ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ልደት ‹‹ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ/ ማርያምስ (ማርያም ግን) ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች፡፡›› በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሥርወ ልደቷ ‹‹እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ…ሐረገ ወይን/ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿም በሰማይ ያሉ…የወይን ሐረግ›› በማለት የተወለደችው በምድር ከነበሩት ኢያቄምና ሐና መሆኑን የወለደችው ግን ሰማያዊውን ንጉሥ እንደሆነ በማመስጠር ዘምሯል፡፡ በዚህም ሰውና እግዚአብሔርን ያገናኘች መሰላል መሆኗል ገልጾ አስተምሯል፡፡
🥰2
❄ በእንተ ቅዱሳን መላእክት ❄
" ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።" (ራእ 19:10)
ይህን በመጥቀስም ለመላእክት መስገድ ተገቢ አይደለም የሚሉ ክፍሎችም አሉ። ዳሩ ግን የመልአኩ አባባል ካለመረዳት እንጂ ለመላእክት መስገድ ከሃይማኖት ውጭ ሆኖ ዮሐንስ ባለማወቅ የሰገደለት ሆኖ አይደለም። ይህንንማ እንዳንል የሰጋጁ የዮሐንስ ማንነት ያግደናል። ዮሐንስ ድንግላዊና የጌታ ሐዋርያ ከመሆኑም ሌላ ጌታ የሚወደው በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ፤ ወንግጌልን መልእክታትን የጻፈ ፥ እንዲሁም የዓለምን ፍጻሜ በራእይ ያየ ነው ነው።
ይህን ያህል የጌታ ባለሟል የሆነ ቅዱስን ሰው ለትንሿ ለነገር ለመላእክት መስገድ ተገቢ አለመሆን አጥቶት በስሕተት ሰገደ ማለት የጻፋቸው ወንጌሎችም መልእክታትም ስሕተት አላቸው ማለት ነው።
ይህ ማለት ግን ሰው እንደ እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት አይደለም። እሱ በፍጹም እምነት ውስጥ ሳይሆን እሱ ማን መመለክ እንዳለበት ሳያውቅ ለእኛ ማሳወቅ አይችልምና። ስለዚህ በስሕተት ሰገደ ማለት ከፍተኛ ስህተት ነው።
ዮሐንስ ለመልአኩ የአክብሮት ስግደት ያቀረበው ለመላእክት መስገድ ተገቢ መሆኑን ስላወቀ ነው። መልአኩም ደግሞ #አትስገድልኝ ማለቱ የዮሐንስን ክብርና ማዕረግ መግለጡ ነው። ዮሐንስም በክብሩ ከመልአኩ እኩል ሆኖ ነበርና፥ እንድም በስልጣን በልጦት ነበር #ካህን ነውና ስልጣነ ክህነትህ ከእኔ ስልጣን ትበልጣለች ሲለው ነው..ስለ ስልጣነ ክህነት ታላቅነት " የትዳር ጉዳይ ይቅርና በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን?" (1ኛ ቆሮ 6:3) ተብሎ ተጽፏልና።
ስግደት ደግሞ የበላይና የበታች መግለጫ ስለሆነ አንተ'ኮ በክብር ከእኔ እኩል ነህ። ስለዚህ ለእኔ ልትሰግድ አይገባም ቢለውም ዮሐንስ ግን ከመስጊድ ወደ ኋላ አላለም ትሁት ነውና። ይህን ማረጋገጥ ከፈለግን ራእይ 22:8-9 እንመልከት.. '' ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።'' (ራእ 22:8-9)
እንግዲህ ዮሐንስ ተሳስቶ ሰገደ ቢባል እንኳ ሁለት ጊዜ ይሳሳታል? የመጀመሪያው አንሶ? እንግዲህ አባባሉ የትሕትና አባባል መሆኑ ግልጽ ነው።
'' መላእክትም ከሰይጣናት የሚለያቸው አንዱ ይህ ነው። ሰይጣናት የማይገባቸውን ክብር ሁሉ በትዕቢት ይቀበላሉ ፤ መላእክት ግን የሚገባቸው እንኳን ቢሆን ስለ ትህትና ይተዋሉ። ክብርን ሁሉ ለጌታቸው ይሰጣሉ። '' ቅዱስ እንድርያስ ዘቂሳርያ
ይቆየን 🍋

❤2🥰2
ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው ቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴጥርስ ማለት ኮኩኽ ሃይማኖት ማለት ነው። ማቴ. ፲፮፡፲፰ (16፡18) በዕራይስጥ ኬፋ ይለዋል። ቀዳሚ ስሙ ስምዖን ነው። ዮሐ.፩፡፵፭ (1፥45)፡፡ የአባቱ ስም ዮና ሲሆን ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ ዮና ከነገደ ስምዖን የምትሆን አንዲት ሴት አግብቶ ቅዱስ ጴጥሮስን ወለደ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ከተወለደ በኋላ እንደ ሕገ ኦሪት ትእዛዝ በስምንተኛው ቀን ወደ ግዝረት ቤት አግብተው ስሙን በእናቱ ነገድ ስም ስምዖን ብለው ሰይመውታል፡፡
እድሜው አምስት ዓመት ሲሆን እንደ አይሁድ ሥርዓት ሕገ ኦሪትን እየተማረ እንዲያድግ በቤተ ሳይዳ አጠግብ ወደሚገኘው ወደ ቅፍርናሆም ሰደዱት፡፡ በዘመኑ በባህር ዳር በምትገኘውና ታላቅ የንግድ መነኸርያ በነበረችው ቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረችው በቅፍርናሆም የሮም ጭፍሮች አለቃ የነበረው ኢያኢሮስ አይሁድን ደስ ለማሰኘት አሰርቶት በነበረው ምኩራብ እየተማረ አደገ፡፡
ከዚያም በኋላ በዚያ ከተማ ቤት ሰርቶ ኮን ኮርድያ (ጴርጴቱዋ) የምትባል ሚስት አግብቶ እንደ አባቱ እንደ ዮና ይተዳደር የነበረው ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ ነበር። ዓሣ እያጠመደና እየሸጠ ይኖር ነበር፡፡ ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗለ። ማቴ. ፬፡፲፱ (4፡19) ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከተቀበሉ በኋላ መዲናቸው ኢየሩሳሌም አንድ ዓመት ካስተማሩ በኋላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን ዕዳ በዕዳ ከተከፋፈሉ ጊዜ ርዕሰ ሐዋያ ነውና ሮምን ደርቦ ሰርቶታል። በሮምም ፳፭ (25) አስተምሯል። ከዚያ በፊ ግን በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ጳንጦስ፣ በገላቲያ፣በቀጳዶያና በቢታኒያ አስተምራል። በትምህርቱም ጣቢታ ከሞት አስነስቷል። ሐዋ. ፱፡፴፪-፴፬ (9፡32¬-34) ያስተማራቸው ምዕመናም ከሃማኖታቸው እንዳይወጡ ፪ (2) መዕክታትን ጽፎላቸዋል። ንጉሱ ኔሮን ቆሳር መምለኬ ጣኦት ነበርና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር። ለጣዖትም እንዲሰግድ ባስገደደው ጊዜ ለጣኦ አልሰግድም በማለቱ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት። አይሁድ ሲጣሉት ወደ ጌታ ቢያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር። ይዞ ዳግም ቢሰቅሉትም ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው። በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅሎታል። ሥጋውን ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቱ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንቦ እንዳይፈርስ በማረ በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል።

🔥3❤2
በዚህች ቀን ከሮም ነገስታት ወገን የሆነው አባ ኪሮስ አረፈ፡፡ አባ ኪሮስ አባቱ ንጉስ ዮናስ እናቱ አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ነው፡፡ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ወለዱ፡፡
አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡
በ17 ዓመቱ ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡ ከዚህ በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላእክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይተውት ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል፡፡
ቃል ኪዳናቸውም ፡- መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡ በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ በተወለዱ 270 ዓመቱ ሐምሌ 8 አርፏል፡፡
አባታችን አቡነ ኪሮስ በመዲናችን አዲስ አበባ በኮተቤ መስመር በስማቸው ታላቅ ቤተክርስቲያን አላቸው ሐምሌ 8 ታቦታቸው ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡ ልጅ የሌላቸው እናትና እህቶቻችን ገድላቸውን አዝለው ልጅ እንዲሰጧቸው ስለት ይሳላሉ በዓመቱም ልጅ አዝለው መጥተው ስለታቸውን ይከፍላሉ፡፡ ይህንንም በአይናችን አይተን በጆሯችን ሰምተን ይኸው እንመሰክራለን ፡፡ ከቅዱሳን ሁሉ ረድኤታቸውንና በረከታቸውን ይደርብን፡፡

❤6
ቅዱስ ሉክያኖስ
በዚህችም ዕለት ቅዱስ ሉክያኖስ ከሌሎች አራት ሰማዕታት ጋራ ሰማዕት ሆነ። ይህም ቅዱስ አስቀድሞ የጣዖት ካህን ነበረ የሰማዕታትንም መከራቸውን በእሳት ሲአቃጥሏቸውና ሕዋሳታቸውን ሲቆራርጧቸው ሲሰቅሏቸው ከእሳት ምድጃ ውስጥም ሲጥሏቸው ምንም ምን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው በአየ ጊዜ ከዚህ ሥራ የተነሣ አደነቀ ክብር ይግባውና በጌታችን አመነ ያገለግላቸው የነበሩ ጣዖታት ከእሳት ቢጥሏቸው ፈጥነው ይቃጠላሉ እንጂ ይህን ሥራ ሊሠሩ እንደማይችሉ ተረድቷልና።
ዳግመኛም እንዲህ አለ ይህን ድንቅ ሥራ የሚሠራ አምላክስ በእውነት እርሱ አምላክ ነው። ከዚህ በኋላም በንጉሥ ፊት እኔ ክርስቲያን ነኝ ክብር ይግባውና በክርስቶስ አምናለሁ ብሎ በግልጥ ጮኾ ተናገረ። ንጉሡም ወደርሱ አቅርቦ ጣዖት ማምለክን እንዳይተው መከረው ወደ አምልኮ ጣዖት ይመለስ እንደሆነ ብሎ ብዙ ቃል ኪዳኖችን ገባላት።
እርሱ ግን አልሰማውም ሥቃዩንም አልፈራም ከዚህም በኋላ ንጉሡ ጽኑዕ ሥቃይን ሊአሠቃየው ጀመረ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት መንጋጋውንም በደንጊያ እንዲሰብሩት ታላቅ ግርፋትንም እንዲገርፉት አዘዘ።
ከዚህ በኋላም አራት ክርስቲያን እሥረኞች ቀረቡና ከእርሱ ጋራ አቆሟቸው ንጉሡም ለአማልክት ዕጣን ዕጠኑ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሥቃይን አሠቃያችኋለሁ አላቸው። እነርሱም ለስሕተቱ አልታዘዙለትም በላያቸውም ተቆጥቶ በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመራቸው ያንጊዜ ዝናብ ዘነበ እሳቱንም አጠፋው።
ቅዱስ ሉክዮስን ግን እንደ አምላክህ እሰቅልሃለሁ ብሎ በዕንጨት መስቀል ላይ እንዲሰቅሉት አዘዘ በረጃጅም ችንካሮችም ሥጋውን ሁሉ ቸነከሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። እነዚያን አራቱን ሰዎችም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።

❤3👏2
እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው
ዘለዓለማዊ የሚለው ቃል ከቋንቋነቱ አኳያ ሲታይ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ለመግለጽ ደካማ ወይም አናሳ ቃል ሆኖ የሚታይ ይመስላል። በእርግጥም የቃሉ ገላጭነት የደከመ ወይም የጠበበ ነው። ይሁንና ሌሎች ቃላት ቢሆኑም የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ባሕርይ በፍጹምነት የመግለጽ ብቃት አላቸው ብሎ መገመት አስቸጋሪ መሆኑ አይቀርም።
የሆነ ሆኖ ግን ዘለዓለማዊ ከሚለው ቃል መረዳት የሚቻለው፣ እግዚአብሔር አምላክ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በማዕከለ ዓለም ያለ፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፣ ፍጻሜ /መጨረሻ/ መነሻና መድረሻ የሌለው፣ እርሱ ራሱ መጀመሪያና መጨረሻ፣ የሆነ፣ የነበረ፣ ያለና የሚኖር ኅልፈትና ሽረት የሌለበት አምላክ መሆኑን ነው።
ማስረጃ
«ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም፥ ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ አንተ ነህ።» መዝ ፹፱፥፪።
«የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፣ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።» ኢሳ ፵፬፥፮።
«ሙሴም አግዚአብሔርን፦ እነሆ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናነተ ላከኝ ባልሁም ጊዜ ስሙስ ማነው ባሉኝ ጊዜ ምን እላቸዋለሁ? አለው። እግዚአብሔርም ሙሴን ያለና የሚኖር እኔ ነኝ አለው።» ዘጸ ፫፥፲፫።
«ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።» ዮሐ ራእ ፩፥፰።

🥰5
Abba Dorotheos said: No matter what kind of sorrow comes to you, don't blame anyone but yourself, and say, "This has happened because of my sins."
(St. Ignatius Brianchaninov, Patericon)
(St. Ignatius Brianchaninov, Patericon)
❤3
የቅድስና ደረጃዎች(መንፈሳዊ ማዕረጋት
፩. ጽማዌ
ይህ ማዕረግ የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን ትህትናን፤ ራስን ዝቅ ማድረግን፤መታገሥንና ነገሮችን በውስጥ ይዞ ማሰላሰልን ወዘተ…ይይዛል፡፡እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው የዚህን ዓለም ውጣ ውረድ ከማውራት ይከለከላል በብዙ ነገሮች ላይ ዝምታን ይመርጣል፡፡
፪. ልባዌ
ይህ ማስተዋልና ልብ ማለትን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች የሚገኙበት ደረጃ ነው፡፡እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ ሰዎች ልናገር ሳይሆን ልስማ ፤ ላስተምር ሳይሆን ልማር ይላሉ፡፡ የመጽሐፉ ቃል የሚለውን ማስተዋልና አብዝተው ኃጢአታቸውን ያሰላስላሉ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ፡፡
፫. ጣዕመ ዝማሬ
እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው አንደበቱን ከንባብ ልቡናውን ከምሥጢር ያቆራኛል፡፡እዚህ ደረጃ የደረሱ ቅዱሳን አንደበታቸው ዝም ቢል በልባቸው ግን ዝም ብለው አያውቁም ከሰውነታቸውም ንጽሕና አይለይም፡፡የሚያነቡትን መጽሐፍና የሚጸልዩትን ጸሎት ምሥጢሩን በደንብ እየተረዱት ስለሚያደርጉት አይሰለቻቸውም፡፡ እነዚህ ከ1-3 ያሉት የንጽሐ ሥጋ (ወጣኒነት) ማዕረጋት ናቸው፡፡
፬. አንብዕ
እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ ሰዎች የጌታቸውን ፍቅር እያሰቡ እስከ ሞትና መከራ የተጓዘውን ጉዞ እያሰቡ ዘወትር ያለቅሳሉ፡፡ ያለምንም ተጽዕኖ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይወርዳል፡፡ ይህንንም የሚያደርጉት ለዚህ ዓለም ፍላጎታቸው መሟላት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ምሕረትና ቸርነት በመናፈቅ ነው፡፡
፭. ኩነኔ
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ሥጋዊ ፈቃድ ሁሉ ለነፍስ ፈቃድ ይገዛል ፤ ነፍስ በሥጋ ፍላጎት ላይ ትሰለጥናለች፡፡ ምድራዊ (ሥጋዊ) ፍላጎቶች ይጠፉና ሰማያዊ"(የነፍስ) ፍላጎቶች ቦታውን ይወርሳል፡፡
፮. ፍቅር
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ማንንም ሳይመርጡ ወዳጅንም ጠላትንም መውደድ ይጀምራሉ፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ያደረገውን ታላቁን የፍቅር ሥራ እርሱን በመምሰል ሕይወት በመኖር በተግባር ይገልጻሉ፡፡
፯. ሁሰት
ከዚህ ማዕረግ የደረሱ ቅዱሳን ባሉበት ቦታ ሆነው ሁሉን ነገር ማየት ይችላሉ፡፡የቦታ ርቀትና የገዘፉ ቁሶች ሳያግዳቸው ፤ ሁሉን ያያሉ፡፡እነዚህ ከ4-7 ያሉት የንጽሐ ነፍስ (ማዕከላዊነት) ማዕረጋት ናቸው፡፡
፰. ንጻሬ መላእክት
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ መላእክትን ሲወጡና ሲወርዱ ማየት ይቻላል፡፡
፱. ተሰጥሞ
ከዚህ ማዕረግ የደረሰ ሰው በብርሃን ባሕር እየተመላለሰ በምድሪቱ ላይ ያለውን ሁሉ ማወቅ መረዳትና መመልከት ከመቻላቸውም አልፈው ሥሉስ ቅዱስ ከመመልከት በስተቀር በሰማያት ያለውንም ምሥጢር ወደ መረዳት ይደርሳሉ፡፡
፲. ማዕረገ ከዊነ እሳት/ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ
ከዚህ ማዕረግ የደረሱ ሰዎች ሥላሴን በዙፋኑ ላይ ሆኖ እንደ እስጢፋኖስ መመልከት ይጀምራሉ፡፡እንዲሁም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በአካለ ነፍስ ተነጥቀው ወደ ሰማያት በመውጣት ሰማያትን መጎብኘት ወደ መቻል ይደርሳሉ ተሐዋሲያን እንኳን እነሱ ላይ ሲያርፉ እየተቃጠሉ ይወድቃሉ እነዚህ ንጽሐ ልቦና (ፍፁምነት) የቅድስና ማዕረግ የደረሱ ናቸው፡፡
የቅዱሳንን መንገድ እንድንከትል የአምላካችን መልካም ፈቃድ ይሁንልን ከቅዱሳን ረድኤት በረከት ያሳትፈን!
ምንጭ https://www.atronsmedia.com/2021/10/blog-post_59.html?m=1

አትሮንስ ሚዲያ - Atrons Media
የቅድስና ደረጃዎች(መንፈሳዊ ማዕረጋት)
የቅድስና ደረጃዎች(መንፈሳዊ ማዕረጋት) _______________________________ ቅድስና በአንድ ሌሊት የሚደረስበት ሳይሆን የብዙ ጊዜ መንፈሳዊ ተጋድሎን ንጹህ ልቡናን ትዕግስትን የሚጠይቅ ቅዱሱን እግዚአብሔርን ...
❤4😢1
በዚህ ቀን ሐምሌ 19 - የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የኢየሱስ ምስክር የሆኑትን ቅድስት ኢየሉጣና ልጇ ቅዱስ ቂርቆስን ከመከራ አዳናቸው። ጌታ ኢየሱስ በዚህ በከበረ ቅዱስ መልአክ ጸሎት ይማረን። እኛንና ሐገራችንንም ከዘረኝነት ፤ ከመከራ ፤ ከድህነት ከሁሉ ፈተና ይታደገን።
❤6
አባ ዮሐንስ እንዲህ አለ፡- ቀላል ሸክሙን ማለትም ራስን መተቸትን ትተን ከባድ ሸክም ተሸከምን ይኸውም ራስን ማጽደቅ ነው።
🥰2😢1
St. Cyril of Alexandria
Hail to Mary, mother of God, Majestic treasure of the whole world, the lamp unquinchable, the crown of virginity.

ሐምሌ ሃያ አምስት በዚች ቀን የቅዱስ መርቆሬዎስ ቅዳሴ ቤቱ እና ልደቱ ነው፣ የደብረ ሊባኖሱ አባ ሕፃን ሞዐ አረፈ፣ ቅድስት ቴክላ አረፈች፣ ቅዱስ እንዲኒና በሰማዕትነት አረፈ፣ አባ ይስሐቅ በሰማዕትነት ሞተ፣ ቅድስት ኢላርያ ሰማዕት ሆነችች፣ ቅዱሳት ቴክላና ሙጊ ሰማዕታት ሆኑ፣ ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት ሆነ፣ ቅዱስ ዱማድዮስ አረፈ፣ ነቢዩ ቅዱስ ሄኖክ የዕርገቱ መታሰቢያ ነው፡፡
ከስንክሳር 👇
ቅድስት ቴክላ
በዚህችም ቀን ከኒቆምድያ አገር ሐዋርያዊት ቅድስት ቴክላ አረፈች። ይህችም ቅድስት በቅዱስ ሐዋርያ በጳውሎስ ዘመን ሐዋርያዊት ሆነች። ቅዱስ ጳውሎስም ከአንጾኪያ ከተማ በወጣ ጊዜ ወደ ኒቆምድያ ከተማ ሔደ በዚያም ስሙ ሰፋሮስ የሚባል ምእመን ሰው ነበረ ቅዱስ ጳውሎስን ወስዶ በቤቱ አኖረው ብዙ አሕዛብም የሐዋርያው የጳውሎስን ትምህርት ይሰሙ ዘንድ በእርሱ ዘንድ ይሰበሰቡ ነበር። ይህች ቅድስት ቴክላም በቤቷ መስኮት ተመለከተች የሐዋርያውንም ትምህርት ሰማች እንዲሁም ትምህርቱን እያዳመጠች ሳትበላና ሳትጠጣ ሦስት ቀኖች ቆየች ትምህርቱም በልቧ አደረ አባትና እናቷ ቤተሰቦቿ ሁሉ አዘኑ። ከምክርዋም እንድትመለስ ሐዋርያው ጳውሎስንም እንዳትከተል ለመኑዋት ነገር ግን አልሰማቻቸውም።
ሁለተኛም አባቷ ወደ ንጉሡ ሒዶ ሐዋርያው ጳውሎስን ከሰሰው ንጉሡም ወደ እርሱ አስቀርቦ ስለ ሥራው ጠየቀው። ነገር ግን የሚቀጣበት ምክንያትን በላዩ አላገኘም ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስንም እንዲአሥሩት አዘዘ።
ይህች ቅድስት ቴክላም ልብሶቿንና ጌጦቿን ከላይዋ አስወገደች። ወደ ቅዱስ ጳውሎስም ሒዳ ከእግሩ በታች ሰገደች በእርሱም ዘንድ እየተማረች ተቀመጠች። ወላጆቿም በፈለጓት ጊዜ አላገኟትም በሐዋርያው ጳውሎስ ዘንድ እርሷ እንዳለች ሰዎች ነገሩዋቸው በመኰንኑም ዘንድ ከሰሱዋት እርሱም በእሳት እንዲአቃጥሉዋት አዘዘ። እናቷም ስለርሷ ሴቶች ሁሉ እንዲገሠጹና እንዲፈሩ አቃጥሏት እያለች ጮኸች ብዙዎች የከበሩ ሴቶች በሐዋርያው ጳውሎስ ትምህርት አምነው ነበርና እርሷ ግን በሚአቃጥሏት ጊዜ ልቧን አጽንታ ቅዱስ ጳውሎስን ተመለከተችው።
ዳግመኛም ሲጸልይ ቅዱስ ጳውሎስን አወጡት በላይዋም በመስቀል ምልክት አማተበ። ራሷንም ወደ እሳቱ ምድጃ ወረወረች። ሴቶችም ያለቅሱላት ነበር። ያን ጊዜም እግዚአብሔር ብዙ ዝናብን በረድና መብረቅን ላከ የእሳቱም ምድጃ እንደ ቀዝቃዛ ጠል ሆነ ቴክላም ሩጣ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ተሠውሮ ወደ አለበት ቦታ ደረሰች ራሷንም ላጭቶ ትከተለው ዘንድ ለመነችው እንዲሁም አደረገላት።
ወደ አንጾኪያ ከተማም በሔደች ጊዜ ከመኳንንቶች አንዱ ሊአገባት ፈለገ መልኳ እጅግ ውብ ነበረና እርሷም ዘለፈችው ረገመችውም እርሱም በዚያች አገር ገዥ በሆነ በሌላ መኰንን ዘንድ ከሰሳት እርሱም ለአንበሶች እንዲጥሏት አዘዘ። በአንበሶች መካከልም ሁለት መዓልት ሁለት ሌሊት ኖረች እነዚያም አንበሶች እግርዋን ይልሱ ነበር እንጂ ምንም አልከፉባትም።
ከዚህም በኋላ በሁለት በሬዎች መካከል አሥረው በከተማው ውስጥ ሁሉ አስጐተቷት። ነገር ግን ምንም ምን ክፉ ነገር በላይዋ አልደረሰም ከዚያም በኋላ ለቀቁዋት። ወደ ቅዱስ ጳውሎስም ሔደች እርሱም አረጋጋት አጽናናትም። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድትሰብክ አዘዛት።
ከዚህም በኋላ ቆሎንያ ወደሚባል አገር ሔዳ ሰበከች ከዚያም ወደ አገርዋ ሔዳ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረች አባትና እናቷንም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን መለሰቻቸው።
ተጋድሎዋንም ፈጽማ በሰላም አረፈች። የሐዋርያነት አክሊልንም ተቀበለች። ሥጋዋም በግብጽ ደቡብ ሰንጋር በሚባል አገር እስከ ዛሬ አለ። ከሥጋዋም ብዙ ድንቅና ተአምር ተገለጠ።
ቅዱስ እንዲኒና
በዚህችም ቀን ባና ከሚባል አገር ቅዱስ እንዲኒና በሰማዕትነት አረፈ።ይህም ቅዱስ ጎልማሳ ነበር። ወላጆቹም ከሀገር ሽማግሌዎች የሆኑ ምዕመናን ነበሩ።
ከዚህም በኋላ ይህ ቅዱስ ወደ እንዴናው ከተማ ሔደ። በመኮንኑም ፊት በመቆም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኮንኑም በፍላፃ ይነድፉት ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት ነገር ግን ከፍላፃዋች ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም።
ከዝህም በኋላ አሥሮ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው ከእርሱም ጋር ቅዱስ ቢማኮስና ሌሎች ሁለት ሰማዕታት ነበሩ። የእስክንድርያውም ገዥ አሠራቸው።
ቅዱስ እንዲኒናን ግን በአፍንጫው ብዙ ዳም እስኪፈስ ድረስ ዘቅዝቆ ሰቀለው። በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም ብዙ አሠቃየው። ከማሠቃየትም በሰለቸ ጊዜ ፈርማ ወዳሚባል አገር ላከው።
በዚያም በወህኒ ቤት ቅዱስ ሚናስን አገኘውና ደስ አለው። እርስ በርሳቸውም ተፅናኑ። ከዚህም በኋላ መኮንኑ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ አሠቃየው በእሳት ባጋሉትም መጋዝ ሥጋውን ሰነጥቀው። በብረት ምጣድ ውስጥም አበሰሉት ጌታችንም ያለጉዳት በጤና አስነሣው።
መኮንኑም ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንተአምራት የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ከሥጋውም ታላላቅ ተአምራት ተደረጉ። ለበሽተኞችም ፈውስ ተደረገ።
አባ ይስሐቅ ሰማዕት
በዚህችም ቀን ደግሞ ይስሐቅ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ቅዱስ ሳምሳ ከምባል አገር ነበር እሱም የአታክልት ቦታዎች ጠባቅ ነበረ ደግ የዋህና ፁሙድ አገልጋይ ነበረ ሰጋም አይበላም ነበር ወይንም አይጠጣም ነበር በየሁለት ቀን ይፆም ነበረ ቅጠልም ይበላ ነበረ ድሆችንና ችግረኞችንም ይጎበኛቸው ነበረ ከደመዙም የምተርፈውም ይሰጣቸዋል።
ክብር ይግባውና ጌታችንም በራእይ ተገለጠለትና ወደ መኩንኑም ሒዶ በቅዱስ ስሙ እንዲታመን አዘዘው ከዝህም ቡኃላ ብዙ ቃል ክዳን ሰጠው ያዘጋጀለትንም የደስታ አክልሎችን ተስፍ አስደረገው።
በነቃ ግዜም እጅግ ደስ አለው ተነሥቶም ከእርሱ ያለውን ገንዘብ ለድሆች ሰጠ ከዝያም ቡኃላ ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ወደ መኩንኑም ደርሶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኩንኑም ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው በእሳትም አቃጠለው ሕዋሳቱንም ቆራርጦ ሰቀለው በመንኩራኲርም አበራየው ጌታችንም ያጸናውና ይፈውሰው ነበር ከመሠቃየቱም የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ የሰማዕትነትንም አክልሊ በመንግስተ ሰማያት ተቀበለ።
ከዚህም በኃላ ምእመናን ሰዎች ከሀገሩ ሳምሳ መጥተው ሥጋውን ወሰዱ በአማሩ ልብሶችንም ገንዘው የመከራው ዘመን እስክፈጸም ድረስ በመልካም ቦታ አኖሩትከዝያም ቡኃላ ውብ የሆነች ቤተክርስትያን ሠሩለት ሥጋውን በዝያ አኖሩት ከእርሱም ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
ቅድስት ኢላርያ
ዳግመኛም በዚች ቀን በድሜራ አቅራብያ ድምድል ከሚባል አገር ቅድስት ኢላርያ በሰማዕትነት ሞተች። የዚችም ቅድስት ወላጆቿ ደጎች ምእመናን ነበሩ እርሷዋም በስጋዋና በነፍሷ የነጻች ነበረች ሁሉ ጊዜም ተጻምና ትጸልይ ነበረች።
አሥራ አንድ አመትም በሆናት ጊዜ እርሷ ቆማ ስትጸልይ ጌታችን ታላቅ። ብርሃንን ገለጠላት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሩፍኤልም ተገልጦ እንድህ አላት ተጋድሎ ተዘርግቶ ሳለ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ለምጋደሉም አክልሎች ተዘጋጅተው ሳሉ አንቺ ለምን ከዝህ ተቀምጣሻል አላት።

🥰1
ይህንንም በሰማች ግዜ ደስ አላት ገንዘቧዋንም ሁሉ ለድኖችና ለችግረኞች ሰጥታ ጣው ወደ ምባል አገር ሔደች ከዝያም ስርስና ወደ ምባል አገር ሒዳ በመኩንኑ ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰም ታመነች ጌታችንም ሳኑሲ ለሚባል ሰው ለዝች ቅድስት ከእርሷ የሚሆነውን ነገረው።
ባያትም ጊዜ በእርሷ ደስ አለው አረጋጋት ልቧንም አጸናናት መኩንኑም ታላቅ ሥቃይን አሰቃያት ሥጋዋን ሁሉ ሠነጣጠቀ በእሳት ያጋሏቸውንም የብረት ችንካሮች በሥጋዋ ውስጥ ቸነከሩ።
ከዝህም ቡኃላ ከአምስት መቶ ባልንጀራሞች ሰማዕታት ጋራ አሠራት በመርከቦችም ከእርሱ ጋራ ወስዳቸው እነርሱም በመርከብ ስጓዙ አንበሪ መጥቶ ከእናቱ እቅፍ አንዱን ሕፃን ልጅ ነጥቆ ወሰደ እናቱም ከእርሱ በቀር ሌላ ስለሌላት እጅግ አዝና አለቀሰች ይች ቅድስትም አይታ ራራችላት ስለእርስዋም ጌታችንን ለመነችው ጌታችንም አንበርውን አዘዘውና ሕፃኑን ደኅና እንደሆነ ወደ እናቱ መለሰው ምንም ጥፋት አላገኘውም።
ከዚህም በኃላ ሕዋሳቷን ቆራረጡ የእጆቿንና የእግሮቿን ጥፍሮች ነቀሉ ምላሷንም ቆረጡ እግሮቿንም በብረት ችንካሮች ቸነከሩ። በብረት ዐልጋ ላይም አስተኝተው ከበታችዋ እሳትን አነደዱ። ነገር ግን ምንም ምን ጥፋት አልደረሰባትም ክብር ይግባውና ጌታችን አድኗታልና።
መኮንኑም እርሷን ከማሠቃየት የተነሣ በሰለቸ ጊዜ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች።
ቅዱስ አበከረዙን
በዚችም ቀን ዳግመኛ ባንዋን ከሚባል አገር ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት ሆነ። ይህም ቅዱስ አስቀድሞ ወንበዴ ነበር ሌሎችም ሁለት ወንበዴዎች ነበሩ ገንዘቡን ሊሰርቁ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደ አንድ መነኩስ በአንድነት ሔዱ በጸሎትም እየተጋ አገኙት ጸሎቱን ጨርሶ እስቲተኛ ድረስ ጠበቁት እርሱ ግን ከቶ አልተኛም በልቡናቸውም ፍርሀት አደረባቸውና ደነገጡ።
በነጋ ጊዜም ያ ሽማግሌ መነኰስ ወደ ሽፍቶቹ ወጣ ባዩትም ጊዜ ከእግሩ በታች ሰገዱ ሰይፎቻቸውንም በፊቱ ጥለው ደቀ መዝሙሮቹ ያደርጋቸው ዘንድ ለመኑት በርሱም ዘንድ መነኰሱ። ቅዱስ አባ አበከረዙንም በሥጋውም በመንፈሱም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። አንድ አረጋዊም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰማዕት ይሆን ዘንድ እንዳለው ነገረው።
ከሰባት ዓመት በኃላም ሰይጣን በክርስቲያን ወገኖች ላይ መከራን አመጣ አባ አበከረዙንም ተነሥቶ መንፈሳዊ አባቱን እጅ ነሥቶ ከእርሱም ቡራኬ ተቀብሎ ኒቅዮስ ወደሚባል አገር ሔደ ንጉሥ መክስምያኖስንም አገኘው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰም በፊቱ ታመነ መኰንኑም በጽኑ ስቃይ አሰቃየው በብረት መጋዝም ስጋውን መገዘው ቁስሉንም በመጣጣና በጨው አሸው።
ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ከተማ ሲወስዱት አምስት ጊዜ በመርከብ ምሰሶ ላይ ሰቀሉት ገመዶችም ተበጠሱ ከማስ በተሠራ ጋን ውስጥም አድርገው በባሕር ጣሉት ከእግዚአብሔርም የተላከ መላክ ከባሕር አውጥቶ ወደ ገምኑዲ ከተመሰ እንዲሔድ አዘዘው ብንውም ወደሚባል አገር ደረሰ ስለ አባ አበከረዙንም ጠየቀ እነርሱም አላወቁትም ነበርና ከብዙ ጊዚያትም ጀምሮ ከዚህ ሔዷል ወዴት እንዳለም አናውቅም ወሬውንም አልሰማንም አሉት።
አንዲት ብላቴና ግን አስተውላ አወቀችው ፈራችም ከፍርሀቷም ብዛት የተነሣ ወደቀችና እንስራዋ ተሰበረ እርሷም ሰዎች ይህ አባ አበከረዙን ነው አለቻቸው የአገሩ ሰዋችም ሁሉም ፈጥነው መጥተው ከእርሱ ተባረኩ ደዌ ያለባቸውም ወደርሱ ይመጡ ነበር እርሱም በዘይት ላይ ጸልዮ ሲቀባቸው ወዲያውኑ ይድኑ ነበር።
ከዚህም በኋላ ወደ ገመኑዲ ከተማ ሔደ ከወታደሮቹም አንዱን እኔ ክርስቲያን ነኝና በዚች ከተማ ውስጥ አሥረህ ጎትተኝ አለው እርሱም ወደ መኰንኑ እስከሚአደርሰው እንደ አዘዘው አደረገ መኰንኑም በእንጨት ላይ ዘቅዝቆ ሰቀለው በአፍንጫውና በአፋም ብዙ ደምእየፈሰሰ ዐሥር ቀኖች ኖረ አባ አበከረዙንም የጭፍራ አለቃውን ልጅ ረገማትና ወዲያውኑ ሞተች በመቃብርም ዐሥራ ሁለት ቀኖች ኖረች። ስለ እርሷም አባ አበከረዙንን ለመኑት ክብር ይግባውና ወደጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየ ያንጊዜም ከሙታን ተለይታ ተነሥታበሲኦል ያየችውን ሁሉ ነገረቻቸው ከጭፍሮቹ ጋር ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ ቁጥራቸውም ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት ነፍስ ነበር።
ከዚህ በኋላ አባ አበከረዙንን ወደ እስክንድርያ ሰደደው በዚያም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ዳግመኛ ወደ ገምኑዲ ላኩት በዚያም በብረት በትሮች ደብድበው የጀርባውን አጥንት ሰበሩት እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ዳነ።
መኰንኑም ማሰቃየት በደከመ ጊዜ ዳግመኛ ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው ወደ እስክንድርያም በሚያዚያ ወር በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለትና አጽናናው ገድሉንም በዚያ እንደሚፈጽም ነገረው።
ስሙን ለሚጠራ ሁሉ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ ኃጥያቱን እንደሚያስተሠርይለት ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኃላ ራሱን ቆረጡት ተጋድሎውንም ፈጽሞ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ።
የእግዚአብሔር መልአክም መኑፍ ከሚባል አገር ለአንድ ቄስ ተገልጦ የቅዱስ አበከረዙን ሥጋ ያለበትን ቦታ ነገረውና እንዲወስደው አዘዘ። እርሱም ወስዶ ባማሩ ልብሶች ገነዘው የመከራውም ወራት እስከሚፈጸም በመልካም ቤት አኖረው ከዚህም በኋላ ቦታ ክርስቲያን ሰርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
ቅዱስ ሰማዕት ዱማድዮስ
ዳግመኛም በዚች ቀን የሶርያ ሰው ቅዱስ ሰማዕት ዱማድዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ በፋርስ አገር አደገ የከዋክትን ምግብን ጥበብ ተማረ ከዚህም በኋላ ክርስርስቲያን ሊሆን ወደደ ከፋርስ ሰዎችም ስሙ አጋሊዮስ የሚባል ቄስ በገበያ ውስጥ አገኘ እርሱም ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ ሃይማኖትን አስተማረው እጅግ ደስ ብሎት ቤተሰቦቹን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ያስተምራቸው ጀመረ አሳመናቸውም።
ከዚህም በኋላ በሶሪያና በሮም መካከል ወዳለች አገር ሔደ በዚያም የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቆ መነኮሰ ታላቅ ተጋድሎንም መጋደል ጀመረ መነኰሳቱም ታላቅ የሆነ ተጋድሎውን በአዩ ጊዜ በእርሱ ላይ ቀንተው ከገዳም ሊያሳድዱት ወደዱ።
በአወቀም ጊዜም ወጥቶ ወደ ቅዱስ ሰርጊዮስ ገዳም ሔደ በዚያም በአንድ ባህታዊ ቄስ ዘንድ ተቀመጠ ከዚህም በኋላ ዲቁና እንዲሾመውና ከእርሱ ጋር በቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግል ቅዱስ ዲማድዮስን አስገደደው ትዛዙንም መተላለፍ ባልተቻለው ጊዜ ዲቁና ተሾመ።
አረጋዊው ቄስ በመሰዊያው ላይ በሚሰየም ጊዜ በቅዳሴው እኩሌታ በምሥዋቱ ላይ ርግብ ስትወርድ ቀዱስ ዱማድዮስ ያያት ነበር እርሱም ሥጋዊት ርግብ እንደሆነች ያስብ ነበር ሽማግሌው ግን አያያትም ነበር የቅዳሴው ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ባሕታዊው ቄስ እንዲህ ብሎ ጠየቀው በቅዳሴ ጊዜ የምትደነግጥ እጅህንም ወደ መሥዋቱ የምትዘረጋው ምን ሆነህ ነው እርሱም ርግቧን እንዳያት ነገረው ከእንግዲህ ስታያት ንገረኝ አለው።
ከዚያም በኋላ በአያት ጊዜ አባቴ ሆይ ያቺ ርግብ መጣች ብሎ ነገረው ሽማግሌው ግን አላያትምእጅግም አዝኖበእግዚአብሔር ፊት ሰገደ ያቺንም ርግብ እስከሚያያት ድረስ ፈጽሞ ይጸልይና ይማልድ ነበር ያቺ ርግብ መንፈስ ቅዱስ እንደ ሆነ ያውቅ ነበርና ለዲያቆን አባ ዱማድዮስም ልቡ እንዳይታበይ አልነገረውም።

ከዚህ በኃላም ሽማግሌው ቄስ ወደ ኤጲስቆጶስ ሒዶ ዱማድዮስን የቅስና መዐረግ ይሾምለት ዘንድ ለመነው ልመናውንም ተቀብሎ ያለ ውዴታው ቅስናን ሾመው።
ሊቀ ጳጳሳቱም ዜናውንና ገድሉን በሰማ ጊዜ ከእርሱ ጋራ ወገኖቹን ወሰደ ከወገኖቹ ጋራም ወደርሱ ሔዶ በረከቱን ሊቀበል ወደደ። ቅዱስ ዱማድዮስ ግን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ከዚያ ተሠውሮ ሔደ ወደ ሰማዕቱ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንም ደረሰ ከዚያም ወደ በረሀ ሔዶ በዚያ ሣር እየበላ ኖረ እርሱ ከከንቱ ውዳሴ ይሸሽ ነበረና።
እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆችንና ተአምራቶችን ያደርግ ነበር። በአንዲት ቀንም ውኃ ሊቀዳ ወደ ወንዝ ሔደ ውኃ የሚቀዱ ሴቶችም አይተውት በመጠቃቀስ በእርሱ ላይ ተዘባበቱ በልቡም እያዘነ ውኃ ሳይቀዳ ተመለሰ ያን ጊዜም ወንዙ ደረቀ።
ሰዎችም ቅዱስ ዱማድዮስ እንዳደረቀው በአወቁ ጊዜ ሴቶችና ወንዶች ሁሉ ወጥተው በብዙ ለቅሶ ለመኑት ልቅሶአቸውንም አይቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን ለመነው የወንዙንም ውኃ እንደ ቀድሞው መለሰላቸው።
ሰዎችም ሲያከብሩት በአየ ጊዜ ከዚያ መጠለያ ከሰማይ በታች ያለውን የበጋውን ቃጠሎና የክረምቱን ቅዝቃዜ ታግሦ እየተጋደለ ዓመት ሙሉ ኖረ በብዙ ድካምም አስገድደው ትንሽ ጎጆ ሠርተው በውስጧ አስገብት።
ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ ከእነርሱም አንድ ዐይኑ የታወረች አንድ ሰው ነበረ ከእርሱም በተባረከ ጊዜ ዐይኑ ድና አየች እንደ ሁለተኛዋም ሆነች ሁለተኛም ጉባጣ ሰው ወደርሱ አመጡ በውኃና በዘይትም ላይ ጸልዮ የመጻጉዑን ሥጋ አጥቦ አዳነው ዲዳውንም እንዲሁ አዳነው።
ከዚህም በኃላ ባልና መካን ሚስቱ መጡ ስለ እነርሱም ይጸልይ ዘንድ ለመኑት እርሱም ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ለምኖላቸው ልጆችን ሰጣቸው ወደርሱም ልጆቻቸውን አምጥተው ባረካቸው። ከዚህም የሚበዛ ብዙ ተአምራትን አደረገ።
በከሀዲው በዋሊጦስ ዘመንም የአምላክ ወዳጅ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ ያሠራቸውን አብያተ ክርስቲያናት ጭፍሮቹ ወደ አንጾኪያ መጥተው አፈረሱ። ከዚህም በኃላ የፋርስ ሰዎች ጦርነት ሊገጥሙት መጡ ሲጓዙም ወደ ቅዱስ ዱማድዮስ ማደሪያ ደረሱ ስለ ርሱም ለመኵንኑ ነገሩት እርሱም ይወግሩት ዘንድ አዘዘ ከረድኡም ጋራ በድንጊያ ወገሩት። የጣሉባቸው ድንጋይም በበዐታቸው ላይ ታላቅ ኮረብታ ሆነ። እርሱና ረድኡም እንዲህ በሆነ ድርጊት አረፉ።
ከአንድ ዓመትም በኃላ ለአንድ መንገደኛ ነጋዴ ሰው ገለጠለት።ገመልም ጭኖ ነበር። እርሱም ሲያልፍ ገመሉ ከምድር በታች በጉድጓድ ውስጥ ወደቀ። ሰዎችም ገመሉን ሊያወጡት በመጡ ጊዜ የቅዱስ ዱማድዮስ በዐት ተገለጠ። ቆፍረውም የቅዱስ ዱማድዮስንና የረድኡን ሥጋ በክብር አወጡ ይኸውም በአረፈበት በሐምሌ ሃያ አምስት ቀን ነበር። ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው የእርሱን ሥጋና የረድኡን ሥጋ በውስጥዋ አኖሩ ጌታችንም ከእርሱ ብዙዎች ተአምራትን ገለጠ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ 25)
🗓 ሀምሌ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ዕርገቱ)
3.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
4.ቅዱስ አበከረዙን ታላቁ (ጻድቅና ሰማዕት)
5.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ (ጻድቅና ሰማዕት)
6.ቅድስት ኢላርያ ሰማዕት
7.ቅዱሳት ቴክላ ወሙጊ ሰማዕታት
8.ቅዱስ እንዲኒና ሰማዕት
9.አባ ይስሐቅ ሰማዕት
10.አባ ሕጻን ሞዐ ዘደብረ ሊባኖስ
11."25,000" ሰማዕታት (የአትሪብ /ግብፅ/ ሰዎች)
🗓ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
3.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
የሀምሌ 25 ቀን የእለቱ ግጻዌ
መልእታት
👇
1ቆሮ 2÷1-ፍጻ
ይሁዳ 1÷16-17
ሐዋርያት 26÷6-12
ምስባክ👇
"መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ። አምላከ እግዚአብሔር ውእቱ ይሁብ ኃይለ ወጽንዐ ለሕዝቡ ወይትባረክ እግዚአብሔር ።"መዝ 67÷34-35
ትርጉም➣"ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፤ ግርማው በእስራኤል ላይ፥ ኃይሉም በደመናት ላይ ነው። እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤ እግዚአብሔርም ይመስገን።"መዝ 68÷34-35
የእለቱ ወንጌል📖
👇
ማርቆስ 13÷5-14
የሚቀደሰው ቅዳሴ
👇
ቅዳሴ ዘወልደ ነጐድጓድ ነው።

If an unexpected temptation comes, don't blame the one through whom it came, but seek out the reason. Thus you will find correction for your soul.
(St. Maximus the Confessor, Chapters on Love, 2.42)
❤2
በዚህ የታላቋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጾም ወቅት
ጾመ ፍልሰታ
ስለእርሷ የቅድስናዋ ነገርና ክብር የምንማር ይሆናል።
🥰2
የእመቤታችን የእረፍቷ እና የትንሳኤዋ ነገር በጥንታውያን ( ነባር ) ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ዘንድ የታመነ ነገር ነው።
እርሷ በልጇ ፈቃድ ሞትን ቀመሰች በልጇ ፈቃድ ሞትን አሸንፋ ተነሳች።
🤩2
“It is impossible to be saved without the help of the Most Blessed Virgin, because those who are not saved by the justice of God are saved by the intercession of Mary.”
– St. John Chrysostom
❤3
" But the pious confession of the believer is that, with a view to our salvation, . . . the Creator of all things incorporated with Himself a rational soul and a sensible body from the all-holy Mary, ever-virgin, by an undefiled conception, without conversion, and was made man in nature, but separate from wickedness: the same was perfect God, and the same was perfect man; the same was in nature at once perfect God and man.” — St. Hippolytus of Rome, Against Beron and Helix, Frag VIII, 210 AD
🥰1