ከበሮ ፣ ጸናጽል፣ መቋሚያና ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት ሆነው መመዝገባቸው ተገለጸ !
ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም [ተሚማ/ አዲስ አበባ]
ከበሮ ፣ ጸናጽል ፣ መቋሚያና ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዝግቦ ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው እውቅና ማግኘታቸውን የመምሪያው ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ገልጸዋል።
©የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግኑኝነት መምሪያ

❤3🥰3👍1
የማይሞተው ሞተ ። ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናችው ዘንድ ሞተ ።
👉የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት ።
ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን ።
ወየው ወየው ወየው መድኃኒታችን ኢየሱስ ።
ወየው ወየው ወየው ንጉሣችን ክርስቶስ ።
ወየው ወየው ወየው ጻድቃን
ከዕንጨት አወረዱት ሥጋውንም
ለመገነዝ ከርቤ የሚባል የጣፈጠ ሽቱንና ንጹሕ በፍታን አመጡ ።
ቅዱስ እግዚኣብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለውጥ ። ከድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን ።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ❤️

❤10
“በፈቃዱ በሥጋው የእኛን ሕማም ታመመ፤ በእውነት የእኛን ሞት ሞተ፡፡ ይኸውም የነፍስ ከሥጋ መለየት ነው፡፡ በፈቃዱ በተለየ አካሉ ሞትን ገንዘብ አደረገ፡፡ በሦስተኛውም ቀን በሥልጣኑ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱ ዕሪና ተቀመጠ፡፡ በኋለኛይቱ ቀንም በሙታን በሕያዋን ሊፈርድ ይመጣል፤” (ቅዱስ ፊላታዎስ፣ ሃይ. አበ. ፻፭፥፲፬)፡፡
እንኳንና አደረሳችሁ!
@wweotc
እንኳንና አደረሳችሁ!
@wweotc
👏2
“ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ከጲላጦስ ተካሰው ከመስቀል አውርደው፣ በድርብ በፍታ ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት፡፡ በሦስተኛው ቀን መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበት በዝግ ቤት ገብቶ በጽርሐ ጽዮን ታያቸው፤” (ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ፣ ፩፥፱-፴፩)፡፡
ስለ ቤዛነት
“ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።”
— ሐዋርያት 7፥35
ቤዛነትን የተመለከቱ ጥቅሶች በብዙ ዓይነት መልክ በብዙ ስፍራ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፈው እናነባለን። በሁለቱ ታላላቅ ሊቃውንት ካዳነ ወልድ ክፍሌና ደስታ ተክለወልድ መዝገበ ቃላት ስለ ቤዛነት እንዲህ እናነባለን
1/"ቤዛ በቁሙ ዋጋ፣ ካሳ፣ ለውጥ፣ ምትክ፣ ዋስ፣ መድን፣ተያዥ፣ ጫማ፣ ጥላ" (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ 266)
ቤዛ ደቂቅ አገባብ፦ "ስለ ፈንታ ምክንያት እሜጡ ነፍስየ ቤዛ አባግዕየ ዐይን ቤዛ ዐይን፤ ወስን ቤዛ ስን፦ በዐይን ፈንታ፤ በጥርስ ፈንታ ተሰቅለ ቤዛነ ስለ እኛ በእኛ ምክንያት፤
"ቤዛ ለውጥ ካሳ ባንድ ሰው መከራና ሞት ተላልፎ መሞት፣ ታዳጊን ምትክን መኾን ለሞት ለመከራ መለወጥ፣ መሥዋዕት ነት፣ መገረፍ መሰቀል
ቤዛ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ብሎ የአምላክነቱን ባሕርይ ከሥጋ ጋር አዋሕዶ ለኃጢአታችን ቤዛ መኾን፤
ቤዛነት በጥቅሉ ምትክነትን የሚያሳይ ሲሆን በአዳም ምትክ ሞትን የተቋደሰው ብቸኛ ክርሰሰቶስ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያን ስትገልጠው የኖረችው እውነት ነው። ስለ አዳም መሞትን ገንዘብ ያደረገ ቤዛ ክርስቶስ ብቻ ነው። ይህን እንኳን ለእመቤታችን፥ ለአብ እና ለመንፈስ ቅዱስም አትናገረውም። ምክንያቱም የተሰቀለው ወልድ በተለየ አካሉ ነውና።
ድንግል ማርያምን ቤዛዊተ ዓለም ስንል የሔዋን ምትክ ማለታችን እንደሆነ የታወቀ የተረዳ ነው። የቀደመችቱ ሔዋን የአለማመን፣ የአለመታዘዝ፣ የኃጢአት፣ የውድቀትና የሞት ምልክት በመሆን ሴትነትና ሰውነትን አሳንሳው ነበር፤ ሁለተኛይቱ ሔዋን ደግሞ የማመን፣ የመታዘዝ፣ የቅድስና የንጽሕና ምልክት በመሆን የቀደመችቱ ሔዋን ምትክ(ቤዛ) በመሆን መማሪያችን ሆናለችና የአንስተ ዓለም ምልክት በመሆኗ "ቤዛዊተ ዓለም" እንላታለን።
➾ Tesfaye Mosissa W/mariyam

❤3👏3👍1
ብፁዕ ሆይ ሲያገለግሉ እነዚህን እየዘለሉ ነበር???
+ ብፁዕነቶ፤ ይህችን የሰዓታት ክፍል ብለዋት ይሆን?
ኪሩቤል ሰባሕያን ወሱራፌል መዘምራን፥ ምሉዓነ ጸዳል ወብርሃን፥ ይቄድሱኪ ወይብሉኪ በአሐቲ ልሳን፥
ቅድስት ማርያም "ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም"
አመስጋኞች ኪሩቤልና ወጋገንና ብርሃንን የተመሉ ሱራፌል አክብረው በአንዲት አንደበት ንጽህት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣
ልዩ "ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም ይሉሻል"
+ ብፁዕነቶ፤ ይህችን የስብሐተ ነግህ ክፍል ብለዋት ይሆን?
"ቤዛ ቤዛ ነፍሰ ኲሉ መዋቲ በሰማይኒ ወበምድር አንቲ"
+ ብፁዕነቶ፤ ይህችን የጸሎት ክፍል ብለዋት ይሆን?
መስቀል ሀይልነ መስቀል ፅንእነ "መስቀል ቤዛነ"
መስቀል መድኀኒተ ነፍስነ…።
+ ብፁዕነቶ፤ ይህችን የነግሥ ክፍል ብለዋት ይሆን?
ኪያኪ ሰናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ እግዚአብሔር ይ ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ።
+ ብፁዕነቶ፤ ይህችን የመልክዐ ሕማማት ክፍል ብለዋት ይሆን?
"ቤዛዊተ ኵሉ ዓለም ሰላም ለኪ፡፡"
+ ብፁዕነቶ፤ ይህችን ክፍል ብለዋት ይሆን?
ንትፈሣሕ ኵልነ በዝክረ ስምኪ ጥዑም ወበደመ አስካልኪ መዓድም ቅድስት ማርያም "ቤዛዊተ ኵሉ ዓለም"
+ ብፁዕነቶ፤ ይህችን መልክአ ኪዳነምሕረት ክፍል ብለዋት ይሆን?
"ቤዛዊተ ዓለም ማርያም" አስተበቊዓኪ አንሰ፤
ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚአየ ነፍሰ፤
እስመ በሥራይኪ ለቊስልየ ቀባዕክኒ ፈውሰ፡፡
ብዙ ማንሳት ይቻላል…
➾ መጋቤ ለሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
@WwEotc

👍2
#ሰበር
ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ ተወያየ !
ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ማለዳ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባሳለፍነው አርብ በስቅለት ዕለት በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል።
በብፁዕነታቸው የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት ለአርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞል።
በተያያዘ ዜና የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ቤተ ክርስቲያናችንን በመወከል እንዲገኙ ተወስኗል።
©የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

🔥1
‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል››
➾ ቅዱስ እንጦስ
➾ ቅዱስ እንጦስ
-የወይን ጠጅ የላቸውም -
ይህ ጥያቄ እመቤታችን ለምትጠይቃቸው ጥያቄዎች መጀመሪያ ነው። የጽድቅ ሥራ መሥራት ስለአቃታቸው ሰዎች ንጽሕናቸውን፣ ቅድስናቸውን፣ ስላጡ ሰዎች ሥነምግባር ስለሌላቸው ሰዎች አስራት ጸሎት መጾም መስጠት ስላቃታቸውውና ራሳቸውን መግዛት ስለተሳናቸው ሰዎች :- ጽድቅ እኮ የላቸውም' ንጽሕና ቅድስና እኮ የላቸውም' ሥነምግባር እኮ የላቸው' ኃጢአትን የማሸነፍ ችሎታ እኮ የላቸው / ሥርየተ ኃጢአት ይደርግላቸው / ብላ ስለምታቀርበው ምልጃ መጀመሪያ ነው።

❤1
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን አትሰብክም የሚሉ ወገኖች ሆን ብለው ሰውን ለማደናገር የሚያረጉት ተራ ወሬ እንጂ ልባቸውማ እውነታውን ያውቀዋል።
ኢየሱስ በቤተክርስቲያን እንዲህ ይመሠገናል
“ሰውን ስለ መውደድህ ይህን ሁሉ አደረግህ፤ ከሙታን ተለይተህ ‹መቃብር ክፈቱልኝ፤ መግነዝ ፍቱልኝ› ሳትል ተነሣህ፡፡ ከእግረ መስቀል ሙታንን አስነሣህ ነፍሳትን ከሲኦል ማርከህ ለአባትህ አቀረብህ፤” (ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ ፩፥፳፬)፡፡
🔥2
🥰1
ቋሚ ሲኖዶስ ልዩልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ።
ሚያዚያ ፳፪/ ፳፻፲፯ ዓ.ም
ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከቤተክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አዳራሽ የሰጡትን ትምህርትና በማኅበሩ ሚዲያ የተላለፈበትን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬው መደበኛ ጉባኤው በሰፊው ተወያይቶ ለመወሰን በያዘው ቀጠሮ መሰረት በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
1. ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር በተለያዩ ጊዜያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ውጪ በሚዲያው ያስተላለፈው የስሕተት ትምህርት የቤተክርስቲያናችንን አባቶች፣ሊቃውንቱንና መላው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሳዘነ በመሆኑ በማህበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ በኩል ጊዜያዊ የእገዳ ደብዳቤ እንዲደርሰው እና በመምሪያው በኩል አስፈላጊው ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ሆኖ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት ይቻል ዘንድ አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ እንዲቋቋም አድርጓል።
በዚህም መሰረት ቋማ ሲኖዶስ ያቋቋማቸው አጣሪ ልዑካን አጠቃላይ የማህበሩን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እና በሚዲያው ያስተላለፋቸውን የስህተት ትምህርቶች በተመለከተ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ከማህበራት ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ ጋር በመነጋገር በሚገባ መርምርውና አጣርተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውሳኔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ፣
2. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “ማርያም ቤዛዊተ ዓለም” አትባልም በማለት ከቤተ ክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ የሰጡት ሕጸጽ ያለበት ትምህርት በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚገባ ተመርምሮና ተጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲቀርብ ብፁዕነታቸውም ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተአቅቦ እንዲቆዩ፣
3. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፏቸው የስሕተት ትምህርቶችና በሌሎችም መምህራን የተላለፉ ነቀፋ ያለባቸው ትምህርቶች ካሉ የሊቃውንት ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አንጻር በሚገባ መርምሮና አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብ፣
4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኝ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር ሚዲያ የአየር ሰዓት የሰጠበትን ዝርዝር ሁኔታና ከማኅበሩ ጋር በተያያዘ አየር ላይ ያዋላቸውን ትምህርቶች የሚያሳይ ሪፖርት እንዲያቀርብ ይደረግ በማለት ቋሚ ሲኖዶስ ወስኖ የዕለቱን ጉባኤ በቅዱስነታቸው ጸሎተ ቡራኬ አጠናቋል።
ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

❤1🔥1👏1
“ዳግመኛ እርሱ እንደ ሞተ፣ በሦስተኛውም ቀን እንደ ተነሣ፣ ስለ ተነሣም ሥጋው የማይፈርስ የማይበሰብስ፣ የማይታመም፣ የማይሞት እንደ ኾነ እናምናለን፡፡ ሥጋውም ከእርሱ ጋር አንድ ኾኖ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአርያም በልዑል ዙፋኑ ተቀመጠ፡፡ ዳግመኛም በሙታንና በሕያዋን ይፈርድ ዘንድ ዂሉ አንድ ኾኖ በሚነሣበት ጊዜ እርሱ በጌትነት ይመጣል፤ ለዂሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል፡፡ እኛ በእነዚህ ቃላት ሳናወላውል ጸንተን እንኖራለን፤” (ቅዱስ ዲዮናስዮስ፣ ሃይ. አበ. ፺፱፥፴፪)፡፡
🥰2👍1
'' እንደ ጋኔን ቅናተኛ የለም። ቅናቱ ግን በሰው ልጆች ላይ እንጂ እርሱን በሚመስሉ አጋንንትን ላይ አይደለም። ሰው ግን በገዛ ወንድሙ ላይ ይቀናል።'' ( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )
@WwEotc
@WwEotc
👏2
" ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።"(የዮሐንስ ወንጌል 14:6)
ኢየሱስ የአብን አምላክነት የምንረዳበት የምናውቅበት እውነተኛ መንገዳችን ነው። አስቀደምን የኢየሱስን አምላክነት ካልተረዳንና ካልተቀበልን የአብን አምላክነት ልንረዳና ልንቀበል አንችልም፥ ለዚህ ነው '' በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም'' ያለው - የእኔን አምላክነት ሳታምኑና ሳትቀበሉ የአብን አምላክነት ልትረዱ ልትቀበሉ አትችሉም ሲለን ነው።

🥰3🔥1