ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
1.5K subscribers
1.09K photos
20 videos
13 files
247 links
Download Telegram
'' እግዚአብሔር ትንሽ ይናገራል ብዙ ያደርጋል፥ እኛ ግን ብዙ እንናገራለን ጥቂት እንሰራለን።'' ( ቅዱስ ሳዊሮስ )
❤2
ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በአካል የሚገኝበት ጉባኤ ቅዳሴ የተባለው የቤተክርስቲያን የምሳጋና ጊዜ ነው።
❤3
አርባዕቱ እንስሳ ህዳር_8 በዓላቸው መንፈሳውያን አመስጋኞችና መዘምራን የምትሆኑ አራቱ እንስሳት ስለ አኛ ለምኑ፤ አርባዕቱ እንስሳ መንፈሳውያን ሰባሕያን ወመዘምራን

ሰዐሉ በእንቲአነ
(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ሰዓታት )

#_ኪሩቤል
🔥 ገጸ ሰብዕ
🔥 ገጸ አንበሳ
#_ሱራፌል
💥 ገጸ ላህም
💥 ገጸ ንስር

👉 ገጸ ሰብዕ ፦ ስለ ሰው ልጆች ይለምናል
ገጸ አንበሳ ፦ ስለ አራዊት ይለምናል
ገጸ ላህም ፦ ስለ እንስሳት ይለምናል
ገጸ ንሥር ፦ ስለ አዕዋፍ ይለምናል
( ሥንክሳር ኅዳር 8 ፥ ቁጥር 17 )

ቅዱስ ጄሮም እንዲህ አለ ፦
አርባዕቱ እንስሳት የድኅነታችን ምሥጢር የሆኑትን አራት ደረጀዋች ያስረዳሉ ።

ገጸ ሰብእ ፦ ሥጋዌውን ( ቃል ስጋ መሆኑን )
ገጸ አንበሳ ፦ ትንሣኤውን
ገጸ ላህም ፦ ንጹሕ መሥዋዕት ( ቤዛ ) መሆኑን
ገጸ ንሥር ፦ ዕርገቱን

አርባዕቱ አንስሳት
የጳጳሳት
የቀሳውስት
የዲያቆናት
የምዕመናን
( የቤተ ክርስቲያን አምድ እኚህ ናቸውና )

የእግዚአብሔርን ባሕርያት ያመለክታሉ።

ገጸ ሰብእ ፦ ጥበቡንና ዕውቀቱን
ገጸ አንበሳ ፦ ግርማውንና ኃይሉን
ገጸ ላህም ፦ ትዕግስቱን ፈታሒነቱን
ገጸ ንሥር ፦ ክብሩን ልዕልናውን

አንድም አርባዕቱ እንስሳት በአራቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ። “አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።” (ራእይ 4፥8)

አርባዕቱ_እንስሳት በእመቤታችን ድንግል ማርያም ይመሰላሉ። እነሱ መንበሩን ለመሸከም እንደተመረጡ፤ ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸክማዋለችና።

ወርኃዊ መታሰቢያ በዓላቸው በ 8 ነው።
❤3
ከላይ ያለው ቀለበት የቤተክርስቲያን ራስ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን።

ከታች ያለው ተንቀሳቃሽ ቀለበት እግዚአብሔር ወልድ ከሰማያት ሰማያት እኛን ስለማዳን ወደ ምድር መምጣቱን።

አራቱ ሰንሰለቶች 4ቱ ወንጌላውያ ማቴዎስ ሉቃስ ማርቆስ ዮሐንስ ናቸው።

በአንዱ ሰንሰለት ላይ ያለው ሶስቱ ደውሎች የሥላሴ ሶስት አካላት አጠቃላይ ድምር 12 ፥ ይህም የ12ቱ የሐዋርያት ምሳሌ ነው።

ዕጣኑ ጭስ የሚወጣበት ጉልላት መሳዩ የላይኛው ክፍል የእውነተኛዋ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምሳሌ ከታች ያለው ዕጣኑ የሚጨስበት ክፍል የክርስቲያኖች ጸሎት ቅድመ እግዚአብሔር እንደሚደር ያሳያል።
❤2
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ በከበረ ገናና ቅዱስ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ጸሎትና ምልጃ ይማረን ሐገራችንን ሰላም ያርግልን ከበሽታ ከጦርነት ከከፋ ጉስቁልና ይጠብቀን።
❤3
Another brother asked Abba Macarius, "How can I be saved?" The elder answered him, "Be like one dead: do not think about insults from people, nor of glory, and you will be saved." (Ancient Patericon, 10.45)
❤2
'' ሃጢአት ሰርተሃል? ወደ ቤተ ክርስቲያን ና!''
( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )
❤11👍1
አስገራሚው የፕሮቴስታንት አይዶሎጂ 🙄

በኢየሱስ ያመነ ተአምር መስራት እንደሚችል ይናገሩና የእርሱ የኢየሱስ እናት ቅድስት ድንግል ማርያምና መላእክት ሁሉ እንዲሁም በክርስቶስ ቅዱሳን የተባሉ ግን ምንም ማድረግ አይችሉም ይላሉ።

እንዴት ? 😂
👍3
ፕሮቴስታንት :- ቅዱሳን ከሞቱ በኋላ ምንም ማድረግ አይችሉም።

መጽሐፍ ቅዱስ :- 2ኛ ነገሥት 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ኤልሳዕም ሞተ፥ ቀበሩትም። ከሞዓብም አደጋ ጣዮች በየዓመቱ ወደ አገሩ ይገቡ ነበር።
²¹ ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፥ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት፤ የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ።

ቅዱሳን በሥጋ ቢለዩም ይፈውሳሉ ያድናሉ።
❤4👍3
ፕሮቴስታንት :- ቅዱሳን ከሞቱ በኃላ ስለ እኛ አይጸልዩም።

መጽሐፍ ቅዱስ :- “ከመውጣቴም በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ።” — 2ኛ ጴጥሮስ 1፥15

“ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።”
— ያዕቆብ 5፥16
እንኳን አደረሰን

Source - EOTCMK TV ታኅሣሥ 3 ቀን 2018 ዓ.ም

ቅድስት ድንግል ማርያም በ፶፻፬፻፹፭ ዓመተ ዓለም ከሐና እና ከኢያቄም በፈቃደ እግዚአብሔር ተወልዳ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ የኖረችው በወላጆቿ ቤት ነበር፡፡

ከዚህ በኋላ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸውን አስታውሰው ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሰጧት፤ ካህኑ ዘካርያስም ስለምግቧ በመጨነቁ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ታጥቆ እጅ ነስቶ ቢቆም ወደ ላይ ራቀበት፡፡

ከስምዖን ጀምሮ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም በተራ ቢሞክሩ በተመሳሳይ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ ብለው ሐና እና ኢያቄም እንዲቀርቡ አደረጓቸው፤ ለእነርሱም ራቀባቸው፤ ዘካርያስም ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› ባላት ጊዜ ቅድስት ማርያም ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መግቧት ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱም ሕዝቡም የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር ብለው አስገቧት፤ይህም ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር፡፡

ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ፲፭ ዓመት ሲሞላት ግን ለአቅመ ሔዋን በመድረሷ ከቤተ መቅደስ ትውጣልን በማለት አይሁድ በጠላትነት ተነሱባት፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ይህን ሰምቶ እመቤታችንን ጠየቃት «ኦ ወለተ እስራኤል እፎ ትፈቅዲ ትንበሪ፤ ልጄ እንደምን ሆነሽ ልትኖሪ ትወጂያለሽ?» አላት፡፡ እርሷም «ከእግዚአብሐር በታች ያለኸኝ አባት አንተ ነህ፤ በዚያውም ላይ እናት አባቴ አደራ ያሉህ አንተን ነው፤ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ፤» አለችው፡፡

ዘካርያስም ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ከነገደ ይሁዳ ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን በትራቸውን ሰብስበህ በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት ከቤተ መቅደስ አግብተህ ስትጸልይ አድረህ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት አውጣው ብሎ ምልክትም እሳይህአለው ብሎ ነገረው፡፡ እርሱም እንዳለው አድርጎ በማግሥቱ በትሮቹን አውጥተው ቢያዩ የዮሴፍ በትር አብባና አፍርታ ተገኘች፡፡

ከበትሩ ጫፍ ላይ «ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ዕቀባ ለማርያም ፍኅርትከ፤ ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ጠብቃት፤» የሚል ጽሑፍ አገኙ፤ርግብም መጥታ በራሱ ላይ አርፋለች፤ ስለሆነም ዮሴፍ እንዲጠብቃት ተወሰነ፡፡
❤4
ቅዱሳን ከሞቱ በዋላ ያማልዳሉ?

“በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።”— ራእይ 6፥10

🌼 ይህን ልመና የለመኑት በሥጋ ያረፉ ቅዱሳን ናቸው። ስለፈሰሰው ደማቸው እውነተኛ ፍርድን ከጌታ ጠየቁ። በሥጋ ሳይኖሩ ይህን ጥያቄና ልመናን ማቅረብ ከቻሉ ለኛ ለሰው ልጆች ጸሎት እንደሚያቀርቡ ትልቅ ማሳያ ነው።

ቅዱሳን ከሞቱ በኃላ በምድር ስላለው ነገር አያውቁም ማለት ሞኝነት ነው። እንደውም እውቀታቸው የበለጠ ይጨምራል እንጂ።

“ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።”— 1ኛ ቆሮንቶስ 13፥12
❤8
ቅዱስ ሚካኤል መልካም ነገርን ሁሉ ያሰማን
ሐሳባችንን ይሙላልን
ከመከራ ከበሽታ ከጉስቁልና ይጠብቀን።
❤10
የኢየሱስ ክርስቶስ መልአክ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል በምልጃው ይርዳን።

ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ነቢያትን የረዳቸው እርሱ ነው። እኛንም ይራዳን።
❤7🥰1
'' ወንድሜ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው።'' መኃልይ (Song of Solomon)
5:10

ወንድሜ የተባለው የክብር ጌታና አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከእመቤታችን በነሳው ሥጋና ደም ወንድማችን ሆኗልና።

'' ለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።'' (ዕብ 2:17)

'' ነጭና ቀይ ነው'' ማለት ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ማለት ነው። ነጭ :- መለኮት መሆኑን ፤ ቀይ :- ሥጋ ወይም ሰው መሆኑን ያሳያል።


ወልድ ዋሕድ!
👏5❤4
ከኪዳኖች ሁሉ ለእመቤታችን የተገባላት ኪዳን ይበልጣል ታላቅም ነው።
❤6
"አፉን የሚጠብቅ ነብሱን ይጠብቃል ከንፈሩን የሚያሞጦሙጥ ግን ጥፋት ያገኘዋል" ምሳሌ 13:3
🌸 " መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።" ሉቃ 1:35 🌸

✥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እመቤታችን መጥቶ '' መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል'' ያለበት ምክንያት ምንድን ነው? :- በመጀመሪያ ይህ መጸለል ወይም መጋረድ የሚለው ቃል በሐዲስ ኪዳን ሶስት ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ተጽፎ እናገኘዋለን። የመጀመሪያው በዚሁ በሉቃ 1:35 ላይ፣ ሁለተኛው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሶስቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ ተራራ ባወጣቸው ጊዜ '' ደመና 'ጋረዳቸው'' ይለናል..  እነዚህ ሐዋርያት ማለትም ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ያዕቆብ በደመና በመጋረዳቸው ሰማያዊ ምስጢርን አይተዋልና << የምሥጢር_ሐዋርያት >> ይባላሉ ማቴ 17፥5 - ማር 9፥7 - ሉቃ 9፥34። ሶስተኛው ደግሞ " ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ << ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን #ይጋርድ >> ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።" (ሐዋ 5:15) ቅዱስ ጴጥሮስ ሲያልፍ ህመምተኞቹን በጥላው እየጋረደ ይፈውሳቸው ነበር..." ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለችው ከተማ ድውያንንና በርኵሳን መናፍስት የተሣቀዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤ #ሁሉም_ይፈወሱ_ነበር ።" (ሐዋ 5:16)

✥ መጋረድ ሲባል ብዙ ትርጉም ይኖረዋል። አንድን ነገር ከሌላ ነገር #መለየቱን ለማሳየት ተጋረደ፣ ተሸፈነ የሚሉ ቃላትን ልንጠቀምን እንችላለን። ከላይ ያየናቸው ጥቅሶች አንጻር ስናየው መጸለል፣ መጋረድ የሚለው ቃል ልዩና በጎ ትርጉም አለው። ለምሳሌ ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው በሽተኞችን ባይጋርዳቸው ኖሮ አይፈወሱም ነበረ ሐዋ 5:15-16 ። ስለዚህ በቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ መጋረዳቸው ይበልጥ ለፈውስ አቅርቧቸዋል። ጥላው በላያቸው/ በአካላቸው ሲጋረድ ተፈወሱ። እንጂማ ጥላው ጋረዷቸዋልና ከቅዱስ ጴጥሮስ የማዳን ጸጋ ተለዮ፣ ራቁ ብለን ማሰብ የለብንም። ይልቁም ቀረቡ፣ ተካፈሉ ከፈውሱ ጸጋ በረከት ለማግኘት ተዘጋጁ ማለት ነው።

✥ ዳግመኛም ቅዱሳን ሐዋሪያው በጌታችን መሪነት ወደ ተራራው ከወጡ በኃላ ከሰማይ የመጣው ደመና ጋርዷቸው ሰማያዊ የሆኑ ምስጢራትን ማለትም የጌታ መልኩ/ሰውነቱና ልብሱ ሲበራ፣ እንዲሁም ታላላቅ ነቢያትን - ነቢዩ ሙሴንና ነቢዩ ኤልያስን በክብር ተገልጠው ተመልክተዋል። ደመና ጋርዷቸዋልና ምንም አላዩም ማለት አንችልም። እንደውም ምሥጢርን ያላዩት እነማናቸው ቢሉ በደመና ያልተጋረዱት ናቸው ከደመናው ውጪ የሆኑት። ቅዱሳን ሐዋርያትን በደመና ተጋርዳው ከዚህ ከዓለም ተለይተው ኢየሱስ ክርስቶስ ከነቢያት ጋር ሲነጋገር አይተዋል፣ ነቢያትንም አይተዋል የአብን ድምጽንም በግርማ ሰምተዋል። ስለዚህ ሐዋርያት በደመና በመጋረዳቸው ይበልጥኑ ወደ ምሥጢር መቅረባቸውን፣ መመረጣቸውን ያሳያል። ግዕዙም '' ወመጽአ ደመና ብሩህ #ወጸለሎሙ - ብሩህ ደመና መጥቶም #ሠወራቸው ይለናል (ማር 9:7)። ''ወጸለሎሙ'' የሚለውን ''ሠወራቸው'' ብሎ ይፈተዋል ትርጎሜ ወንጌል። አንድም ደመናው ከዓለም ይለያቸዋል ይደብቃቸዋልና - ሰማያዊው ምሥጢርን ለመማር ያቀረባቸዋል ማለቱ ነው።

✥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እመቤታችን መጥቶ '' መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል'' ያለበት ምክንያትንም ስንመለከት መልአኩ ወደ ታላቋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መጥቶ እሳተ መለኮትን፣ እግዚአብሔር እንደምትወልደው የምሥራቹን ቃል በነገራት ጊዜ እመቤታችን የጠየቀችው ጥያቄ ነበረ ይህም " ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?"(ሉቃ 1:34) የሚል ጥያቄ ነበር። በእውነቱ የመልአኩ ንግግር እመቤታችንን አስገረማት። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ግን ስለ ጽንሰቱ ሲነግራት፥ በጽንሰቱ ሂደት ውስጥ እንደሌላው ጽንሰት የወንድ ዘር ሊኖር እንደማይችል ይልቁኑስ መንፈስ ቅዱስ ወደ እርሷ እንደ ሚመጣና፥ የልዑልም ኃይልም እንደሚጸልልባት የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስንም እንደምትወልደው ነው የነገራት። መጸለል ፣ መጋረድ የሚለው ቃል እዚህ ጋር የሚያሳየው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን እግዚአብሔር ወልድን እንድትጸንሰው፣ እንድትወልደው በአጠቃላይ የማይቻለውን ነገር እንድትችለው አበጃጃት፣ አዘገጃጃት ለማለት ነው።

✥ በስነ ፍጥረት ስንመለከት " ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ #ሰፍፎ ነበር።" ( ዘፍ 1:2) ምንም ህይወት በሌለባት ምድር ህይወትን እንድትሰጥና ህይወት ያለባቸው ፍጥረታት መገኛ እንድትሆን ዘንድ አስቀድሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር። አንድም ሴቶች ሲጸንሱ በቅድሚያ እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ በእንሽሪት ውኃው ላይ በመስፈፍ ለጽንሱ ሕይወትን ይሰጠዋል፣ ነፍስንም ይዘራበታል - ሰው እንዲሆንም ያዘጋጀዋልና " እነሆ፥ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።"(መዝ 127:3) እንዲል። ዳግመኛም ጻዲቁ ኢዮብ '' የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።'' ( ኢዮ 33:4 ) በማለት ይገልጸዋል። 

✥ አሁን መመልከት ያለብን ግን በእመቤታችን ማህጸን ውስጥ የሚጸነሰው ፍጡር ሳይሆን ፈጣሪ ነው። የዓለም ሁሉ ቤዛ ነው፣ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ይህን ጽንስ ልዮና አስገራሚ ያደርገዋል። እመቤታችን በእግዚአብሔር የተፈጠረች ፍጥረት ናት ምድራዊ እናትና አባትም አሏት። የማይቻለውን አምላክን ጸንሳ በሆዷ እንትይዘውና እንድትወልደው የሚያስችላት መንፈስቅዱስ ነውና። ስለዚህ ይጸልልባታል ወይንም ይጋርዳታል ሲል ከክብሮች ሁሉ በላይ ለሆነው ክብር ለአምላክ እናትነት ፣ ወደ ልዩ ሰማያዊ ምስጢር ያቀርባታል ይህም ጌታዋን እግዚአብሔርን እንድትጸንሰውና እንድትወልደው ማህጸኗን ያዘጋጀዋል ማለት ነው። እንጂ እመቤታችን ሃጢአት የኖረባት ሆና አይደለም። ክብር ለእመቤታችን ይሁን። አሜን።

ይቆየን።
👍1