቱን የጋራ ፈተናዎች በውይይት፣ በመግባባትና በትብብር ለመፍታት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል።

ይህም አዲስ አበባ የአፍሪካ የነፃነት ታሪክ መዲና ብቻ ሳትሆን፣ የፖለቲካ ውይይት፣ የአህጉራዊ መግባባት፣ የጋራ መፍትሄና የተባበረ የወደፊት ራዕይ ማዕከል መሆኗን የሚያረጋግጥ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።

አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስና ውብ እየሆነች፣ የታሪክና የባህል እሴቶቿን ከዘመናዊ የከተማ ልማት ጋር አጣምራ፣ ለፖለቲካዊ፣ ለዲፕሎማሲያዊ፣ ለኢኮኖሚያዊ፣ ለባህላዊ፣ ለሳይንሳዊና ለስፖርታዊ ኩነቶች ተመራጭ ማዕከልነቷን እያጠናከረች ትገኛለች።

ይህ የከተማ ውበት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ አንድነትን፣ ትብብርንና የጋራ ብልጽግናን የሚያጎለብት ታላቅ ራዕይ ነው።

አዲስ አበባ፤ ሀገራት እና አለምአቀፍ ተቋማት የሚገናኙባት፣ የሚመክሩባት፣ የጋራ መፍትሔ የሚያፈልቁባት፣ ዓለም የሚሰበሰብባት የአፍሪካ የጋራ መዲና ናት!
#aa_prosperity
ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ጎን ለጎን በተዘጋጀው የሴቶችና ወጣቶች የፖለቲካ አመራር ሚና መድረክ ላይ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች

👉 ኢትዮጵያ ዉስጥ በፌደራል ደረጃ 50% የአመራር ቦታዎች በወጣቶች የተያዙና ወጣቶች የነገን ቀን ሳይጠብቁ ዛሬውኑ በፖለቲካው እየመሩ እንደሚገኙ፤

👉 በኢትዮጵያ 50% የካቢኔ ቦታዎች እና ከ40% በላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮች በሴቶች የተያዙ ሲሆን፣ ሴቶች የፖሊሲ ቀራጭነት ሚና እንዳላቸዉ፤

👉የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች በራሳቸው መዋቅር እና እጩዎች ውስጥ ወጣቶችን እና ሴቶችን እንደ እኩል የፖለቲካ አጋር ሊቀበሏቸው እንደሚገባ፤

👉ከአፍሪካ ህዝብ 60% በላይ የሚሆነው ዕድሜው ከ25 ዓመት በታች በመሆኑ ወጣቶች የአህጉሪቱ ትልቅ ማህበራዊ ሀብት መሆናቸዉ፣

👉አህጉሪቱ ግማሽ ህዝቧ የሆኑትን ሴቶች ወደ ጎን በመተው እና እያገለለች እምቅ አቅሟን እና ማህበራዊ ትስስሯን እዉን አድርጋ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ እንደማትችል፤

👉እንደ ግጭት እና የአየር ንብረት ለውጥ ያሉ ማህበራዊ ፈተናዎች ያለ ወጣቶች እና ሴቶች ንቁ ተሳትፎ ሊፈቱ አይችሉም፤

👉 ወጣቶች እና ሴቶች የልማት ወይም የዕርዳታ ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ የፈጠራ ባለቤቶች እና ስራ ፈጣሪዎች መሆን አለባቸው፤

👉በሴቶች እና ወጣቶች ስራ ፈጠራ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ለአፍሪካ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ሽግግር እና ቀጣይነት ያለው ልማት መሰረት መሆኑን፤

👉 የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ወጣቶችን በስራ እድል ፈጠራ እና በፈጠራ ስራዎች ማብቃት ወሳኝ እንደሚገባ

#aa_prosperity