ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
1.5K subscribers
1.09K photos
20 videos
13 files
247 links
Download Telegram
'' እግዚአብሔር ትንሽ ይናገራል ብዙ ያደርጋል፥ እኛ ግን ብዙ እንናገራለን ጥቂት እንሰራለን።'' ( ቅዱስ ሳዊሮስ )

@WwEotc
👏3
የተወደደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የጌታዬ እናት ለማለት መንፈስ ቅዱስ ሊያነሳሳህ ይገባል። ልክ እንደ ቅድስት ኤልሳቤጥ።

እርሷን የጌታዬ እናት ስንል ሁለት ነገር እየመሰከርን ነው። አንድ እርሷን የጌታ አምላክ እናት መሆኗን። ሁለት ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ አምላክ እንደሆነ።

@WwEotc
❤2
በዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 11 ንዑሰ ክርስቲያን ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ !

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን !

አሜን !
👍3🥰2👏1
" ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።"(ዮሐ 3:13)
ሰማይ የተባለው ክብሩ ነው። አዎ በስልጣኑ በሀይሉ ወደ ሰማይ ያረገው የወጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። " አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።"(መዝ 47:5) ቅዱሳን ወደ ሰማይ ቢወጡ ቢያርጉ በእግዚአብሔር ስልጣን ነው። አስቡት በአንድ ቀን እንኳ ቅዱሳን መላዕክት ወደ ሰማይ ይወጣሉ ይወርዳሉ። " ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፥ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ። "(ትንቢተ ኢሳ 6:6)--" ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ። "(ዳን 9:21) "13 በአልጋዬም ላይ በራሴ ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ አንድ ቅዱስ ጠባቂ ከሰማይ ወረደ። "(ዳን 4:13) እንዲል።
አንድም " ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።" ማለቱ ከሰማይ ከወረደው በቀር - በፍቃዱ ከሰማያት ወርዶ ከተወለደው #ከኢየሱስ በቀር - ወደ ሰማይ - ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም #ሰማይ የተባለችው እመቤታችን ናትና - የወጣ የለም - በማህጸኗ ያደረ የተወለደ የለም ማለቱ ነው። ይህም ጌታችን የእመቤታችንን ዘላለማዊ ድንግልናዋን መሥክሯል።
ይቆየን።

ቤተሠብ ይሁኑን 👉 @wwEotc
👍3🔥2
ታላቁ አባት ጌታ አምላክ ኢየሱስ የአለም ብርሃን ነው። ይህ ብርሃንነቱ ከራሱ የሆነ ማለትም የባህርይ ነው። ቅዱሳንን ደግሞ እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ ብሏቸዋል። የእነርሱ ብርሃንነት የጸጋ ወይም ከኢየሱስ ያገኙት(የተሰጣቸው) ነው።

ቅዱሳን የአለም ብርሐን ቢባሉ ወንጌልን በመስበክ ጨለማው አለም ስላበሩልን ነው።

እመቤታችን የአለም ብርሐን ብትባል ራሱን ብርሃን የተባለውን ኢየሱስን ስለወለደችው ነው።

ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ።

@WwEotc
👏3👍1🥰1
ጥያቄ:- ድንግል ማርያም ስለ ተወለደች “ልደታ” እያሉ መደሰት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን? አምላክን እንጂ ድንግል ማርያምን ማመስገን ተገቢነቱ እንዴት ነው???

ክብረ ነክ የሆነውን የመናፍቃኑን አጠያየቅ፤ በጨው እንደ ተቀመመ ቀይሬ ያቀረብኩት እኔ እንጂ፤ እነርሱ እንዲህ በክብር እንደማይጠይቁ የታወቀ ነው::
መልስ:- አዎ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለተወለደች ሁላችን ደስስስስ…. ስለሚለን የተወለደችበትን ቀን በማስታወስ ‹‹ልደታ ማርያም›› በማለት ሐሴት እናደርጋለን:: እርሷስ ዓለምን ሁሉ የሚያድንን ፈጣሪ ለመውለድ በመታጨትዋ ነው:: መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ አምላክን ለማጥመቅ መንገድ ጠራጊ ሆኖ ስለሚወለድ:- "በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል" ከተባለ፤ አምላክን በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ጸንታ፤ በድንግልና የምትወልደው ወላዲተ አምላክ በመወለድዋ፤ እንዴት አንደሰት? ሁላችን አብልጠን እንደሰታለን:: ምስጋናም እናቀርብላታለን /ሉቃስ 1፥14/፡፡

የባህርይ ምስጋና የሚቀርበው ፈጥሮ ለሚገዛን አምላክ ብቻ ነው "አምላካችን ሆይ፥ እንገዛልሃለን፥ ለክቡር ስምህም ምስጋና እናቀርባለን" /1ኛ ዜና 29፥13/፡፡ ወላዲተ አምላክን የምናመሰግነው ከፍጥረታት በላይ፤ ምልዕተ ጸጋ እርሷ ብቻ በመሆንዋ ነው፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ኤፍሬም:- "ኩሉ ትውልድ ያስተበፅኡኪ ለኪ ለባሕቲትኪ ኦ እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ /አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንችን ብቻ ያመሰግኑሻል/" ብሎ በረቡዕ ውዳሴ ማርያም ያመሰገናት፡፡
መናፍቃን ባልተረዳ አእምሮአቸው የምናደርገውን ሳይጠይቁን፤ በራሳቸው አሳብ እየተነዱ "እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ" እንደተባሉት ሆነዋል /ሮሜ 1፥21/፡፡

በተአምረ ማርያም “አዳምና ሔዋንም እመቤታችንን ከእነርሱ ልትወለድ ተፈጠሩ፤ ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ” ተብሎ ተጽፏል:: ይህ ቃል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓለም ሳይፈጠር በፊት በአምላክ ሕሊና ታስባ ስለተመረጠች እናም ፍጥረታትን ለማዳን ከእርሷ ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍስዋ ነፍስን ነሥቶ ስለሚወለድ፡፡ አዳም እና ሔዋን ይህንን እያሰቡ፤ ከእኛ ባህርይ የምትወለድ በልጃችን አምላክ ያድነናል እያሉ፤ በትንቢት መነጽር እንዳመሰገኑአት ለመጥቀስ ነው::

እንኳን እመቤታችን ሐዋርያትም የተመረጡት፡- “ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን፤ በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን” እንዳሉ ማስታወስ በቂ ነው /ኤፌ 1፥4/::
አዳምና ሔዋን አመሰገንዋት አከበሩአት ማለት አስቀድሞ ዓለም ሳይፈጠር ከእርስዋ እንደሚወለድ ስለወሰነ ቃል ኪዳኑ ስለነገራቸውም ልጃቸውን አወደሱአት ማለት ነው:: ይህ ውሳኔ በሐዋርያትም ተጠቅሷል "አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው" እንዳለው አይነት ነው /ሮሜ 8፥29-30/::

አዳም በምን ትንቢት እንዳወደሳት እንስማ:- "የሕያዋን ሁሉ እናት" አላት፡፡ ይህንን ለጊዜው ሚስቱን ሔዋን የጠራበት ስያሜ ነው /ዘፍ 3፥20/ ምሥጢሩ የተፈጸመው ግን በተስፋቸው በድንግል ማርያም በኩል ነውና እናመሰግናታለን።

ይቆየን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❤3👍3🔥2
አባትሽ ሰሎሞን ሁለንተናሽ ውብ ነው በማለት የነፍስና የሥጋ ንጽሕናዋን መሰከረ!

ልደትሽ ልደታችን ነው።
🔥6❤3
በአለም ላይ በብቸኛ የሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ያላት ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክስ ብቻ ነች። ኦርቶዶክስ ስል በኢትዮጵያ አትወስኑት በአለም ላይ ያለችው የጌታ ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን ነው ።

ኦርቶዶክስ ስለሆን እግዚአብሔር ይመስገን።

@WwEotc
👏9
" እንደ ኢየሱስ ያለን መልካም እረኛን ይፈልጉታል።"
( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው በሽተኛ ይፈውስ ነበረ። ጥላ ምንድነው? ጥላ በመሰናክል አካል ምክንያት ብርሀን የማያገኝ ቦታ ነው። ይህ ቦታ ብርሀን አስተላላፊ ካልሆነ አካል በስተጀርባ ይገኛል። #ይህ_ጥላ_የሚፈጥረው_ቅርፅ_ብርሀን_እንዳያልፍ_ያደረገውን_አካል_ግልብጥ_ምስል_ነው ። ማለትም ራስኑን ቅርጽ በጥቁር ቀለም መልክ ማለት ነው።

ጥላን ወደ ስነ-ጥበብ ስንመጣው ደግሞ Shadow Art በሚባል የአሳሳል ጥበብ እናኘዋለን። ጥቁር ቀለምን ብቻ በመጠቀም አንድን አካል አስመስሎ የመሳል ጥበብ ነው። የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ ልክ እንደ Shadow art ነው በተፈጥሮ ብርሃን በምደር ላይ የተሳለ ፥ ይህንን ጥቁር ጥላ ከነቅርጹ በደንብ ሙያ ተጨምሮበት በቀለም አሳምሮ በመሳል የባለቤቱን ገጽታ ማምጣት ይቻላል። በመሬት ላይ ያረፈው ጥላ መፈወሱ ፤ በክብር በሸራና በተለያዩ አካላት ላይ ምሥጢርን፥ ሥርአትን ጠብቀው የተሳሉ ስዕላት እንደሚፈውሱ የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ነው።
❤2👍2
ሰይጣን ( እርኩስ መንፈሱ ) ተጠምቆ ክርስቲያን ሆነና ገነት ገባ የሚል የቤተክርስቲያን ትምህርት የለም። ታዲያ በገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት ላይ የተጠቀሰው ምንድን ነው ቢሉ :-

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያጠመቁት የሰው ልጅን ነው። ነገር ግን ያ ሰው ከምግባሩና ከውሎው የተነሳ ሰይጣን ተባለ። እንደዚህ አይነት ሰዎች በምትሓት በእሳት ላይ ይራመዳሉ ፤ እሶኸ ላይ ይተኛሉ ፤ ባህር ውስጥ ይኖራሉ ወዘተ...

ስለዚህ እንዲህ ከእርኩስ መንፈስ ጋር ይኖር የነበረውን ሰው አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጠመቁትና ክርስቲያን አደረጉት። አንዳንዶች ግን ይህንን ታሪክ በመቀየር ለራሳቸው አላማ ሲጠቀሙ እናያለን። እኛ ግን እውነትን እንመሰክራለን።

የጻድቁ በረከት አይለየን።

@WwEotc
👍5
ቅዱስ ዑራኤል - የከበረው መልአክ

የህይወትን ጽዋ ለአበው የሚያጠጣቸው እርሱ ነው።

የጌታ አምላክ ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በምድሪቱ የረጨ እርሱ ነው።

ጌታ አምላክ ኢየሱስ ሲወለድ በአብሪ ኮከብ ተመስሎ 3ቱን ነገስታት ወደ ቤተልሄም የመራቸው እርሱ ነው።

በሐዲስ ኪዳን እንደተጻፈው በመጠመቂያው ቦታ መልአኩ ሲገባ ውሃው ይነዋወጽ ነበረ ቀድሞ የገባውም የታመመ ሰው ከያዘው በሽታ ሁሉ ይድን ነበረ። ያ ውሀውን የሚቀድሰው መልአክ ዑራኤል እርሱ ነው።

ጌታ ኢየሱስ በዚህ በከበረ መልአክ ምልጃ ይማረን። አሜን።

@WwEotc
🔥3
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ ሁለት በዚህች ቀን የመነኮሳት ሁሉ አለቃ ሐዋርያና ሰማዕት የታላቁ መምህር የቅዱስ አባታችን ተክለሃይማኖት የሥጋው ፍልሰት ሆነ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን አሜን።
❤5
• ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱሥ አንድነት ሣይለይ በምልአት ሣለ ሥጋ መሆኑ እንደምን ነው? ቢሉ የዓይን ብርሃን ከአይን ብሌን ሣይለይ ከብርሃነ ፀሀይ ጋር ተዋህዶ ምሉዕ እንደሆነ ጌታም በመልአተ ባሕርዩ ሣለ በመኀፀነ ድንግል አድሮ ከመቅጽበት ዓይን ሠው ሆነ፡፡ የማይለይ የማይነገር የማይመረመር ተዋህዶ ሆነ፡፡
❤6👏2
'' ሶስት ሲሆን አንድ አንድ ሲሆን ሶስት በአካል ሶስት ሲሆን በመለኮት አንድ ለሚሆን አምላክ እሰግዳለሁ።'' ( የዘወትር ጸሎት )

#ሥላሴ_አምላኬ
❤7👍1🥰1
'' እግዚአብሔር ከዓለም በፊት እስከ ዘለዓለምም ድረስ፤ እግዚአብሔር በሦስትነቱ አለ፣ እግዚአብሔር በመለኮቱ፣ እግዚአብሔር በመንግስቱ አለ።'' ቅዱስ ዲዮስቆሮስ
❤5🥰2