የሊቀ ዲያቆናት እስጢፋኖስ ምልጃው ይርዳን።
በተለይ ወጣቶች በእስጢፋኖስን ምልጃ መጠቀም አለብን።
እስጢፋኖስ ታላቅ አባት የኢየሱስ ምስክር የመጀመሪያው ሰማእት ነው።

🔥2
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
💥 ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሚወግሩት ሰዎች ከኢየሱስ ዘንድ ምህረትን ጠየቀላቸው - አማለዳቸው። 💥
ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማእትነትን ሊቀበል ባለ ጊዜ አይኑን ወደ ሰማይ ቀና ቢያደርግ ሥላሴን በክብሩ ተመለከተ።
'' መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፡— እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ፡ አለ።'' (ሐዋ. ሥራ 7:55-56)
ቅዱስ እስጢፋኖስ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ባለ ክብር ያየው ከትንሳኤ በኋላ ማለትም ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነውና በአባቱ ቀኝ ቆሞ አየው።
🌿 ስለሚወግሩትም ሰዎች እንዲህ ብሎ ጸለየ - ማለደ
''እስጢፋኖስም፡— ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል፡ ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም፡— ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። (ሐዋ.ሥራ 7:59-60)
❤ ተወዳጆች ሆይ 💥
እስጢፋኖስ ስለሚወግሩት ሰዎች ያለውን ልብ አላችሁ?
እስጢፋኖስ ኢየሱስ ክርስቶስን አማልዳቸው አላለውም - '' ኃጢአት አትቍጠርባቸው '' በማለት ከራሱ ከኢየሱስ ዘንድ አማለዳቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነውና ነፍስን ተቀበል ፣ ይቅር በል ይባላል። ኢየሱስ ክርስቶስ የሚማለድ የሚለመን ቅዱስ አምላክ ነው።
የሊቀ ዲያቆናት - ቀዳሜ ሰማእት የቅዱስ እስጢፋኖስ ምልጃው አይለየን 🌿 አሜን።

🔥3❤2
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ዐሥራ ስምንት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ ከትንሣኤው በሃምሳኛ ቀን ለደቀመዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስን የላከበት በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፣ የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ፣ የሰማዕት ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ፡፡

❤1🔥1
ልሳን ማለት ቋንቋ ማለት ነው ይህም ሰው ሊሰማው የሚችለው ቋንቋ። ሐዋርያት የተሰጣቸውም ጸጋ እንዱ ልሳን ነው። ዋና አላማውም ይህ ጸጋ የተገባቸው በአለም ሄደው ወንጌልን እንዲሰብኩ ነው።
❤4🔥1
ቅዱስ ቶማስ ህንደኛ ቋንቋ አይችልም ነበረ። ነገር ግን እግዚአብሔር የልሳን ጸጋ ስለሰጠው የህንድ ቋንቋ መናገር ቻለ። ወደ ህንድ ሄዶም ወንጌልን ሰብኳል። ዛሬም የህንድ ቤተክርስቲያን ለቶማስ ትልቅ ቦታ አላት።
❤3🥰3
On this day all Christian communities celebrate the festival of the appearance in public of our holy Lady, the Virgin Mary, the God-bearer, in Debre Mitmak. ነቢዩ ዳዊት ‹‹ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ›› በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት በርካት ቅዱሳን ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው ፊቷን ለማየትን ክብሯን ለመግለጥ ቅዱሳን አባቶች፣ ጻድቃን ሰማዕታት በቅተዋል፡፡ ይህም የሆነው በፍጹም ልቡናቸው በመማፀናቸውና በፍጹም ትጋት የጌታቸውን እናት ሲያገለግሉ በመኖራቸው እንደሆነ የጻድቃኑ ገድል ምስክር ነው፡፡ እነርሱም ሌት ከቀን ምኞታቸው ይሳካላቸው ዘንድ በጸሎት ይማፀኑ ነበር፡፡ (መዝ. ፵፬፥፲፪)
🔥1
ሰማዕታትም እንደየክብራቸው ማዕረግ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ሊሰግዱ ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው ወደ እርሷ ቀረቡ፤ በመጀመሪያ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሁሉም ቀድሞ ከሰገደላት በኋላ ሌሎቹም በተመሳሳይ መልኩ ሰገዱላት፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዮስ በዱሪ ፈረስ ተቀምጦ ወደ እርሷ በመምጣት ሰገደላት፡፡ ጻድቃን በአንድነት ቀርበው ለክብሯ ሰገዱላት፤ ቀጥሎም በንጉሥ ሄሮድስ በግፍ የተገደሉት ሕፃናት ለእርሷ ሰገዱ፤ በደስታና በፍቅርም ተጫወቱ፡፡ በዚያ የተሰበሰቡትም ክርስቲያኖች፣ እስላሞችና አረማውያን ይህን በአዩ ጊዜ ደስታ ሞልቶባቸው በተለየ ዓለም ያሉ ይመስላቸው ነበር፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰)
ግንቦት ሃያ አምስት በዚች ቀን አምላክን የወለደች የቅድስት ድንግል የእመቤታችን የአክስቷ ልጅ ብፅዕት ሰሎሜ አረፈች። እርሷም የማጣት ልጅ የሌዊ ልጅ የሚልኪ ልጅ የካህን አሮን ልጅ ናት።
👏1
ቅዱስ ኮጦሎስ
በዚህችም ቀን ከእንዴናው አገር የከበረ ኮጦሎስ በሰማዕትነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ እናትና አባቱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው አባቱም የእንዴናው ገዥ መኰንን ነው ልጅ አልነበረውም ይህን ቅዱስ ልጅ እስከ ሰጠው ድረስ ጌታችንን አዘውትሮ ይለምነው ነበር የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት አስተማረው።
ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ሆነ ለራሱም ሥርዓት በመሥራት በቀን መቶ እንዲሁ በሌሊትም መቶ ጸሎታትን ይጸልያል። ጥቂት በአደገ ጊዜም ወላጆቹ ሊአጋቡት ፈለጉ እርሱ ግን አልፈቀደም። ነገር ግን ከእርሱ በኋላ የተወለደች ሴት ልጅ ነበረቻቸውና እርሷን ከአርያኖስ ጋራ አጋቧት።
አባቱም ከሞተ በኋላ ለስደተኞች የእንግዳ መቀበያ ቤት ሠርቶ ስደተኛውንና እንግዳ መቀበልን ጀመረ። ከዚህም በኋላ የጥበብ መጽሐፍ ተምሮ ሐኪም ሆነ። በሽተኞቹ ሁሉ ወደ ርሱ ይመጣሉ እርሱም ያለ ዋጋ ይፈውሳቸዋል።
ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ አርያኖስ ስለ ሹመቱ ከንጉሡ ጋራ ተስማምቶ ሰማዕታትን የሚያሠቃያቸው ሆነ። ይህ ቅዱስም ሰማዕት ለመሆን ይተጋ ነበር ወደ ፍርድ አደባባይም ሒዶ አርያኖስን ንጉሡንም አለቆቹን ሁሉ ረገማቸው ጣዖታቱንም ሰደበ።
አርያኖስም ስለ እኅቱ በእርሱ ክፉ ሊአደርግበት አልተቻለውም ወደ እኅቱ ላከው እንጂ። እርሷም ከመታሠር አዳነችው። ከአርያኖስም በኋላ ሌላ መኰንን ተሾመ የዚህ የቅዱስ ኮጦሎስን ዜና ነገሩት። ጭፍራ ልኮ ወደርሱ አስመጣውና በርሱ ላይ በመቆጣት ለአማልክት ካላጠንክ ይህ ካልሆነ ጽኑ ሥቃይ አሠቃይሃለሁ አለው። ቅዱሱም እኔ ለረከሱ አማልክት ዕጣን አላቀርብም ለክብር ባለቤት ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ንጹሕ መሥዋዕትን አቀርባለሁ እንጂ ብሎ መለሰለት። በዚያን ጊዜም መኰንኑ ተቆጥቶ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። የእግዚአብሔር መልአክም ወደ ርሱ መጥቶ ይፈውሰው ያጽናናውና ያረጋጋው ነበር።
ጌታችንም በእጆቹ ታላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራትን አደረገ። ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ በሰይፍ ራሱን ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ። የሰማዕታትንም አክሊል ተቀበለ ቤተ ሰቦቹም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖሩት። ከሥጋውም እጅግ ብዙ ድንቆች ተአምራት የሚታዩ ሆነ።

❤1
ቅዱስ ቅብዓ ሜሮን
ዳግመኛ በዚህች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ የምንከብርበትን ቅብዐ ሜሮን አፍልቆልናል:: በስደቱ ጊዜ ጌታችን በምድረ ግብፅ ደክሟቸው ካረፉበት ቦታ ላይ የዮሴፍ በትርን ቆራርጦ: በኪነ ጥበቡ ውሃ አፍልቆ: አጠጥቶ: ትልልቅ ዛፎች አደረጋቸው:: እዛውም ላይ ቅብዐ ሜሮንን አፈለቀ:: ቅብዐ በለሶንም ይሏቸዋል::
በሁዋላም የጌታችን ወዙ በታጠበ ጊዜ ተቀላቅሎበታል:: ዛሬ እኛም: ንዋየ ቅድሳትም የምንከብረው በዚሁ ቅዱስ ቅብዐት ነው::
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፤ ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት

❤3
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት 13 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን፣ ከ280 በላይ ምእመናን መፈናቀላቸውንና የ101 ዓመት ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን አሳወቁ።
ብፁዕነታቸው በደረሰው ጥቃት ሐዘናቸውን ገልጸዋል።
EOTCMK TV ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም
እስመ በእንቲአከ ይቀትሉነ ኩሎ አሚረ::
ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ መዝ 43:22
"ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል። መዝ 43:22
Waa'ee Keetif Yeroo Hunda Duuna, Akka Hoolota qalamaniis Taane. Far 43:22
ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ:ም ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ ወረዳ; በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13 ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ የ101 ዓመት እድሜ ያለው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።
የካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

😢3
ምን አልባት እንደ አንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ያልተገደልነው አርሲ የሚባለው ቦታ ስላልተገኘን ነው። ዛሬ ላይ ዝም የተባለ ነገር ነገ ከቤታቸን በር ላይ መምጣቱ አይቀርምና የሚመለከተው አካል በቶሎ ምላሽ ቢሰጥና ለቀሩትም ከለላና ጥበቃ ቢሰጥ መልካም ነው።
ታሪክ ነገ ይጠይቃል።
ታሪክ ነገ ይጠይቃል።
😢5
በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን ሁሉ ወንድማማቾች እና እህትማማቾች ነን። የአንዱ ጉዳት ለሌላው ጉዳቱ ሊሆን ይገባል።
🕊️🔴 #የኦርቶዶክስ_ክርስቲያኖች_ግድያ_ይቁም!
🛑 ሰላምና ፍትህ ለንጹሃን!
በአርሲና በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሃን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ሰቆቃ የእያንዳንዳችን ህመም ነው። ማንነትን እና እምነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል!
ቤተክርስቲያን የሰላም እንጂ የጦርነት አውድማ አይደለችም!
ምዕመናን በነፃነት የመኖርና የማምለክ ሰብአዊ መብት አላቸው!
🕯️ በጸሎትና በድምፅ እንቁም!
የተሰበረውን እንዲጠግን፣ ለተጎዱት መፅናናትን እንዲሰጥና ለሀገራችን ሰላምን እንዲያወርድ ወደ ፈጣሪ እያለቀስን፤ በግፍ ለሚፈሰው የንጹሃን ደም ግን ፍትህን እንጠይቃለን።
🛡️ ህይወት ውድ ነው! ሰብአዊነት ይቀድማል!
#ፍትህ #አርሲ #ኦርቶዶክስ #ኢትዮጵያ #StopOrthodoxChristianKilling #Justice ForAll
“አንዱ አካል ቢሰቃይ፥ አካላት ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሰቃያሉ።”
(፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፪፥፳፮)