Hasen Injamo
15K subscribers
2.6K photos
61 videos
42 files
391 links
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው::

https://telega.io/c/Haseniye
Download Telegram
ቲክቶክ ግን ሲጨንቅ ወላሂ:: ስክሮል እያደረግህ ሳትፈልግ መጦዝ ነው:: ፌስቡክ እኮ አይንቀዠቀዥም:: ዓይንን አይወሰውስም:: በቀልምና በምስል ተንቀልቅሎ ልብህን አያስገድድብህም:: ቲክቶክ የግድ የሆነ መልእክት ያላችሁ ሰዎች እንደ ካካ ጣል አድርጋችሁና ውኃ ደፍታችሁ ማለቴ logout ተጭናችሁ መጥፋት ነው:: ኮሜንትና ኢንቦክስ ዘግቸዋለሁ:: ስክሮል ስታደርግ ውለህ ምን እንደተማርክ የት እንደዋልክ ይጠፋብሃል::
😢62
የምትሸጡትን እቃ
ቀድማችሁ ለዩ
=======
ኢምፖርት ቢዝነስ ቀላል እንዳይመስላችሁ:: ከፍተኛ ውድድር እና ከፍተኛ መጭ^በርበር ያለበት ሰፈር ነው:: በየትኛውም stages ላይ ገንዘብ ከመክፈላችሁ በፊት የሰዎቹን ማንነት አጣሩ:: ለማንም ሰው ይህንን ያህል ብር አለኝ ምን ልሥራ ባትሉ ይመከራል:: አትመካከሩ እያልኩ አይደለም:: ብር ጋር ሲደርስ ጠንቀቅ ማለት ነው:: ገራሚ ትርፍ ካሳዩዋችሁ ችግር አለ:: በዚህ ብር ምን ልጫን? ተብዬ በተደጋጋሚ እጠየቃለሁ:: እንዲህ ለሚለኝ ሰው "ሲጀመር ይህ ያህል ብር እንዴት እዚህ ጋር ደረሰ? ምን ሠርተህ ነው ያመጣኸው?" ነው ልለው የምችለው:: ምክንያቱም ሥራን የሚያውቅ ሰው ምን ልጫን አይልም:: ቢልም ዋነኛ ሥራ መጫን ሳይሆን መሸጥ መቻል ነው:: የማትሸጠውን ዕቃ እንዴት ልትጭነው ነው? ንግድ ፈቃድ ከማውጣት ጀምሮ መዘጋጀት ይፈልጋል:: ዛሬ የጫንከው እቃ ሰነድ እስከ 10 ዓመት ማስቀመጥ አለብህ:: ይህንን ለመሸሽ በሌላ ሰው ማለትም በኪራይ ንግድ ፈቃድ መጫን የራሱ ሪስክ አለው:: ሁሌ መጠያየቅ ሁሌ መረጃ ማነፍነፍ የግድ ይላል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈርተህ ከቆምክማ አበቃልህ:: ገብተህ መታገል ነው:: የባሕሩን ጥልቀት በአንድ እግርህ ለካ::
❤38
ኢምፖርተር የሚሆነው እቃውን መሸጥ የሚችል ሰው ብቻ ነው:: <<ብቻ>> የሚለው ቃል ስጠቀም እርግጠኛ ሆኜ ነው:: ከመርካቶ ሳሪስ ወስደህ ለመሸጥ ትልቁ ልፋት ከመርካቶ ማምጣቱ ሳይሆን ላልታወቁ ለወደፊት ዓመታት ሳሪስ ላይ ከደንብ, ከደንበኛና ከተወዳዳሪ ጋር ታግለህ አትርፈህ ሽጠህ ቅርንጫፍ ለመክፈት መቻል ማለት ነው:: ኢምፖርተር ከመሆንህ በፊት የግድ ኮንሲዩመሮችህን ማለትም እቃህን የሚገዙህ ተጠቃሚዎችህን ማወቅ አለብህ:: ዘው ብለህ ገብተህ እቃ ካመጣህ "አሕያ ያረጀበት ሰው" ትሆናለህ:: አሕያህን አታ^ርደው, አትጭነው, አትጥለው ነገር ይሆንብሃል:: ላስፈራራችሁ ሳይሆን ትልቁ ሥራ ያለው ቻይና ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው:: መሸጥ ከቻልክ ሌላው ቀላል ባይባልም ከባድ አይደለም:: ካልኩለሱ እዚሁ እኛው ሀገር ነው:: እዚያ እኮ የእቃ ውቅያኖስ ነው ያለው:: ከውቅያኖሶች ወይም ወንዞች ጨልፈህ መምጣቱን አያሳስብህ:: እኛ አለን:: ካንተ ግን ሁለት ነገር እንፈልጋለን:: መሸጥ መቻል እና መነሻ ካፒታል:: ከካፒታልህ ጋር ንክኪ አይኖረንም:: በስንት እንደምትሸጠው አናውቅም:: ያንተ ምስጢር እና ሀጃ ነው::

(ምሥጢርህን መጠበቅ ዋነኛ ካፒታላችን መሆኑንም ማስታወስ ያስፈልጋል)
👏17
Live stream scheduled for
ዛሬ ቀጣሪ ወይስ ተቀጣሪ? በሚል ርዕስ Live ይኖረናል:: ቀጣይ ሲስተሙ በዚህ እየከፈለን ስለሆነ ጎራችንን ለመለየት ይረዳናል:: ሲስተሙ እየቆለፈና እያጠበበ ነው::
🔥20
Live stream started
Live stream finished (55 minutes)
ዛሬ የነበረው የ Live ፕሮግራም አንኳር ነጥቦች
🫡9
Audio
የግብርና ባንክ በኢትዮ FM 📻 107 በዓብዱልቃዲር ኑረዲን ከእስከዳር ጋር
❤22
የባንክ ሒሳባችሁ ከታገደ ከንግድ ፈቃድ ጋር የተያያዘ ሊሆን ስለሚችል TIN እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ይዛችሁ የከፈታችሁበት ባንክ ሄዳችሁ ማስለቀቅ ትችላላችሁ:: ምክንያቱም ከንግድ ፈቃድ ጋር ያልተያያዙ የባንክ አካውንቶች ላይ ብሮች ሲዘዋወሩ ሲስተሙ እየዘጋ ነው::

ቀጣይ አቅጣጫ የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መቀጠር የሚል ነው:: የቀጣሪነት ወይም የተቀጣሪነት እድላችሁን እራሳችሁ ናችሁ የምትወስኑት:: መቼለት ቴሌግራም "ቀጣሪ ወይስ ተቀጣሪ?" Live ፕሮግራሜ ይህንን የተመለከተ ነበር:: የባንኩንም አንስቼዋለሁ:: ወይ ድርጅት ከፍተህ ቀጣሪ ትሆንና እያንዳንዱ እንቅስቃሴህ በደረሰኝ ይሆናል ወይ ተቀጣሪ ሆነህ ገቢህ በፔይሮል ይሆናል:: (መ-ገንዘብ 2 ስለዚህ ጉዳይ ነው የሚያወራው)::
❤25
በግል ሴቪንግ የሚንቀሳቀስ ምንጩ ያልታወቀ እንቅስቃሴ የባንክ ሲስተም Block እና Lock 🔒 እያደረገ ነው:: በዚህ ወቅት የገቢህ ምንጭ ከሁለት አቅጣጫ ብቻ እየሆነ ነው::

1ኛ) ንግድ ፈቃድ አውጥቶ በደረሰኝ የገቡ ገቢዎች
2ኛ) ተቀጥሮ በደመወዝ እና አክሲዮን ገዝቶ በዲቪደንድ መልክ ነው የሚሆኑት
ሌሎች ገቢዎች እንኳ ቋሚ ስላልሆኑ ብዙ ምድብ አናወጣላቸውም::
_____
በችርቻሮም ይሁን ጅምላ ንግድ ተሠማርታችሁ ግን ከኢምፖርተር የምትረከቡ ምእመናን የኢምፖርት ስልጠናው ይመለከታችሗል:: በ Less than Container Load (LCL) ሞድ ለምሳሌ 2 ሜትር ኪዩብ (CBM) መጫን ብጀምሩ ሲስተሙን ትለማመዱበታላችሁ:: (የተለያዩ መጠኖች ያሉዋቸው የመርከብ 🚢 ኮንቴይነሮች አሉ:: መደበኛዎቹን ብንወስድ ቮሊዩም ላላቸው እቃዎች ባለ68 ሜት ኪዩብ እና ለባለክብደት እቃ 28 ሜትር ኪዩብ በሚል ያዙት):: ስለዚህ በጣምራ አንዱን ሞልቶ ማምጣት ይቻላል:: ታዲያ አሁን ላይ ንግድ ፈቃድ የግድ ብሏል:: ባላችሁ ፈቃድ ላይ ኢምፖርት ታክሉበታላችሁ ከሌላችሁም ታወጣላችሁ:: ያው የራሱ ቅድመ ሁኔታዎች አሉት:: እንዴት እንደሚቀናጅ እና ፈቃድ እንዴት እንደሚወጣ ስልጠናዎቻችን ላይ አለ:: ሁሉንም በባለ ሙያ ነው:: Almost ሞልቶ ሊዘጋ ስለሆነ ግቡለት:: ዝርዝር በኮሜንት አለ:: ዊዝሆልድ የምትቆርጡ ተመዝጋቢዎች ቆርጣችሁ አስገቡና የዊዝሆልድ ደረሰኙን አምጡልን::
❤14
የኢትዮጵያ ባንኮችን ብድር ሢሦ የሚበደሩት አስር ሰዎች ናቸው:: የዓለም 75% ሀብት የተያዘው አስር ፐርሰንት በማይሞሉ ሰዎች ነው:: ይህ ለምን እንደሆነ በመ-ገንዘብ መጽሓፍ በደንብ ተብራርቷል:: እኔ ሲስተሙ ምን እንደሚመስል ከእነመፍትሔው ጽፌያለሁ:: ብዙ ጸሓፍትም ጽፈዋል:: ከየትኞቹ እንደምንሆን ውሳኔው የየግላችን ነው::
👍17
ሀጂ የደመወዝ መዳረሻ ከቴሌብር ብበደር ሀራም ይሆናል ወይ?

-> መድረስ ከቻልክ ችግር የለውም:: ዋናው ትደርሳለህ ወይ ነው ነጥቡ:: ከ10 ዓመታት በላይ ስናገር ኖሬያለሁ:: ይህኛው የፋይናንስ ሲስተም ሲበዛ ጨካኝ ነው:: ከወለድ ነጻ ይመጣል ብለህ አትጠብቅ:: መቼም አይመጣም:: ትናንትና እንደማይመጣው:: ከመደበኛው ቢብስ እንጂ አይሻልም:: ስለዚህ ከደመወዝ መበደሩን እርሳው:: ጉዳዩ ቤት አስይዘህ ከንግድ ብትበደርም አትደርስበትም:: በዚህ ሦስት ዓመት እኔም አንተም ፈጥነን ንብረት እንያዝ:: የማይፈራ ዑለማእ ቢኖር ጥሩ ነበር:: አንዳንዶቹ ካንተ የባሰ ቸግሯቸው ጺም እና አማማ ለባንክ እያከራዩ ናቸው:: ጭራሽ ባንተ ድህነት ላይ ፎቅ ይገነባሉ:: ፑ! ደህና የምትላቸው ዑለሞች ደግሞ ትንሽ ትንፍሽ ቢሉ በጺም አከራዮቹ ይሰ^ደባሉ:: ስ^ድቡን አይችሉትም:: እኔም ቆዳዬ አደንድኜ ሰ^ዳቢዎችን ቦልኬ ነው የተቋቋምኩት:: በዚያኛው ፌስቡክ አካውንቴ እኮ 5K የሚደርስ ተቦላኪ አለ::

መቸም ደመወዝ መዳረሻ ጠየቅኸኝም አይደል? መንግሥት እያለልህ ከመሥሪያ ቤት ጓደኛም ይሁን ከዘመድ አትበደር:: ለግለሰቦች ነውርህን ትዘከዝካለህ:: ኢማን እና ታማኝነትህን አስይዘህ ነው የምትበደረው:: ደመወዝተኛ በነበርኩ ወቅት እንዴት እንደሚጨንቅ አውቀዋለሁ:: ቴሌብር ስለኢማንህ አያገባውም:: በሰከንዶች ያበድርሃል:: ነውርህን ይሸፍንልሃል:: ከዚህ አዙሪት ግን ቶሎ ውጣ:: ጊዜ የለንም:: ሲስተሙ እየቆለፈ እየመጣ ነው::
❤61
ፌስቡክ ላይ ሂዱበት:: በነጻ ማስተዋወቅ ማለቴን ነው::

https://www.facebook.com/share/19cJ6SeifV/?mibextid=wwXIfr
❤3
ኢምፖርት በዚህኛውም ዙር ወዲያው ሞልቷል:: የሚገርመኝ የሪፈራል ሰው ይበዛል:: ማለትም በጥቆማ የሚመጣ ... ከሌላ ስልጠናችን ዞሮ የሚገባ:: አቦ ሀብታም ያድርጋችሁ:: ከዚህ በፊት የሰለጠናችሁ ደግሞ የምንገናኝባቸው መድረኮች ይኖሩናል::

የኢምፖርት ሒሳብ ማስሊያ Microsoft Excel አሪፍ አድርጌ ሠርቸዋለሁ:: ትንሽ ማስተካከያ ይፈልግ ስለነበር ሰሞኑን እሱ ላይ ነበርኩ:: አስተካክዬ ጨረስኩ:: ምክንያቱም በሁሉም ሴናሪዮ ቼክ መደረግ እና ቀለል ማድረግ ይጠይቃል:: ለአንድ ኢምፖርት የሦስት ሀገራት መገበያዎች እና ሁለት ዓይነት ክፍያዎችን በቀላል አገላለጽ ማቀናጀት ቀላል አይደለም:: ደረሰኝ ያላቸው እና የሌላቸው ክፍያዎች አሉ:: ሁሌም ይኖራሉ:: እነዚህ ሁለቱም ወጪዎች ቴክኒካሊ የዕቃው አካል ናቸው:: ደረሰኝ ኖሮኣቸው እንኳ የማይያዙልን አሉ:: ከአየር መንገድ የበረራ ደረሰኝ ይዘህ ገቢዎች "የሄድከው ልትዝናና ቢሆንስ?" ሊልህ ይችላል:: ሁሉም ነጋዴ ደግሞ ወጪውን ሸፍኖ ማትረፍ ይፈልጋል:: አንድ አፕልኬሽን ሲዘጋጅ ሙሉ መስመሩን የሚያውቀው መሆን አለበት:: እራሴ ኢምፖርት ስለማደርግ, ድሮ የኢምፖርተሮችን ሒሳብ እስከ ኦዲት ክርክር ስለሄድኩበት አውቀዋለሁ:: እንዲህም ሆኖ የሚያመልጡኝ recent ጉዳዮች ስለሚኖሩ ለሌላ ታማኝ ባለሙያ አሻግራለሁ::

ገቢዎች በቲዎሪ ደረጃ ቀረጥ የሚያሰሉት በ CIF (Cost insurance freight) ቢሆንም ግን ትግበራው ላይ ግን ሌሎች ወጪዎችም አሉ:: ደረሰኙ አንድ ሆኖ ግን ለገቢዎች ኮስት እና ለጉምሩክ ቀረጥ ተብለው ለሁለት የሚሰነጠቁ ወጪዎች አሉ:: ለማንኛውም ለሰልጣኞቻችን ለድሮዎችም ጭምር እንልከዋለን:: ያልገባችሁ ምእመናን አንዴ እንገርበዋለን::
❤9
መ-ገንዘብ 2 የአዋቂዎቹ ማለት መ-ገንዘብ 1ን ያጠቃልላል:: የታዳጊዎቹ የተዘጋጀው ሌሎቹ ከበድ ስለሚሉ ነው:: ጃእፈር ጋር የገባው ሳያልቅ አይቀርም:: መኖሩን ቀድማችሁ ብትደውሉ መልካም ይመስለኛል:: ተጨማሪ ይታተም አይታተም ሲወሰን አሳውቃለሁ::
ስልኩ
+251 91 112 5324
❤2
ጊዜ ኖሮኝ በፋይናንስ ጉዳይ ስንትና ስንት የሚብራሩ ነገሮች ነበሩ:: የወረቀት ፊያትን ማስረዳት ስጀምር ያለመጡ ነበሩ:: ያ ዘመን አልፎ የዲጂታል ሜታዳታ ተረከበ:: አሁን ቀጣዩ አንተ የማታዘው እርሱ ግን የሚያዝህ ሥርዓት እየተተከለ ነው:: እስከ 2030 ብዙ ነገር መጠናቀቅ አለበት ተብሎ aggressively እየተሠራ ነው:: ያኔ ገንዘቡ እኛ አናዘውም:: ያዘናል እንጂ:: ንብረት የያዘ ይመነዝራል:: ያልያዘ ያለው አማራጭ ሁለት ሦስት ቦታ እየተቀጠረ በክሬዲት ካርድ ዕድሜውን ቀጥሎ ለልጆቹ ተመሳሳይ ሕይወት ያወርሳል:: እንደ ግለሰብ ንብረት መያዣ ጥቂት ጊዜ ነው ያለው:: አንዳንድ እስላሞችና ሙስሊሞች እንድንከራከር ይፈልጉ ነበር:: የደላው ሙቅ ያኝካል ነው ነገሩ:: የሆነ ጊዜ የሙስሊሞች ቴሌዢዥኖች ፕሮግራም እንድናዘጋጅ ሲደውሉ ... ጉዳዩ ፕሮግራም የማሳመር ... ክፍተት የመሙላት ... ወይም አጉል የመወያየት አይደለም:: የነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው:: አንዳንድ የዋሆች የዓብዱልቃዲር አመለካከት ይመስላቸዋል:: አዲስ ነገር እያወራሁ አይደለም:: ያለ እና እየኖርነው ያለነው ግን የተዘናጋንበት መሠረታዊ ጉዳይ ነው:: መዓት እያወራሁ, እየቃዠሁ, እያስጨነቅሁ አይደለም:: በቂ ጭንቀት ይዞናል:: ሮጠን የማንደርስበት ነገር ውስጥ ሳንገባ አንዘናጋ ለማለት ነው:: በእንጥልጥል የቀረ ንብረት ካለ ቶሎ አስከብር:: ልቀማ ብሎ የሚመጣ ካለም ፋ^ስህን ስለህ ጠብቅ:: አንዳንድ ጅ^ል የምር ፋ^ስ ሊስል ይችላል እኮ::
❤32
የራስ እጅ መጥኖ ያጎርሳል የሰው ጉርሻ ወይ ያንቃል ወይ ያንሳል
========
ከቅጥር ሕይወቴ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በዕርዳታ ድርጅት ውስጥ ነው ያለፈው:: ሆኖም ግን የዕርዳታ ሥራ ላይ ስሠማራ አታዩኝም:: ችግረኛን የሚያባዙት ዕርዳታ ሰጪዎች እንደሆኑ አምናለሁ:: የዕርዳታ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች አይመቹኝም:: ደቾችን (የሆላንዶችን) የታደገ አንድ ፖሊሲ ልንገራችሁ:: የዋሴናር ስምምነት ይባላል:: በመ-ገንዘብ 2 መጽሓፍ አንስቸዋለሁ:: ሆላንድ በአደገኛ ወረርሽኝ ተጠቃች:: በሽታውም "Dutch Disease” በመባል ይታወቃል:: በቫይረስ ወይም ባክቴሪያ የሚተላለፍ ሳይሆን በጋዝ የሚመጣ መርገምት ነው:: በሽታውም የ1960ዎቹ የተፈጥሮ ጋዝ ግኝት ነበር::

ብዙ ሆላንዳውያን እንደ ጸጋ ቢቆጥሩትም ታላላቆች ግን የደች መጥፊያ እንደሆነ ገመቱ:: ሕዝቡ እስኪገባው ጋዙ በገፍ መውጣት ጀመረ:: ዶላር ጎረፈ:: ጋዝ እየሸጡ ስንዴና ዘይት መግዛት ቀላል ሆነ:: የሆላንድ ፋብሪካዎች እየከሰሩ መሄድ ጀመሩ:: መሃንዲስ ፈላጊ እያጣ መጣ:: ሌሎች ምሩቃንም ሥራ ማጣት ቀጠሉ:: ዶላር ግን መጉረፉን አላቆመም:: በጎን የሥራ አጥ ቁጥር እየጨመረና ምስቅልቅሉ እየተዛመተ ሄዶ ሀገር ልትፈርስ ሲሆን ጊዜ ነው በፖልደር ሞዴል እንዳን ያሉት:: ፖልደር ማለት ከባሕር ወለል በታች ያለ መሬት ነው:: መንግሥትም ሕዝብም እየተፎካከሩ መጥለቅለቅ ከመጣ ማንም አይተርፍም:: የጋዝ መውጣት በልክ ይሁንና ሌሎች ፋብሪካዎቻችን ይንቀሳቀሱ ብለው ወደ አቅላቸው ተመለሱ:: ይህ በሽታ አብዛኛውን የዐረብና የአፍሪካ ሀገራትን አጥቅቶ ለምስቅልቅል ዳርጎኣቸዋል:: እንደ ኮንጎ ሀብታም ድሃም የሌለው በዚህ በሽታ ምክንያት ነው::

የስዑድ ዐረብያው ንጉሥ ፈይሶል ልክ ነዳጅ እንደወጣላቸው የስንዴ እርሻ ውስጥ ገቡ:: ባገኙት ዶላር በመታገዝ ሀገሩን በእርሻ አንጣለሉት:: በረሃውን መቀየር ውስጥ ገቡ:: የአሜሪካው ሄነሪ ኪሲንጀር የስንዴ ክምር በመርከብ አምጥቶ አጥለቀለቀው:: ንጉሡ እምቢ አሉ:: "ነዳጁን ትጠጡት እንደሆነ እናያለን" ብሎ ተመናጭቆ የሄደበት ዶክመንት አይቼ ገረመኝ:: ስንዴ ካላመረትን በተውሶ ስንዴ መቼም ነጻ አንወጣም በሚል በጽኑ ቆሙ:: ብዙም ሳይቆዩ አሜሪካ ይኖር በነበረ ቤተሰባቸው አስ^ገደሉዋቸው:: እነሆ ባሪያ ሆነው ዙሪያቸውንም ባሪያ አድርገው ይኖራሉ:: እና በዕርዳታ ሥራ የተሰማራ ሰው እንደ ገ^ዳይ በሽታ ነው የማየው:: ችግርተኛስ አንዴ ቸግሮታል:: መፍትሔው ሥራ እንዴት እንደሚሠራ ማስተማር እንጂ ጉርስ መስጠት አይደለም:: በዚህ ዘመንማ ጭራሽ በቪዲዮ ያልታየ ምጽዋት እንደ ኪሳራ ይቆጠራል:: መረዳዳት ወይም ትብብር ጥሩ ነው:: ዕለታዊ ጉርሻ ግን ያጠፋ^ናል:: አጥፍቶናልም::
❤49
በ Emnet Teshome ከሚባል የፌስቡክ ገጽ
=====
🔔 ገቢዎች ዓመታዊ ግብር ለማሳወቅ ለምትሄዱ ሁሉ
ዓመታዊ ግብር ግመታ በትንሹ 50,000 ብር እንድትከፍሉ በቅድመ ኦዲት የተስተካካለ በሚል መነሻ 2,000,000 ተክለው ኦዲት ይሰራሉ። (ከዚህ በፊትም ይደረግ ነበር)
ሰሞኑን ይህ ደንብ የለም ተብሎ ከሰራችሁት ውጪ የሚጣል የተስተካካለ ግመታ/ልዩነት የሚከፈል ክፍያ የለም ተብሏል።
ስለዚህ ልዩነት ልትከፍሉ ከነበረ ጠብቁ ሂሳብ የሰራውን ኦዲተር ለምን ከየት መጣ ብላችሁ በዝርዝር ጠይቁ!!! ላለመመላለስ በኦንላየን የላካችሁት ሙሉ ዶክመንት withholding እና የሂሳብ ባለሞያ የሰራቸውን/የጻፋቸውን ስሌቶች በሙሉ ይዛችሁ ሂዱ!
ኦዲተሩ የሰጣችሁ ሊስት እና የተጠየቁ ክፍያዎች ካልገባችሁ የውስጥ ኦዲተሩን እና የሂሳብ ሰራተኛችሁን ጠይቁ!
✍️ ይህን የጻፍኩት ትናንት ልዩነት ክፈሉ ተብለን ዛሬ ለመጠየቅ ስሄድ ደንብ የለውም እንዲ አይነት አሰራር የለም ይቅር ተብሏል ብለው ሰምቼ ነው። እኔም አትክፈል ጠብቅ ተብዬ ወጥቻለሁ።
በተጨማሪም emergency fund, trust fund, red cross አሁን Etax system ላይ ገብተዋል ነገር ግን ለክፍያ active አይደሉም። እንደ በፊቱ በማንዋል (bank transfer) ብትከፍሉ ተቀባይነት አይኖረውም! ክፍያው በ tele birr ወይም ደራሽ ብቻ ነው።
Etax ተጠቃሚ ካልሆናችሁ የonline ክፍያውን አትገደዱም።
የተያያዘው ፎቶ
ድርጅቱ የሰራው 164k
የውስጥ ኦዲተር መነሻ የተከለው 2M
ድርጅቱ መክፈል የሚጠበቅበት 18k
ገቢዎች የሚጠብቀው ዝቅተኛ ክፍያ 50k
ድርጅቱ በኳርተር የከፈለው ተቀናንሶ 50k - 14k= 35k
ድርጅቱ አሁይ ይቀርብኛል ብሎ አምኖ የከፈለው= 18k 🔣 35k - 18k= 16k ገቢዎች ለሚጠብቀው ክፍያ የቀረ ግምት 16k
ስለዚህ ድርጅቱ ባላተረፈው ትርፍ ልዩነት 16ሺህ እንዲከፍል ተወስኗል። (አሁን ይሄ አሰራር ቀርቷል ተብሏል) ስለዚህ ከዚህ በኋላ ኦዲት የምትደረጉ ወይም ለመክፈል የምትሄዱ ክፍያ ከመፈጸማችሁ በፊት ለምን በሉ ከሂሳብ ሰራተኛችሁና ኦዲተሩ ጋር ቁጭ ብላችሁ አሰሩ።
በተቻለኝና በገባኝ ጽፌዋለሁ/ገልጬዋለሁ 🤔 ሂሳብ ስሌቱ ሌላ ስም ከተሰጠውም 🤷‍♂️ ብቻ ከመክፈላችሁ በፊት ክፈሉ የተባላችሁት ምን ምን እንደሆነ እና withholdings መቀነሱን እዩት በኳርተር የከፈላችሁትንም አስሉ 😉
መልካም ቀን 🙌
🙏5