ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
1.5K subscribers
1.09K photos
20 videos
13 files
247 links
Download Telegram
ከ11 ዓመታት በፊት ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን፣ የግብጻውያን እና ኤርትራዊናን ክርስቲያኖች ወደ እስልምና እምነት ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በሊቢያ በሰይጣናዊው አይሲስ ታ'ር,ደው በሰማዕትነት አረፉ።

#በሰማዕትነት_ደም_ተጠመቁ።
_
11 years ago today, in 2007 E.C Ethiopian, Egyptian, Eritrean Christians were beheaded by satanic ISIS in Libya for refusing to convert to Islam.
❤3
“ዳግመኛ እርሱ እንደ ሞተ፣ በሦስተኛውም ቀን እንደ ተነሣ፣ ስለ ተነሣም ሥጋው የማይፈርስ የማይበሰብስ፣ የማይታመም፣ የማይሞት እንደ ኾነ እናምናለን፡፡ ሥጋውም ከእርሱ ጋር አንድ ኾኖ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአርያም በልዑል ዙፋኑ ተቀመጠ፡፡ ዳግመኛም በሙታንና በሕያዋን ይፈርድ ዘንድ ዂሉ አንድ ኾኖ በሚነሣበት ጊዜ እርሱ በጌትነት ይመጣል፤ ለዂሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል፡፡ እኛ በእነዚህ ቃላት ሳናወላውል ጸንተን እንኖራለን፤” (ቅዱስ ዲዮናስዮስ፣ ሃይ. አበ. ፺፱፥፴፪)፡፡
🤩1
“በታወቀች በተረዳች በሦስተኛይቱ ቀን ‹መቃብር ክፈቱልኝ፤ መግነዝ ፍቱልኝ› ሳይል ተነሣ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበት በዝግ ቤት ገባ፡፡ የተወጋውን ጎኑን፣ የተቸነከረውን እጁን፣ እግሩን አሳያቸው፡፡ በዓለመ ነፍስ የኾነውን እያስተማራቸው ዐርባ ቀን ኖረ፤” (ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት፣ ፬፥፳፭)፡፡
👏3
ፊልጵስዩስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥
⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
⁸ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
⁹ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤
¹⁰ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥
¹¹ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።
የኢየሱስ ክርስቶስ መልአክ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል በምልጃው ይርዳን።

ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ነቢያትን የረዳቸው እርሱ ነው። እኛንም ይራዳን።
👏4
This image is a powerful and somber example of modern Ethiopian Orthodox iconography. It depicts the 28 Ethiopian Christians who were martyred in Libya in April 2015.
🥰4
ማርቆስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ደግሞም ከጢሮስ አገር ወጥቶ በሲዶና አልፎ አሥር ከተማ በሚባል አገር መካከል ወደ ገሊላ ባሕር መጣ።
³² ደንቆሮና ኰልታፋም የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፥
³³ እጁንም ይጭንበት ዘንድ ለመኑት። ከሕዝቡም ለይቶ ለብቻው ወሰደው፥ ጣቶቹንም በጆሮቹ አገባ እንትፍም ብሎ መላሱን ዳሰሰ፤
³⁴ ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና፦ ኤፍታህ አለው፥ እርሱም ተከፈት ማለት ነው።
³⁵ ወዲያውም ጆሮቹ ተከፈቱ የመላሱም እስራት ተፈታ አጥርቶም ተናገረ።
³⁶ ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት።
³⁷ ያለ መጠንም ተገረሙና፦ ሁሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል አሉ።
❤2
“ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” — ዮሐንስ 14፥21
❤4
'' ሶስት ሲሆን አንድ አንድ ሲሆን ሶስት በአካል ሶስት ሲሆን በመለኮት አንድ ለሚሆን አምላክ እሰግዳለሁ።'' ( የዘወትር ጸሎት )

#ሥላሴ_አምላኬ
❤4🥰2
አቤቱ ጌታ ኢየሱስ ሆይ በተወደደች እናትህ ድንግል ማርያም ጸሎትና ምልጃ ማረን ራራልንም።

🌼 21
❤6🤩3
✅ የተራራ ክብር ከመጽሐፍ ቅዱስ አንደበት

🌸 ተራራ ማለት ከፍ ያለ የመሬት ገጽታ ያለው ስፍራ ማለት ስለሆነ ፤ ወደ ተራራ መውጣት የልዕልና፣ የመንፈሳዊ ዕድገት ፣ ወደ እግዚአብሔር የመቅረብ ምልክት ነው። ተራራ በብሉይ ኪዳንና - በሐዲስ ኪዳን ብዙ ሃይማኖታዊ ስራ ተሰርቶበታል።

✔️ " ኢየሱስም #ወደ_ተራራ_ወጣና በዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር #ተቀመጠ ። | ዮሐ 6:3 |

1/ ተራራ ለእግዚአብሔር መስዋዕት የሚቀርብበትና እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ የሚገጥበት ቦታ ነበር።

▶️ ዘፍ 12:7-9 ፣ ዘፍ 22:2-14 ፣ ዘፍ 31:54 🌸 " የዚያን ጊዜም ኢያሱ በጌባል ተራራ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ።"(ኢያ 8:30)

2/ ተራራ ለእግዚአብሔር ይሰገድበት የነበረ ቦታ ነበር

▶️ 2ኛ ሳሙ 15:32 ፣ ኢሳ 27፡13 🌸 " አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በቅዱስ ተራራውም ስገዱ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና። "(መዝ 98[99]:9)

3/ ተራራ ለቅዱሱ አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና የሚቀርበትና የእርሱም ቤት ማደሪያው ነበር።

▶️ ኢሳ 2:2 ፣ ሚል 4:1-2 🌸 " ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን..። "(ኢሳ 2:3) 🌸 " እኔም በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን የምቀመጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ "(ኢዮ 3:17) በተጨማሪ ✅ መዝ 42(43):3 ፣ መዝ 47(48):1 ፣ መዝ 67(68):16 ፣ መዝ 73(74):2 ፣ መዝ 23(24):3 ፣ አብድ 1:16 ፣ ዕን 3:3 ፣ ሶፎ 3:11 ፣ ኢሳ 18:7 አንብቡ።

4/ ተራራ የእግዚአብሔር ምሥጢር ወይ ክብር የሚጋለጥበት ነበር።

▶️ ዘጸ 24:16 ፣ ዘጸ 20:18 ፣ ዘጸ 19:11 ፣ ዘጸ 24:12( የጽላቱን ምስጢር በተራራ ላይ እንደገለጠለት።)
🌸 እግዚአብሔር ሙሴን ለመጀመሪያ ጊዜ ያነጋገረው በኮሬብ ተራራ ነው በተራራው ላይ ቁጥቋጦው በእሳት ሲነድ ቁጥቋጦው ሳይቃጠል አሳይቶታል /ዘጸ 3:1-12/ ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው የመሆኑ ምሥጢር ነው።

5/ ተራራ ጸሎት የሚጸለይበት ነበር።

▶️ መዝ 41:6 🌸 " በቃሌ ወደ እግዚአብሔር እጮሃለሁ ከተቀደሰ ተራራውም ይሰማኛል።"(መዝ 3:4)

6/ ተራራ እግዚአብሔር የሚመለክበት ስሙ የሚጠራበት ስፍራ / ኢየሩሳሌም / የተቀደሰ ተራራ ይባላል።
🌸 " በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፥ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።" (ኢሳ 57:13)
ተጨማሪ ▶️ መዝ 77:54 / መዝ 77:68 / ኢሳ 11:9 / ኢሳ 18:7 / ኢሳ 56:7 / ኢሳ 66:20 / ሕዝ 20:40 / ሕዝ 28:14 / ዳን 9:16 / መዝ 2:6 አንብቡ።

🌴 ተራራ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የተሠራበትና ቅዱስ የሚል ቅጥያ የተሰጠውን ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስም በሐዲስ ኪዳን ወደ ተራራ እየወጣ ያስተምር ነበር '' ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው ።'' /ማቴ 5:1-2/
▶️ ማር 3:13-16 / ማቴ 15:29-31 አንብቡ።

🌴 ወደ ተራራም እየወጣ ይጸልይ ነበር ▶️ ማቴ 14:23/ ማር 6:46 / ሉቃ 6:12/ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያድረውም ደብረዘይት በምትባል ተራራ ነበረ ▶️ ሉቃ 21:37.. የአምላክነቱን ምሥጢር ለደቀመዛሙርቱ ይገልጽላቸው በረጅም ተራራ ደብር ታቦር ነው ▶️ ማቴ 17:1-8 / ማር 9፡2-9/ ሉቃ 9:28-36/ ማቴ 17:1-8/ ማር 9:2-9/ ሉቃ 9:28-36/

አንባብያን ሆይ ▶️ እንግዲህ የተራራን ክብር ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማስረጃ ተመልክተናል። ስለዚህ ዛሬም ላይ ትላልቅ ገዳማትን አድባራትን በተራራ ላይ በእግዚአብሔር ፈቃድ የምንሰራው ሄደንም የምንሳለመው መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርገን እንደሆነ ልብ በሉ።

ይቆየን።

ቻናላችንን በዚህ ▶️@WwEotc ተቀላቀሉን!
🔥1
ኢዮብ 37
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ከሰሜን ወርቅ የሚመስል ጌጠኛ ብርሃን ይወጣል፤ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስፈራ ግርማ አለ።
²³ ሁሉን የሚችል አምላክን እናገኝ ዘንድ አንችልም፤ በኃይል ታላቅ ነው፤ በፍርድና በጽድቅም አያስጨንቅም።
²⁴ ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል በልባቸውም ጠቢባን የሆኑትን ሁሉ አይመለከትም።
❤1
የሃዘንተኞች መጽናኛቸው : ተስፋ ለቆረጡት ተስፋቸው : የስደተኞች መጠለያቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
❤6
ታላቁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ይታረቀን ይማረን። ለሃገራችን አንድነት ሰላም ይስጥ።

🌼 ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማእታት
❤5🔥3
Always have the fear of God before your eyes. Remember Him who gives death and lives. Hate the world and all that is in it. Hate the peace that comes from the flesh. Renounce this life, so that you may be alive to God. St. Anthony the Great
🤩4
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንደነ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሉ አባቶችን ያፈራች ታላቅ ቤተክርስቲያን ነች።

ጌታ ኢየሱስ በዚህ በተከበረ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ጸሎት ይቅር ይበለን።
🔥4❤1👏1
አቡነ ተክለሃይማኖት ቅድስናቸው ልዩ የሚያረጋቸው ነገር አንዱ የሥላሴን መንበር ከ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር ሆነነው ማጠናቸው ሲሆን ይህን ያደረገ አባት እስካሁን የለም።
❤5
A Christian receives divine wisdom in three ways: by the commandments, teachings, and
faith. The commandments free the mind from passions. Teachings lead it to true knowledge
of nature. Faith leads to the contemplation of the Holy Trinity.
(St. Maximus the Confessor, Chapters on Love, 4.47)
❤2