ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
1.5K subscribers
1.09K photos
20 videos
13 files
247 links
Download Telegram
🕊️🔴 #የኦርቶዶክስ_ክርስቲያኖች_ግድያ_ይቁም!
“አንዱ አካል ቢሰቃይ፥ አካላት ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሰቃያሉ።”
(፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፪፥፳፮)


🛑 ሰላምና ፍትህ ለንጹሃን!
በአርሲና በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሃን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ሰቆቃ የእያንዳንዳችን ህመም ነው። ማንነትን እና እምነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል!
ቤተክርስቲያን የሰላም እንጂ የጦርነት አውድማ አይደለችም!
ምዕመናን በነፃነት የመኖርና የማምለክ ሰብአዊ መብት አላቸው!
🕯️ በጸሎትና በድምፅ እንቁም!
የተሰበረውን እንዲጠግን፣ ለተጎዱት መፅናናትን እንዲሰጥና ለሀገራችን ሰላምን እንዲያወርድ ወደ ፈጣሪ እያለቀስን፤ በግፍ ለሚፈሰው የንጹሃን ደም ግን ፍትህን እንጠይቃለን።
🛡️ ህይወት ውድ ነው! ሰብአዊነት ይቀድማል!
#ፍትህ #አርሲ #ኦርቶዶክስ #ኢትዮጵያ #StopOrthodoxChristianKilling #Justice ForAll
❤1