በሁለንተናዊ መልኩ የስዕበት ማዕከልነቷን እያሳደገች የምትገኘው ፦ አዲስ አበባ!!
ከሀገር በቀሉ የመደመር ፍልስፍና የሚቀዱት የፓርቲያችን አሻጋሪ እሳቤዎች ኢትዮጵያን ከነበረችበት ውስብስብ ችግሮች እያወጡ የብዝሀ ዕድገት ተምሳሌት ሀገር አድርገዋታል፡፡
የትናንት ምንዳዎችን በማላቅ፣ ዕዳዎችን ደግሞ በማስወገድ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና የማረጋገጥ ግዙፍ ራዕይ ያነገበው ብልፅግና ፓርቲ ቃሉን በተግባር በመኖር ተጨባጭ ድሎችን አስመዝግቧል፡፡ በሀገር በቀሉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ኢትዮጵያ ከነበረችበት አረንቋ መውጣት የቻለችው በፓርቲያችን የጠራ እሳቤ ተመርታ ነው፡፡
የብዝሀ ዘርፍ የኢኮኖሚ ፕሮግራሞች ተግባራዊ በመደረጋቸው በግብርናው ዘርፍ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስንዴ ተመፅዋችነት ወደ ስንዴ ላኪነት ተሸጋግራለች፡፡ በአረንጓዴ ኢኒሸቲቭ፣ በበጋ መስኖ እና በሌሎችም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ግስጋሴ ፅኑ መሰረት ሆነዋል፡፡
ተፈጥሯዊ፣ ሰው ሰራሽ እና ታሪካዊ ፀጋዎች እያሏት ሳትጠቀምበት በቆየችው የቱሪዝም ዘርፍ የተመዘገቡ ድሎችን ለመረዳት አዲስ አበባን መመልከት በቂ ነው፡፡ የቱሪስት መሸጋገሪያ እንጅ የቱሪስት መዳረሻ ያልነበረችው መዲናችን አሁን ላይ ተምሳሌታዊ ጉዞዋን በማየት ተሞክሮዋን ለማስፋት የሚመኙ የሀገራት መሪዎች ጭምር ተበራክተዋል፡፡
በሁለንተናዊ መልኩ የስዕበት ማዕከልነቷን እያሳደገች የምትገኘው መዲናችን ባለፈው አንድ ዓመት ኢትዮጵያ ያዘጋጀቻቸውን ከ258 በላይ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በብቃት በማስተናገድ የዲፕሎማቲካ መናኸሪያነቷን በቃል ሳይሆን በተግባር መግለጥ ችላለች፡፡
በመዲናችን የጀመረው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ እየተካሄደበት የሚገኘው የአፍሪካዊያን ኩራት ግዙፉ የአድዋ ድል መታሰቢያ እና አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን የመሳሰሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶቿ ደግሞ የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከልነቷን ከፍ አድርገዋል፡፡
አዲስ አበባ በሜጋ ፕሮጀክቶቿ፣ በኮሪደር ልማቶቿ፣ በወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮግራሞቿ እና በሌሎችም ሰው ተኮር ልማቶቿ እያስመዘገበች የሚገኘው አንፀባራቂ ውጤት የኢትዮጵያን የተፅዕኖ ፈጣሪነት አድማስም ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡
በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በሌሎችም ኢትዮጵያ እያካሄደችው የሚገኘው የቴክኖሎጂ አብዮትም ቢሆን ፓርቲያችን ዘመኑን በመዋጀት ነገን ዛሬ ለመገንባት የነደፈው ትልም ማሳያ ነው፡፡
በማዕድን ዘርፍ፣ በኢንዱስትሪ ምርታማነት፣ ጤና እና ትምህርትን በመሳሰሉ ማህበራዊ ልማቶች እየተመዘገቡ የሚገኙ ስኬቶችም የኢትዮጵያን ተስፋ አለምልመዋል፡፡
የጋራ ዕድገትን እና የጋራ ተጠቃሚነትን ማዕከል ባደረገ እሳቤ ከሀገራት ጋር የጀመረቻቸው ብርቱ ጥረቶችም ኢትዮጵያ የምትመራበትን የመደመር ፍልስፍና ወደ ሌሎች ሀገራት ተደራሽ በማድረግ ጭምር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የተፈጥሮ ሀብቶቿን በራሷ አቅም አልምታ ለመጠቀም በያዘችው ቁርጠኛ አቋም በታሪክ አጋጥመዋት የማያውቁ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን ተቋቁማ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዕውን ማድረግ የቻለችው ሀገራችን ብሪክስን የመሳሰሉ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ስብስቦች አባል በመሆን ተፅዕኖ ፈጣሪነቷን አሳድጋለች፡፡
የሀገራችንን ከመጠላለፍ፣ ከግጭት እና ከጦርነት አዙሪት የማይወጣ ኋላቀር የፖለቲካ ባህል በመደመር እሳቤ በተቃኘ የዴሞክራሲ ባህል ለመተካት ዘርፈ ብዙ እርምጃዎችን የወሰደው ብልፅግና ፓርቲ ሀገራዊ አቅሞችን ለሀገራችን ዕድገት ማዋል ችሏል፡፡
ነፃ እና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማትን በመገንባት የዴሞክራሲ ምህዳሩን ማስፋት የቻለው ብልፅግና የትብብር እና የፉክክር ሚዛንን በመጠበቅ በሀሳብ የበላይነት ከሚያምኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ትውልድ ተሻጋሪ አሻራ ማሳረፍ የቻለ ግዙፍ ፓርቲ ነው፡፡
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ፣ የአፍሪካውያንን አብሮነት ለማጥበቅ፣ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የጠራ ራዕይ ያነገበው ፓርቲያችን የሀገራት መሪዎች፣ የፓርላማ አባላት፣ ሚኒስትሮች እንዲሁም ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ የፖለሪካ ፓርቲዎች ተወካዮች እየተሳተፉበት ለሚገኘው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤም ጉልህ ሚናውን ያበረክታል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
#aa_prosperity

ፓን አፍሪካኒዝም! በአዳዲስ እሳቤዎች በፓን አፍሪካ አዳራሽ!
አፍሪካ በአንዳንዶች ዘንድ ‹‹ጨለማው አህጉር›› በመባል በምትገለፅበት፣ አፍሪካዊያንም በተመሳሳይ ‹‹ያልሰለጠኑ ህዝቦች›› በመባል በሚጠሩበት ዘመን፣ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ጫፍ፣ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምዕራብ ጫፍ የህይወት መስዋዕትነት በከፈሉ አያቶቻችን፣ ኢትዮጵያ የነፃነት ቀንዲልነቷን አስጠብቃ ኖራለች፡፡
የኢትዮጵያውያን አይደፈሬነት በአድዋ ጦርነት ወቅት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ተዳፍሮ የገባውን ፋሽስታዊ ወራሪ ሀይል ድል በማድረግ ከተራራ የገዘፈ ህያው ታሪክ ፅፎ አልፏል፡፡
በአድዋ ጦርነት የተመዘገበው ድል ለአፍሪካ አህጉር እንዲሁም ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ብርሀን የለኮሰ የፓን አፍሪካኒዝም ሞተር መሆኑን ታሪክ ይነግረናል፡፡ የበፊቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አበባን መቀመጫው ያደረገበት አንዱ ምክንያትም ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካ ወንድም እህቶች በለኮሱት የተስፋ ብርሃን መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
ኢትዮጵያ በተምሳሌታዊነት ጉዞዋን አፍሪካውያን ለጋራ እድገት እንዲነሱ ዛሬም እንደ ትናንቱ የድርሻዋን እያበረከተች ትገኛለች፡፡
አፍሪካዊያን እና መላው ፍትህና ነፃነት ወዳድ ህዝብ ሁሉ የሚኮራበትን የአድዋ ድል መታሰቢያ እውን ያደረገችው መዲናችን ፓን አፍሪካን የሚል ስያሜ በያዘው ግዙፉ አዳራሽ 2ኛውን የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ እያካሄደች ትገኛለች፡፡
የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን እውን በማድረግ የተሟላ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ እያደረገች ያለው ዘርፈ ብዙ ርብርብም የአፍሪካዊያንን አብሮነት፣ ነፃነትና እና የጋራ ዕድገት ከፍ ለሚያደርገው የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ትልቅ አቅም ነው፡፡

ጉባኤው የአፍሪካ ገዢም ሆነ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለኢኮኖሚ ለውጥ እና ለዜጎች ህይወት መሻሻል ከፍ አድርገው እንዲሰሩ የሚያደርግ ነው።
ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)
የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር
#aa_prosperity
ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)
የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር
#aa_prosperity
“ለዕድገት መምራት” በሚል መሪ ቃል ዛሬ መካሔድ በጀመረው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በመገኘት ንግግር አድርጌያለሁ። የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ መድረክ ማስተናገዷ ለሁላችንም ታላቅ ኩራት ነው።
በመደመር እሳቤ እየተመራን፤ ሕዝባዊ አንድነትን፣ ተጠያቂነትንና አካታች አስተዳደርን ማረጋገጥ የፖለቲካ አመራር የዜጎችን ሕይወት እንዲያሻሽል የሚያስችሉ ወሳኝ መሠረቶች ናቸው። ይህም ፓርቲዎች ከምርጫ ውድድር ባለፈ አሻግረው እንዲመለከቱ፣ በመንግሥት ለውጦች የማይቀያየሩ፣ ብሔራዊና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ እና ለሀገር ጥቅም በጋራ እንዲሠሩ ይጠይቃል።
በሌላ በኩል፣ ተተኪው ትውልድ ኃላፊነቶችን እየወሰደ የሚያድግበትን ዕድሎችን እያገኘ እንዲሄድ ለማድረግ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ በኩል የምትሰጠውን ሥልጠና በአህጉሪቱ ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍት ማድረጓን ትቀጥላለች።
ለሕዝባችን የተሻለ መጻኢ ዕድል የመገንባት ኃላፊነታችን ሊቀጥል ይገባል!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጉባኤው ለመዲናችን ተምሳሌታዊ ጉዞ ማንሰራራት ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል!
ብልፅግና ፓርቲ የጠራ እሳቤ ያለው፣ ቃሉን በተግባር የመተርጎም ልምድ ያካበተ፣ የአዲስ አበባን ተምሳሌትነት፣ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ያበሰረ ግዙፍ ፓርቲ ነው፡፡
የዴሞክራሲ ባህልን በጠንካራ መሰረቶች ላይ እየገነባ የሚገኘው ፓርቲያችን ለሀሳብ የበላይነት፣ ለሁሉን አቀፍ ልማት፣ ለአካታች ዕድገት እንዲሁም ለብሔራዊነት የወል ትርክት ግንባት ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡
በአዳዲስ ፈጠራዎች እና በመፍጠን መርሆቹ፣ በዳበረ የስራ ባህል፣ ቃሉን በተግባር እየተረጎመ የሚገኘው ብልፅግና ፓርቲ በሁለንተናዊ አቅሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም ላይ ካሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፓርቲዎች ተርታ መጠቀስ የቻለ ተራማጅ ፓርቲ ነው፡፡
ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ሀገራዊ ራዕይውን በተስፋ ሰጪ ድሎች እያሳካ የሚገኘው ፓርቲያችን አህጉራዊ አሻራውን ለማሳረፍም ብርቱ ጥረቶችን እያሳረፈ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፤ የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር እሳቤዎች ተግባር ላይ በመዋላቸው የተመዘገቡ ስኬቶችን ለአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን በማካፈል የጋራ ዕድገትን ለማፋጠት ጉባኤው የጎላ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡
በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ፣ በከተማ ውበትና ፅዳት በተለይም በኮሪደር ልማትና በወንዝ ዳርቻ ልማት እንዲሁም በሌሎች የከተማ መልሶ ግንባታ ተግባራት በመዲናችን የተመዘገቡ ስኬቶች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለመጡ ፖሊሲ አውጪዎች እና የሀሳብ ፖለቲካ አራማጆች ጉልህ አበርክቶ ይኖራቸዋል፡፡
አዲስ አበባን ህፃናት በምቾት የሚያድጉባት፣ ወጣቶች የነገ ህይወታቸውን ዛሬ የሚገነቡባት፣ ሴቶች እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑባት፣ የሀገር ባለውለታ አረጋውያን ተገቢውን ክብርና እንክብካቤ የሚያገኙባት ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ማዕከል ያደረጉ ሰው ተኮር ተግባራት በሌሎች ሀገራትም እንዲሰፉ የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በመዲናችን መካሄዱ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
አህጉር አቀፍ ጉባኤው ለመዲናችንም ለተሞክሮ የሚበቁ ልምዶቿን ከማካፈል ባሻገር፣ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የሀሳብ ፖለቲካ አራማጆች የሚሰጧቸውን ገንቢ አስተያየቶች የዕቅድ አካል በማድረግ የላቀ ድል ለማስመዝገብ ተጨማሪ አቅም ይፈጥርላታል፡፡