ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
1.5K subscribers
1.09K photos
20 videos
13 files
247 links
Download Telegram
ቤተልሔም ማለት ቤተ ህብስት፣ የህብስት ቤት፣ የእንጀራ ቤት ማለት ነው። ይህም ካሌብ እስራኤል ዘሥጋ ምድረ ርስት፣ ኢያሪኮን “ሃይል ዘእግዚአብሔር ኲናት ዘኢያሱ” ብለው በኢያሱ መስፍንነት ሲወርሱ ከኢያሱ የተሰጠችው ምድር፣ ኬብሮን ነበረች። ይህችም የይሁዳ ምድር በኋላም የቅዱስ ዳዊት ከተማ የሆነች ናት። አስቀድሞ ካሌብ ከብታ የምትባል ሚስት አግብቶ በሚስቱ ከብታ አላት ትርጓሜውም የምስጋና ቤት ማለት ነው፤ ይህም ካሌብ በመንፈሰ እግዚአብሔር በዚህች ምድር የሚገለጠውን የክርስቶስ የልደቱን ነገር፣ እና የመላእክትን ምስጋና ስለተረዳ ነበር። በኋላም ካሌብ ኤፍራታ የምትባል ሚስት አገባ ቦታዋን በዚህች ሚስቱ እንደገና ኤፍራታ ብሎ ጠራት። ኤፍራታ ማለት ፀዋሪተ ፍሬ፣ ፍሬ በውስጧ ያለባት ማለት ነው። ይህችውም የእመቤታችን ምሳሌ ናት የህይወት ፍሬ ክርስቶስን ወልዳልናለችና፤ አንቲ ውእቱ ዕፅ ቡሩክ ፍሬኪኒ ፍሬ ሕይወት እንዳለ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን። ቤተልሔም ይህን ስያሜዋን ያገኘችው ካሌብ ከኤፍራታ ባገኘው ልጁ በልሔም ነው፤ ልሔም ማለት ህብስት፣ እንጀራ ማለት ነው ይህም ምሳሌነቱ የጌታ ነው፤ ይኸውም አማናዊ፣ እውነተኛ የሕይወት እንጀራ፣ህብስት ክርስቶስ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ሊያድነን የመወለዱ ምሳሌ ነው። “ከሰማይ የወረደ ህያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል እኔም ስለዓለም ህይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።” እንዲል /ዮሐ 6፥51/።
👍1
‹‹ጥር 4›› በዚች ዕለት የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ሞትን ሳይቀምስ የተሰወረበት መታሰቢያ በዓሉ ነው።

ሐዋርያው ዮሐንስ ከዘብድዮስና ከማርያም ባውፍልያ መስከረም አራት ቀን ተወልደ ።

ዮሐንስ ማለት ትርጓሜው "እግዚአብሔር ፀጋ ነው፣ ደስታ" ማለት ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችን ደቀመዝሙር ከመሆኑ አስቀድሞ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ነበር ገና በወጣትነቱም የመሲሁን የክርስቶስን መምጣት ከመምህሩ ከመጥምቀ መለኮት ስለተረዳ የጌታችን ደቀ መዝሙር ሆኗል፤ ዕድገቱም በገሊላ ነበር።

ለጌታ ቅርብ ከነበሩ የምስጢር ሐዋርያት ( ጴጥሮስና ያዕቆብ) ቀዳሚው እርሱ ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ ልክ ወንጌሉን ሲጀምር " በመጀመሪያ ቃል ነበረ፥ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ይላል።

በኑሮም ጌታ ስለሚመስል (ፍቁረ እግዚእ) ይባለል። ነገረ መለኮትን በበለጠ ከሌሎች አምልቶ አስቶ በጥልቀት በማስተማሩ ነባቤ መለኮት (ታዖሎጎስ)ተሰኝቷል።

ስለጌታም ባለው ቅናት ባሳየው የሀይል ሥራ በኦኔርጌስ (ወልደ ነጎድጓድም) ተብሏል። ፍጥሞ በምትባል ደሴት በራዕይ መጻእያትን በመግለጡ ባለራዕይ (በግሪክ አቡቀለምሲስ) ይባላል።

በዕለተ ዓርብ በመስቀል ሥር ተገኝቶ የጌታን መከራ መስቀል በማየቱ ፊቱ በሀዘን ስለተቋጠረ ቁጽረ ገጽ (ፊቱ በሀዘነ የተቋጠረ) ስምም ተሰቶታል።

ጌታችን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ ከአጠገቡ ያልተለየ፣ ስቃይና መከራውን ያየ፤ በዚህም የተነሳ ለ፸ ዓመታት ፊቱ በሀዘን የተቋጥረ (ቁጽረ ገጽ) ሐዋርያ ነው።

ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ እንደ ሔኖክ፣ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነው።

የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በረከትና ምልጃ አይለየን!
❤1
አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በዓል እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ታሪኩ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደተጻፈ
❤2
ደ ብ ረ ፡ ይ ድ ራ ስ :ተ ራ ራ :ወ ስ ደ ው :አ ፅ ሙ ን :በ ተ ኑ ት

#ጥር_18 ቀን ቅዱስ ጊዮርጊስ በብዙ ተጋድሎ ውስጥ ሆኖ « እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው » በማለት የተመዘዘ ሰይፍ የነደደ እሳትን የከሀዲውን የዲድያኖስ ቁጣ ሳይፈራ መከራን ታግሷል የጌታውን የአምላኩን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የመሰከረበት ዕለት ሲሆን ።

ቅዱስ ጊዮርጊስም በማይመረምረው ጥበበ እግዚአብሔር በመታመኑ ብዙ መከራ ደረሰበት በጉድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አብስለው አቃጥለው አሳርረው ሥጋውንና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው በዕንጨት ቀፎ በማድረግ በዚህ ጥር 18 ቀን ደብረ ይድራስ ወደ ተባለ ረጅም ተራራ ወስደው አፅሙን በተኑት ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት አንድ አካል ሆኖ ወደ ቀድሞ መልኩ ዳግም ተመልሶ አስነሣው ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በመሄድ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ።

ለቁጥር የበዙ አሕዛብ አይተው አደነቁ ከንጉሥ ሠራዊትም ከአሕዛብም ብዙዎችን በጌታችንም አመኑ በማመናቸውም ምክንያት በከሀዲው በንጉሥ ዲድያኖስ ሰማዕትነትን ተቀበሉ::

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም በታላቅ ድምቀት ይህንን ቀን ታሳቢ በማድረግ በዓልን ሰርታ ታከብረዋለች ።
✎﹏ዳዊት ተስፋዬ
ጥር 18 2018 ዓ.ም
👍3
አንተ እንደምታስበው አይደለም!

ልጁ የሞተችበት አንድ ሰው መጥቶ በክርስቶስ ፊት እየሰገደ ልመናውን አቀረበ።

የለመነው ነገር ምን መሰላችሁ?

“ልጄ አሁን ሞተች ሂድና አድናት” ማቴ. 9፥18 የሚል ነበር።
ኢየሱስ ክርስቶስ ልመናውን ተቀብሎ ልጁን ሊያድንለት ወደ ቤት ሲገባ የሚያለቅሱ ሰዎች ዙሪያዋን ከበዋት ቆመዋል፤ “ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችምና ውጡ” ብሎ ተናገረ።

እዚያ የነበሩ ሰዎች በሙሉ በክርስቶስም በኢያኢሮስም ሳቁበት፤ የሞተና ያልሞተ ለይቶ የማያውቅ ሰው መጣ ብለው በክርስቶስ፣ የሞተና ያልሞተ ለይቶ የማያውቀውን ያስነሳልኛል ብሎ ያመጣል? ብለው በኢያኢሮስ ሳቁ።

ጌታ ማዳን የሚጀምረው በንግግር ነው፤ መልካም ንግግር የፈውስ መጀመሪያ ነውና።

ብላቴናይቱ በኢያኢሮስ ልብ ውስጥ ሕያው መሆን የጀመረችው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” ባለ ጊዜ ነው።

አንዳንድ ነገሮች በእኛም ዘንድ እንዲሁ ናቸው፤ የተኛና የሞተ ጉዳያችንን ገና ለይተን አላወቅንም። የተኛው ሁሉ የሞተ መስሎን በጭንቀት ልናልቅ ነው።

አንዳንዴ የትንሳኤ ዕድል ያላቸውን ስንት ነገሮች እንደቀበርናቸው ሳስበው ደሞ የበለጠ ይገርመኛል።

“ጣቢታ ሆይ ተነሺ” ብሎ እጇን ይዞ የሚያስነሳ አምላክ እያለን አጥበው ገንዘው የሚቀብሩ ሰዎችን እንጠራና አጣድፈው መቃብር ያወርዱብናል።

ቀባሪ ፈጣን ነው ወንድሜ መሞቱን ከነገርኽው ትዳርህን፣ ንብረትህን፣ ሕይወትህን ግብዓተ መሬት ሲፈጽምለት ጊዜ አይፈጅበትም። ሰፈሩ በሙሉ ቀባሪ አይደል እንዴ! ከሰፈሩ ውጣና “ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” ብሎ የሚያጽናናህን ጌታ ብትጠራው አይሻልም?

በነገራችን ላይ እግዚአብሔር ስላንተ ሕይወት የሚያስበው የሰፈሩ ሰው እንደሚያስበው አይደለም። እግዚአብሔር የሚጠራህ ሰፈሩ ባወጣልህ ስም አይደለም።

ሰፈሩማ የሚያውቀው መሞትህን ነው፤ እግዚአብሔር ደግሞ የሚያውቀው መተኛትህን ነው። በእግዚአብሔር ዘንድ ሞትም ቢሆን የእንቅልፍን ያኽል ቀላል ነውና። የሰፈሩ ሰው እንደሆነ ወንድሜ መሞትህን ሲያረጋግጥ ዕንባውን አውጥቶ ሲያለቅስልህ ታገኘዋለህ፤ አለመሞትህን ሲሰማ ደሞ ይስቅብሀል እንጂ የሚደሰትልኝ እንዳይመስልህ።

ሲጀመር ለሞተ ሰው የምናዝነውን ያኽል በሕይወት ላለ ሰው ተደስተን አናውቅም።
ታመህ ቢያገኙህ መታከሚያ የማያዋጡልህ ሰዎች ሞተህ ካገኙህ የቀብር ወጪህን ብቻቸውን ይሸፍናሉ።

ደስ የሚለው ግን ሁሉም ነገር የሚከናወነው ባለቤቱ በፈቀደው መሆኑ ነው እንጂ የሰዎችን ነገር ተወው።

መንገድ ላይ ያገኙትን ዕውር ሆኖ የተወለደ ሰው “ጌታ ሆይ የዚህን ሰው ዓይኖች መመለስ ትችላለህ” ብሎ መለመን ሲገባ “ይህ ሰው ዕውር ሆኖ የተወለደው በማን ኃጢአት ነው?” እያሉ መከራከር በሰውየው ላይ የጨለማ ዘመን ማራዘም ነው።

እግዚአብሔር በዚህ ሰው ላይ ያለው ሀሳብ ሌላ ነው፤ “የእግዚአብሔር ሥራ በእሱ ላይ እንዲገለጥ ነው እንጂ ለሌላ አይደለም”

አጠገባችን ያሉ ሰዎች እንዳወሩትማ ቢሆን ኖሮ እስካሁን መች እዚህ እንገኝ ነበር።

ለፍርድ ባንቸኩል መልካም ነበር፤ እንደ ሌሎቹ ሰዎች “ልጄ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ” አላለውም “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ” ብቻ ብሎ ነው ያሰናበተው። መከራ ሁሉ ከኃጢአት አይወለድም ስለጽድቅ የሚመጣ ፈተናም አለ።

ዛሬ ተሸንፎ ያየነው ሰው ሁሉ እግዚአብሔር የረሳው አይደለም የእግዚአብሔር ሥራ በእሱ ላይ እንዲገለጥም ይሆናልና ፈጥነህ አትፍረድ።

ዛሬ በሕይወትህ እያለፈ ያለው ነገር ሁሉ የሆነው አንተ እንደምታስበው ወይም ሰዎች እንደሚሉህ አይደለም።

አንተ ወይም ሰዎች ሞቷል ያላችሁትን ጉዳይ እግዚአብሔር የሚያውቀው አለመሞቱን ነው። ተስፋ አትቁረጥ ሰዎች ተሰብስበው ያለቀሱለት ነገር ሁሉ የሞተ መስሎህ አትሳቀቅ።

መሞቱን እንኳን ተከትለው መጥተው ቢነግሩህ አንተ ግን ሊሞት መቃረቡን እንጂ መሞቱን አትናገር። ይህንኑ ታሪክ በማርቆስ ወንጌል ስንመለከተው “ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት” ማር. 5፥23 ብሎ ሲለምን እንሰማዋለን።

ነገሩ እንደ ማርቆስ ነው፤ የሁለቱ ልዩነት የተፈጠረው ልጅቷ እንደታመመች አባቷ ወደ ክርስቶስ ሄደና ልጄ ታማለችና ወርደህ ፈውሳት እያለ እየለመነላት ሳለ ሞተች። ሰዎች ተከትለው መጥተው “ልጅህ ሞታለች መምህሩን ለምን ታደክመዋለህ?” አሉት። ኢያኢሮስ ጸሎቱን አልቀየረም፤ “ልጄ ታማለች” ነው አሁንም ጸሎቱ።

አንዳንድ ነገሮችህን ከእግዚአብሔር ጋር እንጂ ከሰዎች ጋር አትማከር።

ሞቷል ብለው ያስጥሉህና ብዙ ነገር ያሳጡሀል ።ምንም ነገርህን ሞቷል ብለህ አውጥተህ ከመጣልህ በፊት ከፈጣሪህ ጋር ተማከር፤ ምናልባትም ጉዳዩ አንተ እንደምታስበው ወይም ሰዎች እንደ ነገሩህ ላይሆን ይችላል።

ብዙ ጉዳዮቻችንን እግዚአብሔር በሚያይበት መንገድ ላናያቸው ስለምንችል ዝም ማለትም መልመድ አለብን።

የጲጥፋራ ሚስት እንዳወራችው ቢሆን ኖሮ ሰዉ ሁሉ እስር ቤት ውስጥ ነበር።
የአልዓዛር እህቶች እንደሚያስቡት ጌታ ስለኛ የሚያስብ ቢሆን ኖሮ ሁላችንም በስብሰን ቀርተን ነበር።

አይዞህ! ነገሩ አንተ እንደምታስበው አይደለም!

ተከትለውህ የመጡ ሰዎች እንደነገሩም አይደለም! ወደ ቤትህ እየመጣ ባለው በክርስቶስ የምታምን ከሆንህ የዚህ ለቅሶ መጨረሻው ሳቅ ነው።

አንተ እንደምታስበው አይደለም!

ስምዓኮነ መልአከ / Simakone Melak
❤4🥰4
🍅 " አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤"(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:5)

🍀 በመጀመሪያ መካከለኛ ማለት አማላጅ ማለት አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስም የእውነት ኢየሱስ አማላጅ ቢሆን ኖሮ በግልጽ መካከለኛ በሚለው ቃል ፋንታ አማላጅ ቃል የሚለውን ይጠቀም ነበረ.. ጌታ ተማላጅ እንጂ አማላጅ ስላልሆነ... ቅዱስ ጳውሎስ መካከለኛ የሚለውን ቃል ስለምን ተጠቀመ ቢባል?

🍀 ኢየሱስ መካከለኛ ነው ሲባል በእግዚአብሔርነትና በሰውነት መካከል ያለ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ነው ማለት ነው፡፡

🍀 ቅዱስ ጳውሎስ ይህን በዚህ መልክት ይህን ቃል(መካከለኛ) በጻፈበት ዋና ዓላማ 👉 አካባቢው ብዙ የግሪክ፣ የሮምና የአይሁድ ሠዎች ነበሩ፤ እነርሱም በኢየሱስ ላይ ብዙ አመለካለት ስለ ነበራቸው ነው፡፡

#ግሪኮች :- ኢየሱስ የሚናገረው ቃል አስገራሚና ሚሥጢራዊ በመሆኑ ኢየሱስን " ፈላስፋ " ነው ብለው ያስቡ ስለነበረ፣

#ሮማዎች ደግሞ "ነፃ አውጪ" ማለትም እሥራኤላውያንን ከኛ ቀኝ ግዢ የሚያወጣ ሠው ነው ብለው ያሥቡ ሥለነበረ፣

#አይሁዶች ደግሞ "እንዲሁ ተራ ሰው" አድርገው ያሥቡ ሥለነበረ፡፡

👉 ቅዱስ ጳውሎስ ግን ኢየሱስ እናተ እንደ ምታስቡት ተራ ሰው፣ ፈላስፋ ወዘተ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ማለት ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነው፡፡ ኢየሱስ በእግዚአብሔርነትንና በሠውነት መካከል ያለ ከሁለቱ አካል አንድ አካል ይዞ የመጣ መካከለኛ ነው፤ ለማለትና ለመናገር በመልክቱ #መካከለኛ አለ፡፡ መካከለኛ የመሆኑ ሚሥጢር ረቂቅ ነው፡፡

👉 " ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤"(1ኛቆሮ 2:8)

ይቆየን!

@WwEotc
❤5
👉 ጌታችን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃ ነው ማለት አማላጅ ነው ማለት ነው?

'' ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።" (1ዮሐ 2:1)

🌼 መልክቱን ሲጀምር "ልጆቼ ሆይ ኃጢአትን አታድርጉ" ብሎ ጀመረ ፡፡ ኃጢአትን ማድረግ እንደሌለብን መጽሐፍ ቅዱስ በደንብ አስጠንቅቆ ይነግረናል ምክንያቱም የሀጢአት ደሞዙ ሞት ነውና (ሮሜ 6:23)፡፡

🌼 '' ማንም ሀጢአትን ቢያደርግ
ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፡፡'' መጀመሪያ ሀጢአትን እንዳታደርጉ ብሎ አሁኑ ደግሞ ሀጢአት ብታደርጉ ወይም ብትሰሩ ግን ጠበቃ አለን አለ። ይሀ ማለት እንደፈለጋችሁ በምድር ኑሩ ሀጢአት ስሩ ስትሞቱ ግን ጠበቃ አላችሁ አይዟችሁ የሚል ትርጉም ከሰጠነው ስህተት ነው።

እንግዲያስ ምን ማለት ነው?

🌼 ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ጠበቃው ማንነት ሲናገር ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ተናግሯል። አሁን ልብ ማለት ያለብን ጠበቃ ካለ የሚከስ ከሳሽ አካል አለ ማለት ነው። በአንዳንድ ቤተ እምነት ኢየሱስ ክርስቶስ ጥብቅና የሚቆመው ከአብ ነው ይላሉ አያይዘውም ጥብቅናውን ከአማላጅነት ጋር ያያይዙታል። ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው።

ምክንያቱም ኢየሱስ ከአብ ጥብቅና ቆመ ማለት የሰው ልጆች ከሳሽ አብ ሆነ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ኢ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምርሆ ነው። አብ የኮነነውን ወልድ ይኮንናል አብ ያጸደቀውን ወልድም ያጸድቃል። አንዱ አጽድቆ አንዱ አይኮንንምና።

ስለዚህ የሰው ልጆች ከሳሽ ማነው? የኛ ከሳሽ ሰይጣን ነው።

👉 '' ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።'' ራእ 12:10

👉 '' እርሱም ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንም ይከስሰው ዘንድ በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር።'' ዘካ 3:1

ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ዘንድ ያለ ከሳሹን ዲያቢሎስን የሚያሳፍር ጠበቃችን ነው። ወደ ቀደመው ነገር ስንመለስ ዮሐንስ ኃጢአትን እንዳትሰሩ ብሎ ከዛም ደግሞ ብትሰሩ ግን ጠበቃ አላችሁ ማለቱ እንደምን ነው ቢሉ ፤ ይህ ቃል የተነገረው በክርስቶስ አምነው በንስሐ ለሚመላለሱ ፤ ሥጋውን ደሙን ለሚቀቡ ብጹአን ክርስቲያኖች ነው። ሰው ናቸውና በሀጢአት ቢወድቁወም ተጸጸተው ለሚመለሱት ነው የተናገረው። እነዚህ ሰዎች በሞቱ ጊዜ ሰይጣን ይከሳቸው ዘንድ ይመጣል። አንዲህ አድርገው፣ ሰርቀው ፣ ዘሙተው እያለ የሰሩትን መጥፎ ስራ መርጦ ሲናገር ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሃጢአት ሰርተዋል ግን ንስሐ ገብተዋል ተጸጽተዋል ተመልሰዋል እያለ ከሳሹን ያሳፍረዋል ይረታዋል።

ኢንግሊዘኛው መጽሐፍ ቅዱስ ጠበቃ የሚለውን ቃል Advocate ይለዋል፡፡ ማለትም ከአብ ዘንድ ያለው ጠበቃ ዳኛና ፈራጅም ሲለን ነው፡፡

Advocate ማለት ፍርድን የሚሠጥ ፈራጅ ጠበቃ ማለት ነዉ ይህም ጠበቃ የሚለው ቃል እንደሌሎቹ አባባል ለአማላጅነትን የሚገልጽ አይደለም።

ክርስቶስ ኢየሱስ የኛን ከሳሽ ሰይጣንን ያሳፍረው ዘንድ ፍቃዱ ይሁን።

ይቆየን።
❤4
“በከንቱ ስለምን ይገድሉናል?

በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ 21 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ አስታወቁ።

EOTCMK TV የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

በምሥራቅ አርሲ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ቀጥሎ ትላንት የካቲት 19 ቀን 2018ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በጀመረ ጥቃት 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች መገደላቸውን የሶማሌና ምሥራቅ አርሲ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።

ከሞቱት 21 ምእመናን መካከል አንደኛው ካህን ሲሆኑ
የሁሉም ሥርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት የካቲት 20/2018 ዓ/ም መፈጸሙንም ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ተናግረዋል።

እንደብፁዕነታቸው ተጨማሪ መረጃ ሁለት ምእመናን መታፈናቸውንና ስምንቱ ደግሞ የት እደደረሱ አይታወቅም።

በተጨማሪም የበርካቶች ንብረት መዘረፉንና በዚህ ሰዓት ላይ ከፍተኛ ውጠረት በመንገሱ በአካባቢው መንቀሳቀስ እንደማይቻል ብፁዕነታቸው አሳውቀዋል። የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ባስተላለፉት መልእክት የልጆቻችን ሞት የእኛም ሞት ነው ያሉ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኘተዋል።

አያይዘውም ገዳዮቻችን “በከንቱ ስለምን ይገድሉናል? የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ተጨማሪ የሰው ነፍስ እንዳይጠፋ የመከላከሉ ሥራ ሊሠራ ይገባል” በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።

Via EOTCMK
❤1😢1
የኢየሱስ ክርስቶስ መልአክ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል በምልጃው ይርዳን።

ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ነቢያትን የረዳቸው እርሱ ነው። እኛንም ይራዳን።
❤5
ገብርኤል ሆይ፥ በዚያ ድብቅልቅና ሽብር በሆነበት ዕለት ከጌታ እግረ መስቀል ሥር ለቆሙት ተረከዞችህና ጫማዎችህ ሰላም እላለሁ፤ ገብርኤል ሆይ የጌታን ትዕግሥት የአይሁድን ግፍ ተመልክተህ በታላቅ ዐደባባይ ላይ ሰይፈ ቁጣህን አምዘገዘግኸው ቅዱሳት አንስት ግን ክርስቶስ ተነሥቷል ስላልካቸው የትንሣኤውን ምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ሐዋርያት ሄዱ›› እንዲል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል ከዓለም በፊት አምላኩን ያወቀ ዓለም ልታልፍ ስትልም የወረወረው ሰይፍ እንደሚያርፍ ሊቃውንቱ ያስረዳሉ፡፡
❤4
ከወዴቱ ቆመናል?
😢2❤1
ከሴት ጋር የሚያመነዝር ግን አእምሮው የጐደለ ነው፤ እንዲሁም የሚያደርግ ነፍሱን ያጠፋል።

ምሳሌ 6:32
❤2
ወንድሜ ሆይ እግዚአብሔር ለአላማው ካዘጋጀህ ልክ እንደ ነቢዩ ዮናስ በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ብትገባ እንኳ እርሱ ከአንተ ጋር ነው ፤ እንደ ነቢዩ ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ብትጣል እርሱ ከእንተ ጋር ነው ፤ እንደ ዮሴፍ ዘመንድና ወዳጅ ቢከዳህ እርሱ ከአንተ ጋር ነው።

“በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።”
— መዝሙር 23፥4
❤6
#ኪራላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ
< ኪርዬ ኤሌይሶን> ነው። #ኪሪያ ማለት እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ ፡፡ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፡፡ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡

#ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፤ማረን" ማለት ነው።
#እብኖዲ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው። "እብኖዲ ናይናን" ሲልም " አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው።
#ታኦስ ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣አምላክ" ማለት ነው።
#ማስያስ ፦ የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሲህ" ማለት ነው።
#ትስቡጣ ፦ "ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም "ደግ ገዥ" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ- አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግስትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግስትከ -የሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን " ማለት ነው።
❤3
ዮሐንስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።

¹⁴ እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።

¹⁵ ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።

¹⁶ እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።

¹⁷ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህን አዛችኋለሁ።
❤3
“የሞትን ሥልጣን አጠፋ፤ ዲያብሎስንና ኃይሉን (ኃጢአትን) ሻረ፡፡ የብረት መዝጊያዎችን ሰበረ (ፍዳ መርገምን አጠፋ)፡፡ ሲኦልን በዘበዘ፡፡ የጣዖት ቤቶችን አፈረሰ፡፡ የምሕረትን በር ከፈተ፤ ይህችውም በደሙ የከበረች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ለዂሉ የዘለዓለም ሕይወት መገኛ የሚኾን ልጅነት የተገኘበት ሥጋውን ደሙን ሰጠን፤” (ቅዱስ ቴዎዶስዮስ፣ ሃይ. አበ. ፹፫፥፮)፡፡
🥰1
“በፈቃዱ በሥጋው የእኛን ሕማም ታመመ፤ በእውነት የእኛን ሞት ሞተ፡፡ ይኸውም የነፍስ ከሥጋ መለየት ነው፡፡ በፈቃዱ በተለየ አካሉ ሞትን ገንዘብ አደረገ፡፡ በሦስተኛውም ቀን በሥልጣኑ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፤ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱ ዕሪና ተቀመጠ፡፡ በኋለኛይቱ ቀንም በሙታን በሕያዋን ሊፈርድ ይመጣል፤” (ቅዱስ ፊላታዎስ፣ ሃይ. አበ. ፻፭፥፲፬)፡፡
❤2
“ሰማያት (ሰማያውያን መላእክት) የደስታ በዓልን ያደርጋሉ፤ ደመናት (ቅዱሳን) የደስታን በዓል ያደርጋሉ፡፡ ምድር (ምድራውያን ሰዎችም) በክርስቶስ ደም ታጥባ (ታጥበው) የፋሲካን በዓል ታደርጋለች (ያደርጋሉ)፡፡ ያከብራሉ (ታከብራለች)፡፡ ዛሬ በሰማያት (በመላእክት ዘንድ) ታላቅ ደስታ ኾነ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ የፋሲካን የነጻነት በዓል ታደርጋለች፡፡ የትንሣኤያችን በኵር ክርስቶስ ከሙታን ሰዎች ዂሉ ተለይቶ ቀድሞ ተነሣ፤” (ድጓ ዘፋሲካ)፡፡
👏1
“ሰውን ስለ መውደድህ ይህን ሁሉ አደረግህ፤ ከሙታን ተለይተህ ‹መቃብር ክፈቱልኝ፤ መግነዝ ፍቱልኝ› ሳትል ተነሣህ፡፡ ከእግረ መስቀል ሙታንን አስነሣህ ነፍሳትን ከሲኦል ማርከህ ለአባትህ አቀረብህ፤” (ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ ፩፥፳፬)፡፡
❤3🤩1