ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
1.5K subscribers
1.09K photos
20 videos
13 files
247 links
Download Telegram
እየሞትን እንበዛለን ማለት አቁመን እንዴት ነው ክርስቶስ ዋጋ የከፈለለትን የአንድ ክርስቲያን የግፍ ሞት ማስቆም የምንችለው የሚለውን ብናስብ መልካም ነው። ዛሬ ዝም የተባለ ግፍ ካልቆመ ነገ በራስ ነው።

ለሞቱት ነፍስ ይማር 🤲
“ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።”  — ሐዋርያት 5፥15

መጽሐፍ ቅዱስ የሐዋርያው ጴጥሮስ ጥላውን ይፈውስ እንደነበረ ይነግረናል። ይህም አዳኝ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ በቅዱሳን ላይና በእነርሱ በሆነው ላይ ሁሉ እንዳለ ማሳያ ነው።

ጥላ የሚባለው በብርሐን መሰናክል የማፈጠር የአንድ አካል ጥቁር ምስል ነው። ያ ይፈውስ የነበረውም የጴጥሮስ ጥላም ይሄው አይነት ነው። ይህን ጥላ ነጮች Shadow Art ይሉታል። እኛ በምድር የተሳለ ጥቁር ስእል ማለት እንችላለን።

“ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለችው ከተማ ድውያንንና በርኵሳን መናፍስት የተሣቀዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤ ሁሉም ይፈወሱ ነበር።”— ሐዋርያት 5፥16

ተወዳጆች ሆይ የሰውነን ቅርስን ብቻ የሚያሳየው የጴጥሮስ  ጥላ እንዲህ በእግዚአብሔር ሐይል ተአምር ሲሰራ ካያችሁ፤ በወግና በስርአት በቅዱስ ትውፊት እንዲሁም ሐዋርያው የህይወት ታሪክ ላይ ተመርኩዞ የሚሳሉ ስእሎች ምነኛ ተአምር ይሰሩ ይሆን?!

ይህን አንድ ምሳሌ ሁሉም ቅዱሳት ስእላትም የእግዚአብሔር እያደረባቸው እንደሚፈውሱ ማሳያ ነው።

ይቆየን።
🥰4❤2
አሁንም በአርሲ ለተጨፈጨፉ ኦርቶዶክሳዎያን ክርስቲያኖች ድምጽ እንሁን።

ለፈሰሰው ደምና ለወደመው ንብረት ሃላፊነት የሚወስድ ማነው?

ተጠያቂውስ ማነው?

ድጋሜ እንዳይከሰት ምን እየተደረገ ነው?

ነፍስ ይማር።
😢2
ቅዱሳን ከሞቱ በዋላ ያማልዳሉ?

“በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።”— ራእይ 6፥10

🌼 ይህን ልመና የለመኑት በሥጋ ያረፉ ቅዱሳን ናቸው። ስለፈሰሰው ደማቸው እውነተኛ ፍርድን ከጌታ ጠየቁ። በሥጋ ሳይኖሩ ይህን የፎትህ ጥያቄና ልመናን ማቅረብ ከቻሉ፤ ለኛ ለሰው ልጆች በምድር ላለነው ፧ ጸሎት እንደሚያቀርቡ ትልቅ ማሳያ ነው።

ቅዱሳን ከሞቱ በኃላ በምድር ስላለው ነገር አያውቁም ማለት ሞኝነት ነው። እንደውም በሥጋ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላ እውቀታቸው የበለጠ ይጨምራል።

“ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።”— 1ኛ ቆሮንቶስ 13፥12
❤2
“አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።”

— ያዕቆብ 1፥26
❤1
የእግዚአብሔር ሃይል በቅዱሳን በሆነው ሁሉ ላይ ይሰራል።
❤2
ፀሐይ ከሙቀቱ ጋር ሲወጣ ሣሩን ያደርቀዋል አበባውም ይረግፋል፤ ውበቱም ይጠፋል፤ እንዲሁም ሀብታም ሰው በሥራው ሲባክን ይጠፋል።

— ያዕቆብ 1:1
❤3
እምነትና መልካም ኅሊና ይኑርህ። አንዳንድ ሰዎች ኅሊናቸውን በመጣላቸው መርከብ በማዕበል እንደሚጠፋ እምነታቸውን አጥፍተዋል።

— 1ኛ ጢሞቴዎስ 1:19
🔥2
ስብሐት ለእግዚአብሔር ተብሎ ለምን ስብሐት ለማርያም ይባላል?

ይህ የእግዚአብሔርን ምስጋና ለእመቤታችን መስጠት አደለም። ስብሐት ለእግዚአብሔር ሲባል አምልኮ ነው( ስለፈጠርከን ስላዳንከን ወራሽ ስላደሰከን) እናመሰግናለን እያልን የምናመሰግነው። ስብሐት ለእመቤታችን ሲባል የአክብሮ ምስጋና ነው ልክ ቅዱስ ገብርኤል እንዳመሰገናት እርሷም እንዳለችው ሉቃ 1:49። የሚበላውን ሥጋ የሚጠጣዎን መጠጥ ስለወለደች ስብሐት ለማርያም ይባላል።

አብራ ከእግዚአብሔር ጋር መጠራቷ የእግዚአብሔርን ምስጋና ለእርሷ አያሰጠውም።

ለምሳሌ

“ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።” — ሐዋርያት 15፥28-29

ሐዋርያት ራሳቸውን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጠቅሰው #ፈቅደናል ስላሉ እኩል ናቸው ማለት እንዳልሆነ ስብሐት ሲባል ሁሉ አምልኮ እንዳልሆነ መረዳት ተገቢ ነው።
❤2
'' ሁልጊዜ ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ። እነርሱም :- ክፉ ከመናገር መከልከል፣ ማንንም ሰው እንደ ጠላት ከመመልከት መቆጠብና እንደ ልምድ አድርጋችሁ ከያዛችሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ።''

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
❤4🥰3
“ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤”
— ሉቃስ 22፥31

የወደቀው መልአክ ሰይጣን እግዚአብሔርን ለአላማው መለመን ከቻለ፤ ቅዱሳን መልአክት ስለኛ ሰዎች መዳን፣ ደስታና ሰላም መነኛ ይለምኑ ይሆን?!
“የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቆጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ። እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ለሚነጋገረው መልአክ በመልካምና በማጽናናት ቃል መለሰለት።”
— ዘካርያስ 1፥12-13



የክፋት ምንጭ የሆነው ሰይጣን እንኳ ሰዎችን ለማጥፋትና “እንደ ስንዴ ለማበጠር” ፈቃድ ጠይቆ መለመን ከቻለ፤ በፍቅር የተሞሉ፣ የእግዚአብሔርን ፊት ዘወትር የሚያዩ (ማቴ 18፥10) ቅዱሳን መላእክትማ እጥፍ ድርብ በሆነ ፍቅርና ትጋት ስለ እኛ መዳን፣ ሰላም፣ ጤና እና ደስታ በእግዚአብሔር ፊት ይለምናሉ።

ሰይጣን ክስንና ጥፋትን እንደሚያቀርብ ሁሉ፣ ቅዱሳን መላእክት ደግሞ ምሕረትንና ጥበቃን ይለምኑልናል። ስለዚህ በሕይወታችን የምናገኘው ሰላምና ጥበቃ በስተጀርባ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነትና የማያቋርጥ ልመና አለበት።
ቅዱስ ሚካኤል መልካም ነገርን ሁሉ ያሰማን
ሐሳባችንን ይሙላልን
ከመከራ ከበሽታ ከጉስቁልና ይጠብቀን።
❤11
የባህራንን የሞትና የመከራ ደብዳቤ ወደ ሕይወትና ወደ ደስታ የቀየረ፥

ክርስቲያኖችን ወዳጆቹን የሚወድ የሚጠብቅና የሚረዳ፥

የጌታ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ የከበረ ኃያል መልአኩ፥

በመላእክት ሁሉ በአለቃነት የተሾመ

መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በምልጃው በበረከቱ ይራዳን።
❤1
ከዚህ በኋላ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩ ነጸብራቅ የተነሣ ምድር በራች፤

— ራዕይ 18:1 ሚ ካ ኤ ል
❤2