ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
1.5K subscribers
1.09K photos
20 videos
13 files
247 links
Download Telegram
ያከበርዋ ለሰንበት መላእክትን በሰማያት
ጻድቃን በውስተ ገነት።

#የሰው_ልጅ_የሰንበት_ጌታ_ነው
🥰3
የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ገድለ ቅዱስ አቡነ ተክለ ሀይማኖት ላይ #እባብን_የገደለ_ይፀድቃለል ይላል እና "እባብን እየፈለግን ብንገድል እንፀድቃለን ወይ ???" ብለው ይጠይቁናል፡፡

መልስ

ተፈጥሮአዊውን እባብ መግደል ገነት ያስገባል የሚል እምነት ቤተክርስቲያን የላትም።

እባብ የተባለው የሰው ልጅ ከሳሽ መጽሐፍ ዘንዶው የሚለው የወደቀው መልአክ ዲያቢሎስን እንጂ ተፈጥሮአዊ እባብን አደለም።

ሰይጣንን መግደል ማለት የእርሱን አሰራር ማፍረስ (አለመከተል) እርሱን እምቢ እግዚአብሔርን እሺ ማለት ነው። እግዚአብሔርን ስናምንና የሃጢአት ሸክማችንን ወደ እርሱ ሄደን ስናራግፍ ያኔ ሰይጣንን መግደል ( ማሸነፍ ) እንችላለን። በመቀጠልም በንስሐና ታጥበን በእግዚአብሔር ምህረት የመንግስቱ ወራሾች እንሆናለን ነው መልእክቱ።

ስለዚህም ይህንን የገድል ክፍል ስናነብ ከተፈጥሮአዊ እባብን ከመግደል ጋር የሚያገናኘው ነገር አለመኖሩን በመገንዘብ እንረዳ።

@WwEotc

*" አግዚአብሔር ያላፈረባቸውን እኛ የምናፍርባቸው ለምንድን ነው?? (ሮሜ8:28)
❤5👍3
"እውነተኛ ክርስቲያን ስሜቱ የሚመራው ሳይሆን ስሜቱን የሚመራ ነው" ✍️ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
👍6👏1
የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ድንቅ ተአምር እና የአባታችን ምስክርነት፡፡

በዘመናችን ማለትም ከዛሬ ጥቂት አመት በፊት በጠና የታመሙ አንድ አባት ነበሩ፡፡ ከሕመማቸው የተነሣ አምላክ እግዚአብሔር ምሕረቱን እንዲልክላቸዉ አብዝተዉ ይለምኑ ነበር፡፡

እግዚአብሔር ለሁሉም ጊዜ አለውና ከዕለታት አንድ ቀን ሐምሌ 4 ቀን በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኘው የሊቀ መላዕኩ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በመሄድ በእምነት ይፀልዩ እና ያለቅሱ ነበር፡፡

በፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥዕል ፊትም ተንበርክከው ይለመኑ ነበር ጻድቁ ከጌታ ኢየሱስ አማልደው ከበሽታቸውን ይፈውሷቸው ዘንድ።

የመዳን ቀን ደረሰ

ወደ ቤታቸው ተመልሰዉ ፀልየዉ ወደ ምኝታቸዉ ሄደው ይተኛሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ያዩት ለህዝብ እንዲህ ሲሉ የተናገሩት " አልጋ ላይ ጋደም አልኩ በእንቅልፍ ሸለብ ብዬ ነበር ከዛም ከፊቴ አንድ ሽማጌሌ ሰው ገላው በሙሉ በነጭ ፀጉር የተሸፈነ ገላዉ የሚያበራ የብርሃን መሥቀል የያዘ ሠው ከፊቴ ቆሞ አየሁ፡፡ ፈርቼም ነበር እርሡም በያዘው መስቀል ዳበሥኝ በሚያበራውም እጁ ዳብሥኝ ቤቴን እየዞረ ከባረከ በኋላ ተሰወረ ፡፡ ወዲያውኑ ከእንቅልፌ ስነቃ ጤናዬን አገኘው የጻድቁም ምልጃ ደረሠልኝ፡፡" ብለው ምሥክርነት ሠጥተዋል፡፡

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ በከበረ ጻድቅ ጸሎት ይማረን።

አሜን።
👏8👍3🥰3
ፓስተር እገሌ አዳነኝ እያልክ ድንግል ማርያም አደነችን ስንል የሚከፋህ ሰው እንደምን ነህ? 😊
በቤተክርስቲያናችን የስእል አሳሳል ሕግጋት አንዱ እርኩሳን መናፍስት ሲሳሉ #አይጥማ ቀለም ይይዛሉ። ይህም ቀለም ነጭም ጥቁርም አይደለም። ይህ የሆነበት ምክንያት ቀድሞ የብርሃን መልአክ የነበሩ አሁን ደግሞ እርኩሳን መሆናቸውን ለማሳየት ነው።
👍6❤1
ቅዱሳን ያድናሉ ሰንል ስለምን ትደነቃለህ? የአንተ ፓስተር አዳነኝ ፈወሰኝ ትል የለምን? እኛስ ቅዱሳን በሥጋ በምደር ሳሉ ልክ እንደ ሐዋርያት በጥላቸውና በልብሳቸው ይፈውሳሉ እንላለን። በሥጋ ከተለዩን በኋላ ልክ የኤልሳዕ መቃብር የሞተውን አስነስቶ እንደፈወሰ እነርሱም ይፈውሳሉ እነላለን። ይህን ጸጋና ክብር ሃይሉ ምንድን ነው ብትል #ኢየሱስ የሚለው ኃያልና ታላቅ ሥም ነው እንላለን።

@WwEotc
❤8👍1🥰1
ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው '' #ከክርስቶስ_ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?''

- ሮሜ 8:35 -


'' ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ #ከእግዚአብሔር_ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።''

- ሮሜ 8:39 -
🥰2🤩1
<< ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል። >> መዝሙር 41:1፤

@WwEotc
👏3
ሰይጣን ( እርኩስ መንፈሱ ) ተጠምቆ ክርስቲያን ሆነና ገነት ገባ የሚል የቤተክርስቲያን ትምህርት የለም። ታዲያ በገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት ላይ የተጠቀሰው ምንድን ነው ቢሉ :-

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያጠመቁት የሰው ልጅን ነው። ነገር ግን ያ ሰው ከምግባሩና ከውሎው የተነሳ ሰይጣን ተባለ። እንደዚህ አይነት ሰዎች በምትሓት በእሳት ላይ ይራመዳሉ ፤ እሶኸ ላይ ይተኛሉ ፤ ባህር ውስጥ ይኖራሉ ወዘተ...

ስለዚህ እንዲህ ከእርኩስ መንፈስ ጋር ይኖር የነበረውን ሰው አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጠመቁትና ክርስቲያን አደረጉት። አንዳንዶች ግን ይህንን ታሪክ በመቀየር ለራሳቸው አላማ ሲጠቀሙ እናያለን። እኛ ግን እውነትን እንመሰክራለን።

የጻድቁ በረከት አይለየን።

@WwEotc
❤10
ስለ ጥምቀት ሲነሳ ጥያቄ የሚሆነው አንዱ '' ህጻናትን ለምን ታጠምቃላችሁ'' የሚል ነው።

ህጻናት የሚጠመቁበት በወላጆቻቸው እምነት ነው። የግድ የተወለዱ ህጻናት መማር አይጠበቅባቸው። ይህም ወላጆቻቸው በክርስቶስ ክርስቲያን የሆኑ አንደሆን የእነርሱ እምነት እምነታቸው ሆኖ ይጠመቃሉ።

ጌታችንም ‹‹ሕጻናትን ወደ እኔ እንዲመጡ ተዉ አትከልክሏቸው የእግዚአብሔር መንግስት እንደነዚህ ላሉት ናትና›› (ማር. 10፥14) የሕጻናት ጥምቀትን የሚደግፉ መሆኑን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስረጂ ታደርጋለች፡፡

በበዓለ ኃምሳ ቅዱስ ጴጥሮስ ሲሰብክ ይሕንን ብሎ ነበር ‹‹የተስፋው ቃል ለእናንተና ልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ የሚጠራቸው በሩቅ ላሉሁሉ ነውና አላቸው›› ሐዋ 2፥39) በዚህም ምዕራፍ ላይ በተመሳሳይ ልጆቻቸውም ጭምር ወደ መዳን እንዲቀርቡ ማጥመቅ እንዲገባ ያስተምራቸዋል፡፡ ለዚህም ምስክራችን ‹‹ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ››የሚለው የመጽሐፍ ቃል ነው(ሐዋ. 2፥40)

የጥምቀት ምሳሌ የሆነው ግዝረት በእስራኤላዊያን ልማድ በልጅነት ስለሚደረግ ‹‹በስምንተኛው ቀን ልጅ አስገርዝ›› (ዘፍ.17፥12) ይህም ሥርዓት ከሕጻናት ጥምቀት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ የእስራኤላዊያን ሥርዓት ነው፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናነበው በሐዋርያት ዘመን ክርስትናን የተቀበሉ ክርስቲያኖች ከነቤተ ሰቦቻቸው እንደተጠመቁ አስረጅ የመጻሕፍት ታሪኮች ስላሉ

🌼 ልድያና ቤተሰቧ (ሐዋ 16፥15)
🌼  የወይኒ ቤት ጠባቂውና ቤተሰቡ(ሐዋ. 16፥33)
🌼 ቆርኔሌዎስና ቤተሰቡ(ሐዋ 10፥48)
🌼 የምኩራቡ አለቃ ቀርስጶስና ቤተሰቡ (ሐዋ 18፥8)
🌼 የእስጢፋኖስ ቤተሰቦች(1ኛ ቆሮ 1፥16)
❤3🔥1
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ራቅንህ ፡ አንተ ወደኛ ቀረብክ፤ በግብራችን ናቅንህ አንተ ግን እኛን አከበርክ፤ ያለአንተ መኖር እንደማንችል ታውቃለህና ክፋታችንን ሳታይ ራራህልን ስንፍናችንን ሳታይ ቀረብከን ፤ (ቅዳሴ ያዕቆብ ዘስሩግ)
❤4🥰2
ተአምራዊ ባለ መስቀል ቅርጽ የግሸን ተራራ።

🌿 እግዚአብሔር አምላክ '' መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጠው።'' ባለው መሰረት ንጉስ ዘርዓ ያዕቆብ የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀልን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀመጠው።
🥰6👍1🤩1
ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ሆይ በአንድ ልጅህ በጌታችንና በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ጥበብና ማስተዋልን ስጠን ብለን እንለምንሃለን።

@WwEotc
❤5
" መፍራት ያለብንን እግዚአብሔርን ሳንፈራ ፤ መፍራት የሌለብንን ሰይጣንን እንፈራለን።'' ( ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ )
😢7
'' ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
እግዚአብሔር ነው፥ ብርቱና ኃያል፥
እግዚአብሔር ነው፥ በሰልፍ ኃያል።'' (መዝ 24:8) @WWEOTC
፩. ዕለተ ሰኑይ

ሀ. አንጽሖተ ቤተ መቅደስ፡- በዚች ዕለት መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፡፡ በዚያም በደረሰ ጊዜ ቤተ መቅደሱ የጸሎት የመሥዋዕት ቤት መሆኑ ቀርቶ የንግድ ቤት ሆኖ ቢያገኘው ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው ገርፎም አስወጣቸው፡፡ ይኸውም የእርሱ ቤተ መቅደስ የሆነውን ሰውነታችንን ኃጢአት ሰፍኖበት ቢያገኘው ራሱ ተገርፎ ተገፍፎ መከራ መስቀልንም ሁሉ ተቀብሎ ከሰውነታችን ኃጢአትን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ (ሉቃ.፲፱፥፵፮)

ለ. መርገመ በለስ፡- ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግስቱ ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ፤ በመንገድም ሲያልፍ ቅጠል ያላት በለስን ከሩቁ ተመለከተ፡፡ ወደ በለሲቱም በቀረበ ጊዜ ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ያንጊዜም ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ከአንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር›› ሲል በለሲቱን ረገማት፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ይህንን ሰሙት፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት በለሲቱ የተረገመችባት ቀን ናትና መርገመ በለስ ተብላ ትጠራለች፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩-፲፬)

በዚህ አገላለጽ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ስትሆን ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባር ነው፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈልጎ አላገኘባቸውም፡፡ እስራኤል፦ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም ዘር መባልን እንጂ የአብርሃምን ሥራ በመሥራት በምግባር በሃይማኖት ጸንተው መኖር አይፈልጉምና ደግ ሰው አልተገኘባቸውም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በለስ የተባለች ኦሪት ናት፡፡ ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛትም አማናዊ ድኅነትን የምታሰጥ ሆና አላገኛትም፡፡ ይሁን እንጂ በእርሷ ድኅነት ባይገኝባትም ‹‹ኦሪትና ነቢያትን ከመፈጸም በቀር ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ›› በማለት ሕገ ኦሪትን ፈጽሟታል፡፡ ከዚህም ባሻገር በለስ የተባለች ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አግኝቷታል፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ለጊዜው ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም በአንቺ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ሲል ነው፡፡ በለሲቱ ስትረገም ፈጥና መድረቋም በአዳም ምክንያት ያገኘን በደል በእርሱ እንደጠፋልን ለመግለጽ ነው፡፡

ምንጭ ተዋሕዶ ሚድያ ማዕከል
ሙስሊም ወገኖች ኢየሱስ አልተሰቀለም ብለው የሚጠቅሱት ቃል ላይ እናማማራለን።

ሰዓተ ቃለ ወንጌል ቅዱስ።
👉 " ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም አለ።"(የዮሐንስ ወንጌል 7:34) 👈

ጌታችን ስለሞቱና ወደ አብ ስለ መሄዱ/ስለ ዕርገቱ / እየተናገረ ነው። አይሁድ በኃላ ምፅአት እንዲያጸድቃቸው ይፈልጉታል ግን አያገኙትም።

'' እኔ ወደ አለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም'' ይህ ቃል ሁለት ትርጉሞቹን ይዟል።
1/ እኔ በመስቀል ተሰቅዬ ስሞት እናንተ አትሞቱም የሚል ነው። ለደቀ መዛሙርም ከእርሱ ጋር እንደማይሞቱ ሲገልጽላቸው አይቻላችሁም እንዳልኋቸው አሁን ለእናንተ ደግሞ እላችኋለሁ @ዮሐ 13:33 አሁን ከእኔ ጋር አትሞቱም ሲላቸው ነው።

2/ የእኔ ርስት ወደ ሆነችው ወደ መንግሥተ ሰማያት መምጣት አይቻላችሁም ይላቸዋል አይሁድን።

የቃሉ መልእክት ይህ ሆኖ ሳለ በእስልምና ዘንድ ግን ኢየሱስ ላለመሰቀሉ ምክንያት አሮጌው ማቅረባቸው አጀብ ነው።

የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጠባቂነት አይለየን።
😢3👍1