ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
1.5K subscribers
1.09K photos
20 videos
13 files
247 links
Download Telegram
'' ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።'' ( መዝ 8:2)
❤1
“ጌታ ቅርብ ነው ፤ በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።” ፊልጵስዩስ 4፥6
👏8
❤ በይስሐቅ ፋንታ ኢየሱስ ታረደ ❤

#ይስሐቅ = " አባቴ ሆይ! የመስዋዕቱ በግ ወዴት ነው? " ማለቱ የዓለም መድኃኒት የሚሆነው አማናዊው በግዕ/ክርስቶስ ኢየሱስ ወዴት ነው ማለቱ ነው።

#አብርሃምም = "" ልጄ ሆይ! የመስዋዕቱን በግስ
#እግዚአብሔር ያዘጋጃል።" አለው። ይህም ራሱ መስዋዕት ሆኖ የሚያድንንማ ራሱ ወልደ እግዚአብሔር ነው እንደማለት ነው።

" በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ። እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።" (ዮሐ 1:29)

ይስሐቅ እንጨት ተሸክሞ ተራራን መውጣቱ ፤ የድንግል ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልን ተሸክሞ ተራራን ይወጣል ሲለን ነው።

❤ በይስሐቅ ፋንታ ኢየሱስ ታረደ ❤
🥰3❤2
" Many rich and powerful men would pay dearly to see the Lord or His Most Pure Mother, but God does not appear in riches, but in the humble heart... Every one of the poorest men can be humble and come to know God. It needs neither money nor reputation to come to know God, but only humility. "
(St. Silouan the Athonite, Writings, I.11,21)
🥰2❤1👍1
Do not say, "this happened by chance, while this came to be of itself." In all that exists there is nothing disorderly, nothing indefinite, nothing without purpose, nothing by chance ... How
many hairs are on your head? God will not forget one of them. Do you see how nothing, even the smallest thing, escapes the gaze of God? (St. Basil the Great)
❤1
'' ሶስት ሲሆን አንድ አንድ ሲሆን ሶስት በአካል ሶስት ሲሆን በመለኮት አንድ ለሚሆን አምላክ እሰግዳለሁ።'' ( የዘወትር ጸሎት )

#ሥላሴ_አምላኬ
❤2
ዝሙት፣ ሥካር፣ ዘፈን፣ ሰውን መበደል፣ ጣኦት አምልኮ
🥰1
🔵🔵🔵 44ቱ ታቦት 🔵🔵🔵
"44ቱ ታቦት የሚባለው አነጋገር ልብዙዋች ጥያቄ ነው። ብዙ ጊዜ ለነቀፋና ለትችት 44ቱ ታቦት ሲባል ይሰማል ስለዚህ ነገር የሆነ ጠንከር ያለ መረጃ ያስፈልገናል .....
➨ብዙ ጊዜ ይህ ስም በተደጋጋሚ ይጠቀሳል በተለይ ከተቺዎች። 44ቱ ታቦት በጎንደር የሚገኙ ታቦታት ናቸው።
ጎንደር በአጼ ፋሲል በ16ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከመመስረቷ(ከመቆርቆሯ)በፊት በአካባቢው አራት ደብሮች ነበሩ
🛑 ጓንደር ከተመሰረተች በኋላ ከአጼ ፋሲል እስከ ተክለ ጊዮርጊስ የተነሱ 18 ነገስታት እየተፈራረቁ አድባራትንና ገዳማትን አሳንጸዋል። በዚ ሂደት እነዚህ ነገስታት 30 ደብራት ተከሉ።
🛑14 ያህሉ ቀድሞ የነበሩ ነበሩ። እነዚ ተደምረው ጎንደር የ44 ታቦት መገኛ ሃገር ተባለች።
➨ይሄ ከ1772-1777 የተተከሉት የጎንደር አድባራት ብቻ ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ከ92 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ። ከ1777 በኋላ የታነጹ ብዙ አድባራት ቢኖሩም ነገር ግን እስከ ዛሬም ከ1772-1777 ድረስ ብቻ የታነጹት 44ት አድባራት(ታቦታት) ስማቸው ይነሳል።
🎯ማጠቃለያ
ይህ 44ቱ ታቦት የሚለው ስያሜ የሚገልጸው ከ1772-1777(ከአጼ ፋሲል እስከ ተፍጻሜ መንግስት ተክለ ጊዮርጊስ)ድረስ በጎንደር የነበሩትን ታቦታት ብቻ እንጂ በሰዓቱም ሆነ በአሁን ጊዜ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ታቦታት ብዛት አይገልጽም። አይደለም በመላው ኦርቶዶክስ ፣በጎንደር በአሁኑ ጊዜ እንኳን ያለውን አይገልጽም።ምክንያቱም በየዘመናቱ አዲስ ቤተመቅደስ ሲታነጽ አዲስ ታቦት ተቀርጾ በሃገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ በሜሮን ከብሮ ወደ መንበረ ክብሩ ይገባል። አገልግሎቱ ለሰው ልጅ ሁሉ መዳረስ አለበትና።
🛑➨የ44ቱ ታቦታት ደብር ስም ዝርዝርና ያሳነጹት ነገስታት ስም ዝርዝር
1. አዘዞ ተክለ ሃይማኖት
/በአጼ ሱስንዮስ/
2. ፊት አቦ
/በአጼ ፋሲል/
3. ፊት ሚካኤል
/በአጼ ፋሲል/
4. አደባባይ ኢየሱስ
/በአጼ ፋሲል/
5. ግምጃ ቤት ማርያም
/በአጼ ፋሲል/
6. እልፍኝ ጊዮርጊስ
/በአጼ ፋሲል/
7. መ/መ መድኃኔዓለም
/በአጼ ፋሲል/
8. አቡነ ቤተ ገብርኤል
/በአጼ ፋሲል/
9. ፋሲለደስ
/በአጼ ሰሎሞን/
10. አባ እንጦንስ
/ጻድቁ ዮሐንስ/
11. ጠዳ እግዚአብሔር አብ
/ጻድቁ ዮሐንስ/
12. አርባዕቱ እንስሳ
/አቤቶ አርምሐ/
13. ቀሐ ኢየሱስ
/የአገሬው ትክል/
14. አበራ ጊዮርጊስ
/የአገሬው ትክል/
15. አደባባይ ተክለ ሃይማኖት
/አዲያም ሰገደ ኢያሱ/
16. ደብረ ብርሃን ሥላሴ
/አዲያም ሰገደ ኢያሱ/
17. ዳረገንዳ ኤዎስጣቴዎስ
/አድባር ሰገደ ዳዊት/
18. አጣጣሚ ሚካኤል
/አድባር ሰገደ ዳዊት/
19. ጎንደር ሩፋኤል
/አጼ በካፋ/
20. ደፈጫ ኪዳነ ምህረት
/አጼ በካፋ/
21. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
/ራስ ወልደ ልዑል/
22. ጎንደር ልደታ ማርያም
/አጼ ዮሐንስ/
23. ሠለስቱ ምዕት
/አጼ ቴዎፍሎስ/
24. ጎንደር በዓታ ለማርያም
/መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት/
25. ወልደ ነጎድጓድ ዮሐንስ
/መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት/
26. ጎንደር ቂርቆስ
/መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት/
27. ጎንደር ሐዋርያት(ጴጥሮስ ወጳውሎስ)
/መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት/
28. ፈንጠር ልደታ
/መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት/
29. ሰሖረ ማርያም
/መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት/
30. ወራንገብ ጊዮርጊስ
/መናኔ መንግሥት ተ/ሃይማኖት/
31. ምንዝሮ ተክለ ሃይማኖት
/አጼ ሠርፀ ድንግል/
32. ደብረ ጸሐይ ቊስቋም
/እቴጌ ምንትዋብ/
33. ደብረ ምጥማቅ ማርያም
/ፈጻሜ መንግስት ተ/ሃይማኖት/
34. አባ ሳሙኤል
/ፈጻሜ መንግስት ተ/ሃይማኖት/
35. ጎንደሮች ማርያም
/የአገሬው ተክል/
36. ጎንደሮች ጊዮርጊስ
/የአገሬው ተክል/
37. አባ ጃሌ ተክለ ሃይማኖት
/ደጃች ወንድወሰን/
38. ዐቢየ እግዚአብሔር ኪዳነ ምህረት
/ራስ ገብሬ/
39. ብላጅግ ሚካኤል
/የአገሬው ተክል/
40. አሮጌ ልደታ
/የአገሬው ተክል/
41. ጫጭቁና ማርያም
/የአገሬው ተክል/
42. ጋና ዮሐንስ
/የአገሬው ተክል/
43. አይራ ሚካኤል
/የአገሬው ተክል/
44. ዳሞት ጊዮርጊስ
/የአገሬው ተክል/
❤4👍1
በእስክንድርያ ከተማ ክላወባጥራ የተባለች ንግሥት የበጥሊሙስ ልጅ ዙሐል በሚባል ኮከብ ስም ያሠራችው ታላቅ ምኲራብ ነበር፤ ሕዝቡም ሰኔ በገባ በዐሥራ ሁለት የዚህን ጣዖት በዓል ያከብሩ ነበር። ይህንም ግብራቸው እንዲተው አባታችን እለ እስክንድሮስ ቢነግራቸው አይሆንም አሉት።

በኋላም ጻድቅ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሲነግሥ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኃዋ ወአብያተ ጣዖታት ይትዐፀዋ የሚል አዋጅ ስለወጣ በዚህ ምቹ ጊዜም የጣዖት አምልኮ እንደምን ያለ ክፉ ግብር እንደሆነና በጎ ዋጋም እንደሌለው ነግሮ እንዲተዉ ቢጠይቃቸው እኛስ ይህን አንተውም አሉት። እርሱም በጥበብ እንዲህ አላቸው፤ ‹‹ይህን ግብር ብትተው በዚህች ቦታ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ቤተ ክርስቲያን እንሠራለን። መሥዋዕታችሁንም በዚያ ለቅዱስ እግዚአብሔር ታቀርባላችሁ አላቸው።›› በዚህ ተደስተው ተመለሱና ያንን የጣዖት ቤት አፍርሰው እጅግ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ስም ሠሩ። የመልአኩንም በዓለ ንግሥ በዚህች ዕለት አከበሯት። ከዚያን ጊዜም ጀምሮ የከበረ የመላእክት አለቃ የመልአኩ የሚካኤል የመታሰቢያውን በዓል በሰኔ ዐሥራ ሁለት ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይከበራል፡፡

ንዑድ ክቡር የሚሆን የዋህ ተአዛዚ ባሕራንን በሰኔ ዐሥራ ሁለት ቀን ያዳነበት ድንቅ ተአምርም ይህ ነው። አንድ ደግ ሰው በዚያች ይኖር ነበር። ክፉ ጎረቤት ነበረው። ይህም ደግ ሰው ነዳያንን እጅግ የሚወድ የቅዱስ ሚካኤልንም ዝክር ሳያስታጉል የሚዘክር ሰው ነው። በዚህ ሥራው ግን ይህ ክፉ ጎረቤቱ ይዘብትበት ነበር። በኋላም ያ ደግ ሰው የሚሞትበት ቀን ሲደርስ ሚስቱን ዝክረ ሚካኤልን እንዳታቋርጥና ነዳያንን እንዳትዘነጋ ነግሯት ያርፋል። እርሷም ፀንሳ ነበርና እርሱ ከሞተ በኋላ የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ። ምጥም ቢጠናባት ወደ መልአኩ ጮኸች፤ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ተራዳትና መልከ መልካም የሆነ ልጅ ወለደች። መልአኩም እንዲህ ሲል አላት። ‹‹ልጅሽ የዚህ የጎረቤትሽን ሀብት ይወርሳል።›› መልአኩም ለጎረቤታቸው ጆሮውንም ከፍቶለት ነበርና ይህን ነገር ሰማ። በዚህም ‹‹በምን ምክንያት ወስጄ ላጥፋው›› ብሎ ሲያስብ ሴቲቱ እጅግ ብቻዋን ለማሳደግ ተቸገረች፤ ‹‹ላሳድግልሽ፤ ለአንቺም ይኸው ገንዘብ እሰጥሻለሁ›› ብሎ ብዙ ወርቅ ሰጣት። እርሱም ‹‹ከእንግዲህ አርፋለሁ›› ብሎ ልጁን መጣያ ሳጥን ያዘጋጅና ወደ ባሕር ይጥለዋል። ባሕሩም ሩቅ ሀገር ወስዶት ከዳር ይጥለዋል፤

ከዚህም በኋላ አንድ በጎቹን ያሠማራ ሰው ያገኘዋል። ያንንም ሳጥን ወስዶ ከቤት ያኖረዋል፤ በምን መክፈት እንደሚችል ሲያስብ ዳግመኛ ወደ ባሕሩ እንዲሄድ እግዚአብሔር ሐሳብ ያሳድርበትና ተነሥቶ ይሄዳል። ሲሄድም ዓሣ አጥማጅ ያገኝና ዓሣ ለእርሱና ለቤተሰቡ እንዲያጠምድለት ይነግረዋል። ያም ዓሣ አጥማጅ ሲያጠምድ ታላቅ ዓሣ አገኘና ሰጠው። ዋጋውን ሰጥቶም ወደ ቤት ተመለሰና ሆዱን ቢሰነጥቀው ቁልፉን በዚያ አገኘው። በዚያም ቢከፍተ መልከ መልካም ልጅ አገኘ። ልጅም ስላልነበረው እጅጉን ተደሰተ። ባሕራን ብሎም ሰየመው።

ከብዙ ጊዜያት በኋላ ያ ክፉ ሰው ከንግድ ተመልሶ በዚያ መንገድ ሲያልፍ መሸበትና ከዚህ ሰው ቤት አደረ። ባሕራንንም ተመለከተውና ሰውየውን ልጁ እንደሆነ ለማወቅ ታሪኩን ጠየቀው፤ ሰውየውም የሆነውን ሁሉ ነገረው። ክፉ ሰውም እንዳልሞተ ባወቀ ጊዜ ደነገጠና መልእክት ሊልከው ስለሚፈልግ የባሕራንን አባት ልጁን እንዲሰጠው ጠየቀው። እርሱም ተስማምቶ ሰጠው። በክፋትም ተነሣሥቶ ባሕራንን እንዳገኘው እንዲገድለው ለአገልጋዩ ደብዳቤ ጽፎ አገልጋዩና እርሱ ብቻ የሚያውቁትን ማኅተም አድርጎ ሰጠው። ‹‹ይቺን ደብዳቤ በምታነባት ጊዜ ደብዳቤዋን ይዞ የመጣውን ገድለህ በጉድጓድ ውስጥ ጣለው፡፡ ማንም ዐይወቅ፡፡›› ለባሕራንም ለመንገዱ የሚሆነውን ስንቅ ሰጠው፡፡

የራሱን የሞት ደብዳቤ እንደያዘ ሳያውቅም ባሕራን ወደታዘዘበት ሥፋራ ተጓዘ፤ ከዚያ ሰው ቤት ለመድረስ ሲቀርብ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ‹‹አንተ ጐልማሳ የያዝኸው ምንድነው›› አለው፡፡ ‹‹ወደ ዕገሌ ሀገር ወደ ቤቱ ለማድረስ ከአንድ ባለ ጠጋ የተጻፈች መልእክት ናት›› አለው፡፡ ‹‹ያቺን ደብዳቤ አሳየኝ›› አለው፤ እርሱም ስለ ፈራ ሰጠው፡፡ የሞቱን ደብዳቤ ያቺን የሞት መልእክት ደምስሶ በሕይወት ቀየረለት። በእርሱም ፈንታ በንፍሐት ለውጦ እንደህ ብሎ ጻፈ፤ ‹‹ይቺን ደብዳቤ ይዞ ለመጣ ባሕራን ለሚባል ሰው ይቺ ደብዳቤ ደርሳ በምትነበብበት ጊዜ ልጄ ዕገሊትን አጋቡት፡፡ በውስጥና በውጭ ያለ ንብረቴንና ጥሪቴን፣ ወንዶችና ሴቶች ባሮቼን፣ ጠቅላላ ንብረቴንም አውርሼዋለሁና የፈለገውንም ሊያደርግ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና እኔን አትጠብቁኝ፡፡ እኔ ብዙ እዘገያለሁ የኔ ሹም እገሌ ሆይ! በእኔና በአንተ መካከል ይቺ ምልክት እነኋት፡፡››

አሽጐ ለባሕራን ሰጠውና ‹‹ወደ ባለ ጠጋው ቤት ሂደህ ይቺን ደብዳቤ ለሹሙ ስጠው፡፡ በጎዳናም እኔ እንደ ተገናኘሁህ አትንገረው፡፡ እንዳይገድልህም ይህን የሞት ደብዳቤ ለውጬልሃለሁ›› አለው፡፡ ባሕራንም ‹‹እሺ ጌታዬ ያዘዝኸኝን ዅሉ አደርጋለሁ›› አለ፡፡

ባሕራንም ወደ ባለ ጠጋው ቤት በደረሰ ጊዜ ያቺን ደብዳቤ ለሹሙ ሰጠው፡፡ ካአነበባት በኋላም በመካከላቸው ያለውን ምልክት አገኘ፡፡ አስተውሎም እርግጠኛ እንደ ሆነ ዐወቀ፡፡ ለባሕራን ሠርግ አዘጋጅቶ እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት በተክሊል የባለ ጠጋውን ልጅ አጋቡት፡፡ ዐርባ ቀን ያህልም ደስታና ሐሴት እያደረጉ ኖሩ፡፡ ሀብቱንም ሁሉ አወረሱት።

ከዚህ በኋላ ባለ ጠጋው ከሄደበት ሲመለስ ጊዜ በደስታ የሆነውን የመሰንቆና የእንዚራ ድምፅ ሰምቶ ‹‹ይህ የምሰማው ምንድነው›› ብሎ ጠየቀ፡፡ እነርሱም ‹‹ስሙ ባሕራን ለተባለ የአንተን ደብዳቤ ላመጣ ጐልማሳ ሰው ልጅህ ዕገሊትን አጋቡት፡፡ እነሆ ለዐርባ ቀናት በሠርግ ላይ ነው፡፡ ገንዘብህንና ጥሪትህን ሁሉ ወንዶችና ሴቶች ባሮችህን አንተ እንዳዘዝኽ ሰጥተውታል›› አሉት፡፡ ይህንም በሰማ ጊዜ ደንግጦ ከፈረሱ ላይ ወደቀ በድንገትም ሞተ፡፡

ባሕራንም ከዚህ በኋላ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር በሚገ’ባ እየዘከረና ለቤተ ክርስቲያኑም እየታዘዘ የሚያገለግል ሆነ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የዚህም የከበረ መልአክ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን፤ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
❤2🔥1
በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ቁጥራቸው ያልታወቀ በዋሻ የሚኖሩ መነኮሳት በታጣቂዎች ተገደሉ።

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኘው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚኖሩ መነኮሳት ሰኔ 15/ 2017 ዓ.ም. በታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን የተወሰኑ ታፍነው መወሰዳቸውን ገዳሙ ገልጿል።

ስለተገደሉ እና ታፍነው ስለተወሰዱ መነኮሳት ቁጥር እና ዝርዝር ጉዳይ አጣርተን መረጃዎችን የምናደርስ ይሆናል።

የካቲት 2016 ዓ.ም ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ በገዳሙ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መድረሱ የሚታወስ ነው።

©️ ማኀበረ ቅዱሳን
😢6
በሀገረ ቂሣርያ፣ ኬልቄዶንያ አውራጃ የመጀመሪያዋ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የታነጸችበት ዕለት ሰኔ ፳፩ ‹‹ሕንጸታ ቤታ›› የተከበረ ነው፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ እንጨት፣ ያለ ጭቃና ያለ ውኀ በሦስት ድንጋዮች ቤተ ክርስቲያኗን ያነጸበት ዕለት ነውና፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የዚህችም የከበረች ድንግል ማርያም የረድኤቷ ኃይል ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን፤ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
❤4
እግዚአብሔር ከሃሊ ነው።

ከሃሊ ማለት ሁሉን የሚችል፣ በፍጡር ዘንድ ፈጽሞ የማይቻልን ሁሉ ማድረግ የሚችል፣ ለችሎታው ወሰንና ገደብ የሌለበት፣ ይህን ይችላል ያን ግን አይችልም የማይባል ፍጹም ከሃሊ ማለት ነው። እግዚአብሔር፣ ሁሉም ነገር ከሥልጣኑ በታች በመሆኑ ሁሉም ይቻለዋል።

ይህን አስመልክቶ በዕብራይስጡ ቃል «ኤልሻዳይ» ተብሎ ተሰይሟል፤ ሁሉን የሚችል ማለት ነው። እግዚአብሔር ለአብራም በተገለጠለት ጊዜ፣ ከሃሊነቱን በሚያረጋግጥ ቃል እንደተገለጠለት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ያስተምረናል። «አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ፍጹምም ሁን። ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል አደርጋለሁ፤ እጅግም አበዛሃለሁ አለው።» ዘፍ ፲፯፥፩።

ፍጹም ከሃሊነት የእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥልጣን በመሆኑ እግዚአብሔር ፍጹም ከሃሊ ይባላል። «በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት ወደ አንተ እመለሳለሁ ሣራም ልጅን ታገኛለች።» ዘፍ ፲፰፥፲፬። «. . . ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው። ማቴ ፲፱፥፳፭-፳፮። ሉቃ ፩፥፴፭-፴፰።
❤4🔥1
የእግዚአብሔር ባህሪያት
፩ መንፈስነት
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፥17 ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።

፪ ዘላለማዊነት

፫ ሁሉን ቻይነት

፬ አለመለወጥ
ትንቢተ ሚልክያ – ምዕራፍ 3:6፤ እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።

፭ ምሉእነት
ትንቢተ ኤርምያስ 23:23 እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም።

፮ መለኮታዊ ጥበቃ
መዝሙር 138 ፥7 በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ፤ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ታድነኛለች።
ማቴ 10፥30 የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። ዘፍ ፴፯፥፲፰ ኢዩ ፩፥፲፪

፯ አዋቂነቱና ጥበቡ
ወደ ሮሜ ሰዎች 11:33 የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።

፰ ቅዱስነት

፱ ደግነት
መዝሙረ ዳዊት
86፥15 አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ መዓትህ የራቀ ምሕረትህም እውነትህም የበዛ፤
145፥8 እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቍጣ የራቀ፥ ምሕረቱም ብዙ ነው

፲ የማንንም እርዳታ አለመፈለጉ
ወደ ሮሜ ሰዎች 11 : 34 – 36
የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው፧
ወይስ አማካሪው ማን ነበር፧ ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው፧
ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
❤2🔥1
🌼 ዳንኤል 3:18 🌼

ለእግዚአብሔር መታመን ያለብን እርሱንም ማመስገን ያለብን ስላደረገልን
ብቻ አይደለም። እግዚአብሔር ቢያደርግልንም ይመስገን ፤ ባያደርግልንም ይመስገን።

በትንቢተ ዳንኤል ላይ ያለውም ይህ ነው። ሶስቱ ወጣቶች ወደ እሳቱ ሊጣሉ ባሉ ጊዜ እግዚአብሔር
ባያድነን እንኳ ለእርሱ ታምነን እንሞታለን ነው ያሉት። ግን እግዚአብሔር ከእሳቱ አዳናቸው።

ዳንኤል 3:18 ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ ባያድነንም እንኳ፤ አማልክትህን እንደማናገለግል ...
ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ ባያድነንም እንኳ፤ አማልክትህን እንደማናገለግል፣ ላቆምኸውም የወርቅ ምስል እንደማንሰግድ ዕወቅ።”
🥰2
ሰኔ ፴ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ልደት ነው።

ሊቁ ከመላእክት፣ ከነቢያት፣ ከካህናት፣ ከሐዋርያት መካከል እንደርሱ መለኮትን ለማጥመቅ የተመረጠ አለመኖሩን በመጥቀስ *ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ፤ እሳተ ነዳዴ ኢተክህሎሙ ያጥምቁ፤ ራጉኤል በትጋሁ ወኢዮብ በጽድቁ፤ ዮሐንስ ሆይ ራጉኤል በትጋቱ፣ ኢዮብም በጽድቁ ቢመኙም ሆነ ቢጨነቁ እንደ አንተ የሚነድ እሳትን (መለኮትን) ሊያጠምቁ አልተቻላቸውም* ሲል መስክሮለታል /መልክአ ዮሐንስ መጥምቅ፣ ለአዕይንቲከ/፡፡
❤2
ዮሐንስ ማለት *እግዚአብሔር ጸጋ ነው* ማለት ነው፡፡ ትርጓሜ ወንጌልም መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ፍሥሐ ወሐሴት (ተድላና ደስታ) ይለዋል፤ ወላጆቹ በእርሱ መወለድ ተደስተዋልና /ሉቃ.፩፥፲፬/፡፡
❤3